"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Monday, 20 August 2012

የህወሃት አመራር አባላት አሁንም በከፍተኛ ውጥረት ላይ ናቸው በረከት ስምኦን ስብሃት ነጋን ከስራው አገዷቸው !

በሰሞኑ የኢትዮጵያን አመራሮች እና በህወሃት የቀድሞው አመራር አካል አቶ ስብሃት ነጋ  ከፍተኛ ውጥረት ሲኖር  ባለፈው ሳምንት በዚሁ ጉዳይ ላይ መዘገባችን ይታወሳል ።በዛሬው እለት ከኢዮጵያ በደረሰን ዜና መሰረት የመገናኛ ብዙሃን ሚንስትር መስሪያ ቤት አመራር አካላት አንዱ ከሆኑት አንዱ አቶ በረከት ስምኦን የኢንፎርሜሽን ሚንስትሩ አቶ ስብሃት  ነጋ (አቦይን) ለማገድ በቅተዋል ። ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ሳታላይት ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ መጠይቅን አስመልክቶ እገዳው እንደተጣለባቸው የማለዳ ታይምስ ዘጋቢ ከስፍራው  ገልጾአል ።
በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የመገናኛን አፈና  ከጊዜ ወደዜ  እየተባባሰ መምጣቱን አስመልክቶ ይህ በባለስልጣኖቻቸው የሚደረገው አፈና እና እገዳ በበለጠ በግልጽ አፈናውን የሚያሳይ መሆኑን ማእከላችን ይገልጻል ። ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ከስልጣናቸው ላይ ከተለዩ ጊዜ ጀምሮ የህወሃት አባሎች መላ ቅጡ የጠፋቸው ከመሆኑ በላይ እርስ በእርሳቸው ከመባላታቸውም አልፈው የስልጣን ሽኩቻቸውን በገሃድ አውጥተውታል ። በትላንትናው እለት የኢትዮጵያን ሪቪው ድህረ ገጽ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በጠቅላይ ሚንስትሩ ቦታ  መተካታቸውን የዘገበ ሲሆን የአሜሪካ ባለስልጣናቶች በጠቃላይ ሚንስትሩ ቦታ ጣልቃ ገብተው ስልጣኑን እንዳስረከቧቸው መገለጹን ይታወሳል
በአሁን ሰአት የኢትዮጵያ ጉዳይ ያሳሰባቸው ኢትዮጵያኖች ስለ ሃገራቸው ወቅታዊ ጉዳይ ወቀሳ ያቀረቡ ከመሆኑም በላይ አስቸኳይ የሆነ መግለጫ ከመንግስትም ሆነ ከመላው አለም አቀፍ ተቋማት መቀረብ እንዳለበት አሳውቀዋል ። በተለይም ባሳለፍነው ሳምንት የኢንፎርሜሽን ሚንስትሩን ጨምሮ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ስብሰባ ያደረጉ ሲሆን በዚህ ስብሰባቸው ዋነኛ አጀንዳ የሆነው በእነ አቦይ ስበሃት ነጋ ለረጅም ጊዜ ሲመራ የነበረውን የህወሃት ድርጅትን አፍርሶ በራሳቸው ቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያደርጉት ትልቅ ትግል መሆኑን ከተገለጸ በሁዋላ የህዝቡ እና የተቀዋሚ ፓርቲዎች ጠንካሬአቸውን አሳይተው ሃገራቸውን ከአስከፊ ስቃይ መታደግ እንዳለባቸው ጠቁመዋል ።
በተለይም ኢትዮጵያ በውጭው አለም ያላት ገጽታ በአስከፊ ጦርነት እና በረሃብ መሆኑ እየታወቀ የኢሃዴግ መንግስት ድህነቱን ደብቆ የፖለቲካ አጀንዳውን የእራሱ ብቻ ማድረግ መቻል የለበትም ሲሉ ህብረተሰቦች አመክረው ይገልጻሉ ። የሁላችንም የጋራ ሃገር እና የጋራ ጥያቄ መሆኑን የጠየቁት ዜጎች የህዝቦችን እኩልነት በፖለቲካዊ ልዩነት ጥቁር ጥላሸት መቀባት የለባቸውም  ልዩነታቸውን አጥብበው የሃገሪቱን ሰላም ማስፈን አለባቸው ሲሉ ገልጸዋል ። ሆኖም ግን የወያኔ ኢሃዴግ መንግስት ይህንን አይነት ሃሳብ አይፈልግም ፣ተቻችሎ መኖርን የለመደው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን አሁንም አንድነቱን እና በዘር ተከፋፍሎ መተያየቱ በጣም በአደገኛ ሁኔታ አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ ለአገሪቱ የሚሰጠው ፋይዳ ምንም እንደሌለው አወቆ ተገንዝቦታል። በተለይም የህወሃት አባሎች ከአዜብ መስፍን እና መለስ ወገን ደግፈው የሚኖሩት አንጃዎች የኢትዮጵያን አንድነት የሚፈልጉ እንዳልሆኑ ይታወቃል ፣በዚህም ጉዳይ ስብሃት ነጋ አንደኛው አባል ሲሆኖ አሁን ግን ገለል ተደርገው የሚታዩ አካል ተደርገው እየተቆጠሩ እንደሆነ በኢንፎርሜሽን ሚንስትሩ በኩል የተላለፈው ትእዛዝ የሚገልጽ ሃሳብ ነው ።የሚንስትር መስሪያቤቶች በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያለው ጨዋታ የቁማር አይነት ከመሆኑም ባሻገር የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በህይወት የመኖር እና ያለመኖር ጉዳይ ከህብረተሰቡ ይልቅ ለህወሃት አባሎች ምንም ዴንታ እንዳልሰጣቸውም ከሁነቶቹ ያስታውቃሉ ያሉ አንዳንድ አሰተያየት ሰጭዎችም ሃሳባቸውን ገልጸዋል ።

No comments:

Post a Comment