"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Sunday, 3 June 2012

በነገው ዕለት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ይደረጋል።





Sunday, June 3rd, 2012 | Posted by zehabesha
በርከት ያሉ ምዕመናን በዋልድባ ጉዳይ በሚደረገው ሰልፍ ለመካፈል ወደ ዲሲ እየተመሙ ነው
13
Share
(ዘ-ሐበሻ) በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ መንግስት የዋልድባን ገዳም እየተፈታተነበት ያለውን ድርጊት በመቃወም በነገው ዕለት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ይደረጋል። በዋሽንግተን ዲሲ ለሚደረገው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለመሳተፍ ከሚኒሶታ ኢትዮጵያውያን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች በመኪና ተጉዘው ዋሽንግተን ዲሲ ገብተዋል።
ትናንት ቅዳሜ ጁን 2 ቀን 2012 ከሚኒሶታ የተነሱት ምዕመናንን ጨምሮ ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የተንቀሳቀሱ ምእመናን በዋሽንግተን ዲሲ ሲደርሱ እዚያ የሚኖረው ምእመናን ደማቅ አቀባበል እንደተደረገለት የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዘጋቢዎች ከስፍራው ተናግረዋል።
ከሚኒሶታ የተንቀሳቀሰው ቡድን 8 የ እንግሊዘኛ እና 8 የአማርኛ መፈክሮችን ይዞ እንደሄደ የታወቀ ሲሆን በአጠቃላይ በዋሽንግተን ዲሲ እንዲሁም በሎስ አንጀለስ ነገ ጠዋት በሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ወደ 40 የሚጠጉ መፈክሮች እንደተዘጋጁ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
በዋሽንግተን ዲሲ፣ በሎስ አንጀለስና በሌሎች የአለማችን ክፍሎች የሚያዙት 18 የእንግሊዘኛ መፈክሮች የሚከተሉት ናቸው። በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያዘውን 18 የ እንግሊዘኛ መፈክሮች PDF ለማየት እዚህ ይጫኑ
ከሚኒሶታ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሄዱ ም እመናን የያዟቸው 16 የአማርኛና የ እንግሊዘኛ መፈክሮችን PDF ለማየት እዚህ ይጫኑ
ነገ ጁን 4/2012 በዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገውን ሰልፍ ለመዘገብ የዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ ሪፖርተርም ዋሽንግተን ዲሲ ገብታለች። ዘገባዎችን እንዳደረሰችን ለድረ ገጻችንን አባቢዎች እንደምናቀርብ ከወዲሁ እንገልጻለን።

በAውራምባ ታይምስ የተቆረጠው የታማኝ ቃለ-መጠይቅ


በAውራምባ ታይምስ የተቆረጠው የታማኝ ቃለ-መጠይቅ
Aርቲስት ታማኝ በየነ ከAውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ጋር የቃለ-ምልልስ  Eንዲያደርግ ከAዘጋጁየ ቀረበለትን
ጥያቄ ተቀብሎ ቃለ-ምልልስ  Aድርጎ ነበር፡፡ ቃለ-ምልልሱ በጋዜጣው ታትሞ ከወጣ በኋላ ግን: ለጋዜጣው
Aዘጋጅ በላከው ደብዳቤ "ቃለ ምልልሱን Aነበብኩት፡፡ ስሜንና ፎቶግረፌን ከመያዙ በቀር የኔ ሀሳብ የምለው
Aንድም በውስጡ ባለመኖሩ በጣም  Aዝኛለሁ፡፡"  ሲል ቅሬታውን ገልጿል፡፡ የAውራምባ ታይምስ  Aዘጋጅ
ቃለ-ምልልሱን  Eንዳለ ቢያወጣው በህይወቱ ላይ  Aደጋ ሊያስከትልበት  Eንደሚችል ገልጾ ሙሉውን
ባለማተሙ ይቅርታ ጠይቋል፡፡   ለAንባቢያን ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ሙሉውን ቃለ-ምልልስ  Eንደሚከተለው
Aውጥተነዋል፡፡
ከAውራምባ ታይምስ:- Eንግዲህ በAሁኑ ሰዓት ለAገር ለወገን ትልቅ ስራ ሰርተው ያለፉ ታላላቅ
Iትዮጵያወገኖችን በማስታወስ ብዙ  Eንቅስቃሴዎችን በማከናወን ላይ  Eንደምትገኝ ይታወቃል፡፡  Eስኪ
ለAገር ውስጥ Aንባቢ ጠቅለል Aድርገህ ብትገልጽልኝ?

ቴዲ ወይስ ታማኝ


                                                              ቴዲ  ወይስ ታማኝ 


እኔ ለጸብ ለምን እቸኩላለሁ?
ማንምሰው ደግሞ የፖለቲካን ጉዳይ የጠላውን ሰው የሚያወግዝበት፤የወደደውን ሰው
የሚያሞካሽበት የግል መሣሪያ    አይደለም። ከዚህ  Aስተሳሰብ ካልወጣን በጣም ትልቅ
ሆና፣ ፍትህ የነገሠባትን ታላቂቱን ኢIትዮጵያ ለማየት በጣም  አስቸጋሪ    ይሆናል።
ለማንኛውም    በየቦታው    ለነበረው ሁኔታ ጥሩመስተንግዶ    አድርገው    ለተቀበሉን
ኢትዮጵያውያን  ከፍ  ያለ  ምስጋናዬን  አቀርባለሁ።  በተለይ  በተለይ  ደግሞ  እስር
ቤት  ሆኜ  ብዙ  በመጨነቅ፣ በመፀለይ፣  ከዚያም  አልፎ  ሰልፍ  በመውጣት  ብዙ
ስለእኔ    ለከፈሉት    ኢትዮጵያ ውያን    ወገኖቼ    ከፍተኛ   ምስጋናዬን    እያቀረብሁ፤
የፍቅር   ሠራዊት    የሆነውን    ባንዳችንን  (የሙዚቃ   ጓዳችንን)   ይዘን    ገና    ብዙ
ለመሄድ    እንበረታለን    ከእግዚAብሔር    ጋር።    ቴዲ  አፍሮ ይህን ያለው በስዊድን
ከጋዜጠኛ ያሬድ ክንፈ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስነበር። ጋዜጠኛው በኖርዌይ ቴዲ
አፍሮ ቦይኮት  እንዲደረግ ሰዎች ሲያስተባበሩ  እንደነበር ጠቅሶ ቴዲን በጉዳዩ ላይ
ሲጠይቀው ነበር ይህን ያለው።ቴዲ  አፍሮ ከእስር ከተፈታ በኋላ ባደረጋቸው የሙዚቃ
ኮንሰርቶች ‘’ጃ ያስተሰርያል” ከሚለው ዘፈኑ ውስጥ ገዢውን ፓርቲ ይነካል የሚባለው
17 መርፌ የሚለውን ግጥም ቆርጦ ማውጣቱ በብዙዎች ዘንድ ውግዘትን እያስከተለበት
ሲሆን በአንጻሩ ለውግዘት ያልቸኮሉ ወግኖችም ተቀምጠዋል። የዘሐበሻ ጋዜጣ
ካነጋገራቸው  ኧንድ ስማቸውን መጥቅስ ያልፈልጉ ሰው  እንዳሉት  ‘ቴዲን  እኛ
የወደድነው ሄዋን  እንደዋዛን ስለዘፈነ  አይደለም። በድፍረቱና በተለይም ጃ ያስተሰርያል
በሚለው ዘፈኑ Eንጂ። Aሁን ያንን ቆርጦ ከዘፈነው Eውነትም ቴዲ Aልተፈታም ማለት
ነው”  ሲሉ ሌላ  Aስተያየት ሰጪ ደግሞ  ‘ቴዲ የፈለገውን ማድረግ ይችላል  Eኛ
Eንወደዋለን”  ይላሉ። ይህ በEንዲህ  Eንዳለ ቴዲ  Aፍሮ ከEስር ቤት ከወጣ በኋላ
ባደረጋቸው ነገሮች Aሜሪካ የሚገኘው ታማኝ በየነ Eና Aንዳንድ Iትዮጵያዊያን ደስተኛ
Eንዳልሆነ በማስመሰል በIትዮጵያ የሚታተመው Eቴጌ መጽሄትን ጨምሮ በራዲዮ ፋና
ላይ የሚተላለፈው Iትዮፒካ ሊንክ ፕሮግራሞች  ‘የቴዲ  Aፍሮ ወቅታዊ  Aቋም ታማኝን
Aበሳጭቷል"  በሚል በየIንተርኔቱ  Eየተነዙ ያሉት ወሬዎች ሕዝቡን  Eያደናበሩት
መሆኑን የተነገነዘበው የዘሐበሻ ጋዜጣ የጉዳዩን ባለቤት በግልጽ  Aነጋግሮ የተጣራውን
ነገር ሕዝቡ Eንዲያገኝ ያደረገው ጥረት ታማኝን በማግኘት ተሳክቶልናል።
ዘሐበሻ፦ ታማኝ  Aንተ ለመጽሄቱ በቴዲ  Aፍሮ  Aቋም ላይ ደስተኛ  Aይደለሁም ብለህ
ተናግረሃል?

አንገት ሲደፋ ምን ፈሰሰ?


                                                  አንገት ሲደፋ ምን ፈሰሰ?
SHARE THIS
       
TAGS

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም

ሰሞኑን አዲስ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፎቶግራፍ በብዛት በያለበት ይታይ ነበር፤ ያዘነ፣ የተከዘና አንገቱን የደፋ መለስ ዜናዊ! እኔን ቀልቤን የሳበው የጠቅላይ ሚኒስትሩን አንገት ሊያስደፋ የቻለው ነገር አይደለም፤ ወይም አበበ ገላው የተናገረው ነገር አይደለም፤ አበበ ገላው የተናገረውን ለመናገር ሙሉ መብት አለው፤ በተባለው ነገር የማይስማማ ሰው በማስረጃም ሆነ ያለማስረጃ የተባለውን ለማስተባበል መሞከር መብቱ ነው፤ የአሜሪካኑን ፕሬዚዳንት፣ ወይም የእንግሊዙን ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲህ ያለ ሁኔታ ቢያጋጥማቸው፣ ወይም በጆርጅ ቡሽ ላይ አንዱ ኢራቃዊ እንዳደረገው ጫማውን እያወለቀ ቢወረውርም ምንም የሚያስደንቅ ነገር አይኖርም፤ በ1928 ነው 29 አጼ ኃይለ ሥላሴ በቀድሞ የዓለም መንግሥታት ማኅበር መድረክ ላይ ሲናገሩ የኢጣሊያ ፋሺስቶች ያሰማሩአቸው ሰዎች ንግግሩን ለማደናቀፍ ጩኸትና ፉጨት ያሰሙ ነበረ፤ አጼ ኃይለ ሥላሴን አንገታቸውን አላስደፋቸውም፤ አበበ ገላው የወረወራቸው ቃላት ናቸው፤ ቃላቱ እውነትን የሚገልጹ ከሆነ በተግባራዊ ማረሚያ ይለወጣሉ፤ ቃላቱ ሐሰትን የሚገልጹ ከሆኑ እውነትን በሚገልጹ ቃላት ይደመሰሳሉ።


                                                      አንገት ሲደፋ ምን ፈሰሰ?

Mesfin Woldemariam (Prof.)

እዚህ ላይ አንድ ሌላ ነገር እናስታውስ፤ በመስከረም ግድም ይመስለኛል አቶ ኢሳይያስ አፈወርቅ በኒውዮርክ ነበረ፤ በዚያን ጊዜ በአንድ ስቴድየም ውስጥ የኤርትራ ተወላጆች ሁሉ (የቀረም ያለ አይመስልም!) በስቴድየሙ ታምቀው የኢሳያስን ዲስኩር ከሰሙ በኋላ አስተያየታቸውን እየሰጡና ጥያቄያቸውንም እየጠየቁ ሲወያዩ ነበር፤ ያስቀኑ ነበር፤ የኤርትራም ማኅበረሰብ እንደኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ውስብስብና ጉራማይሌ ነው፤ መሪው ህዝቡን ሳይፈራ፤ ሕዝቡም መሪን ሳይፈራ ተቀራርበው ለመወያየት መቻላቸው እኛን የትና የት ጥለውን እንደሄዱ አያሳይም የሚል አለ? ይህንን እውነት ቢያንስ የዛሬ አሥራ አምስት ዓመት ግድም ሪፖርተር የመጀመሪያውን መጽሔት ባወጣ ጊዜ ሽፋኑ የኢሳይያስ አፈወርቅ ፎቶግራፍ ነበር፤ የመለስ አልነበረም፤ ለኢሳይያስም ከተደረደሩት የውዳሴ ርእሶች አንዱ ኢሳይያስ ለሕዝብ ቅርብ መሆኑ ነበር፤ በአንፃራዊ ዝምታ መለስን ይጎሽም ነበር፤ ዛሬ በጠብ ላይ በመሆናችን እውነትን የምናይበት ዓይናችን ተቸግሮ ይሆናል፤ ለማናቸውም የሪፖርተርን ዘገባ ያስታወስሁት በኒውዮርክ በተደረገው የኤርትራ ተወላጆች ስብሰባ የተነሣ ነው፤ ለመሆኑ በኒውዮርክ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ስብሰባ ቢጠራ መጀመሪያ ስንት ሰዎች ይገኛሉ? ከተገኙትስ ጋር የሠለጠነ ውይይት ይደረጋል? ወይስ በፓርላማ እንደተለመደው ያለ ይሆናል? ሳይናናቁ መሪና ሕዝብ ተከባብረው በነፃነት ሀሳባቸውን መለዋወጥ መቻል ትልቅ እርምጃ ነው።
በኒውዮርክ የተሰበሰቡትን የኤርትራ ተወላጆች ቁጥር የሚያህል ኢትዮጵያውያን ተሰብስበው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መወያየት የሚችሉ ቢሆን እንዴት ያኮራኝ ነበር፤ በበኩሌ ባንስማማም እንነጋገር እያልሁ ስጮህ ብዙ ጊዜ ሆነኝ፤ ክርር ምርር ብሎ ከዚህ ፍንክች አልልም፤ ለአጭሩም፣ ለረጅሙም፣ ለወፍራሙም፣ ለቀጭኑም፣ ለክርስቲያኑም ለእስላሙም፣ ለሁላችሁም የሚበጀውን እኔ አውቃለሁ ማለቱ አያቀራርበንም፤ መናናቅ አያቀራርበንም፤ መፈራራት አያቀራርበንም፤ አበበ ገላው የተናገረው እውነት መሆኑንና አለመሆኑን ወደጎን እንተወውና በኢትዮጵያ ውስጥ እነዚያኑ ቃላት፣ በዚያው የጋለ ስሜት ያለፍርሃት በልበ ሙሉነት መግለጽ የሚቻል ቢሆን የአሜሪካው ድራማ አያስፈልግም ነበር፤ ዋጋም የሚሰጠው አይሆንም ነበር፤ በአሜሪካ በድንገትና ዓለም ሁሉ በሚያይበት መድረክ ስለ መለስ ዜናዊ የተባለው ሁሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ተዝናንቶና ኮርቶ ሊያዳምጥ የሚችልበትን መድረክ በሃያ ዓመታት ውስጥ ሳያዘጋጅ መቅረቱ አንገቱን ለማስደፋቱ አስተዋጽኦ አድርጓል።
በኢትዮጵያ ሳይሆን በአሜሪካ፣ በኢትዮጵያ ፓርላማ ሳይሆን በትልቅ ዓለም-አቀፍ ስብሰባ፣ ጥቂት የአፍሪካ መሪዎች ብቻ በተጋበዙበት ስብሰባ፣ በተለይም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለአፍሪካ ተናጋሪ ሆኖ በተጋበዘበት የታላላቅ መሪዎች ስብሰባ ላይ መገኘቱ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ሊያኮራ የሚገባው ነገር ነበር፤ ቢመቸን የሚያኮራን ነበር፤ መኩራቱ ሳይሆንልን ቢቀርም የማናፍርበት በሆነ መልካም ነበር፤ ምስጋናና ከንቱ ውዳሴ እንደጠበል በሚረጭበት ትልቅ ዓለም-አቀፍ ስብሰባ ላይ ዘለፋና ነቀፌታ መስማት አንገትን ያስደፋል፤ ነገር ግን ከመለስ ዜናዊ ጋር ኢትዮጵያ በዚያ ስብሰባ ላይ አንገትዋን አልደፋችም?
በግድም ይሁን በውድ አንድ መሪ አንድ ሕዝብ አናት ላይ ከተቀመጠ፣ ብዙ ነገሮች ያያዝዋቸዋል፤ ከነዚህ ነገሮች አንዱ ክብር– ወይም ውርደት ነው፤ ሕዝብ ተዋርዶ መሪው ክብር አያገኝም፤ መሪው ተዋርዶ ሕዝብ ክብር አያገኝም፤ የአንዱ ውርደት ለሌላው ክብር ሊሆን አይችልም፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስብሰባው ላይ የተጋበዘው ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን አህጉርንም ወክሎ ነበር፤ በዚህ ሁኔታ ክብር ቢያገኝ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካን በሙሉም ያስከብር ነበር፤ ስለዚህም የዜና ማሰራጫዎች ሁሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሲያወድሱ ኢትዮጵያም አፍሪካም አብረው ይወደሱ ነበር፤ አሁን ግን አንገቱን ስለደፋው ሰው ሲናገሩ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እያሉ ነው፤ ያኔ እኛም አንገታችንን ባንደፋም ወደግብዣው ቋጥረነው የገባነው ትንሽ ክብር ይደፋብንና ውርደቱ ይሰማናል፤ የሚገዙትን ሕዝብ ሳያከብሩ ማስክበር ያስቸግራል፤ የሚገዙትን ሕዝብ ሳያከብሩ መከበርም ያስቸግራል፤ መሪና ሕዝብ ክብርንና ውርደትን ይወራረሳሉ።
በሃያ ዓመት የመሪነት ቦታ ተቀምጦ አንገቱን ቀና አድርጎ በኩራት የሚወረወርበትን ጉድፍ ሁሉ ለመቀበል የሚችልበትን፣ የሚናገርበት ብቻ ሳይሆን አንገቱን ሳይደፋ ለማዳመጥ የሚችልበትን መድረክ ሳያዘጋጅ በመቅረቱ የደረሰበት ውጤት በዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ አንገት መድፋት ነው።
በስንቱ ነገር ነው አንገታችንን የምንደፋው? በደሀነትና በችጋር፣ በመረጃ ማነቆ፣ በቴሌቪዥን እኛ የምንፈልገውንና የምንመርጠውን ለማየት አንችልም፤ በቴሌቪዥን ፕሮግራም እንኳ አጥፍቶ መጥፋት ሊባል ወደሚችል እልህ ውስጥ ገብተን ከዓለም ጋር ብቻ ሳይሆን ከእውቀት ጥበብ (ከቴክኖሎጂ) ጋር የምንታገል ይመስላል፤ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ እየተባለ መራራ ኮሶ የሚጋቱበት ዘመን አክትሞአል፤ ዓለም በሙሉ ጎረቤት ሆኖአል፤ በአንዱ አገር ውስጥ የሚሆነው ውቅያኖስንና አህጉሮችን አቋርጦ ይሰማል፤ ይታወቃል፤ ከጎረቤቶቻችን ከአፍሪካ አገሮች ጋር በመረጃ ልውውጥ በጣም ዝቅተኛ ነን፤ በቴሌቪዥን ብቻ ሳይሆን በኢንተርኔት አገልግሎት ችግር ፍዳችንን እየበላን ነው።
ለዚህ ነው አንገታችንን የምንደፋው፤ አንገታችንን ስንደፋ ክብራችን ይፈስብንና ገበናችን ይጋለጣል፤ መከባበሩ የሚበጀው ለዚህ ነው።


ጥሩነሽ ዲባባ በኦሎምፒክ የሚያሳትፋትን ሰአት ከአስደናቂ ብቃት ጋር አስመዘገበች


ጥሩነሽ ዲባባ በኦሎምፒክ የሚያሳትፋትን ሰአት ከአስደናቂ ብቃት ጋር አስመዘገበች (ከፍሰሃ ተገኝ)
SHARE THIS
     
TAGS

(ከፍሰሃ ተገኝ –የቀድሞው የኤፍኤም አዲስ ስፖርት አዘጋጅ) ድንቋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አሜሪካ ዩጂን ውስጥ በተካሄደው የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር አንደኛ በመውጣት
አሸንፋ በለንደን ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በርቀቱ የሚወክሉት ሴት አትሌቶች መሀል አንዷ መሆኗን አረጋግጣለች። 5 ሺህ ሜትር ያህል ርቀት እንደሮጠች መሪነቱን የያዘችው ጥሩነሽ ርቀቱን ሮጣ ለመጨረስ 30 ደቂቃ ከ24.39 ሰከንድ የሆነ ጊዜ የወሰደባት ሲሆን ሰአቱም የአመቱ ፈጣን ሆኖ ተመዝግቧል። ኬኒያዊቷ ፍሎረንስ ኪፕላጋት ሁለተኛ ስትወጣ፤ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት በላይነሽ ኦልጅራ የራሷን ምርጥ ሰአት በማስመዝገብና የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የኦሎምፒክ መሳተፊያ አንደኛ ደረጃ ሰአት በሚል ካስቀመጠው 31 ደቂቃ ከ45.00 ሰከንድ በፈጠነ 30 ደቂቃ ከ26.70
ሰከንድ በሆነ ጊዜ በማጥናቀቅ ሶስተኛ ሆና ጨርሳለች። ሌሎቹ ኢትዮጵያዊያን ወርቅነሽ ኪዳኔ (30:50.16) እና አበሩ ከበደ (31፡09.28) ከአንደኛ ደረጃው የማለፊያ ሰአት የፈጠነ ሚኒማ በማስመዝገብ አራተኛና አምስተኛ ደረጃን አግኝተው የጨረሱ ሲሆን በኦሎምፒክ አንድ ሀገር በአንድ የውድድር አይነት ቢበዛ ሶስት አትሌቶችን ብቻ የምታሳትፍ በመሆኑና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ይሄንን የዩጂን ውድድር በለንደን ኦሎምፒክ የሚሳተፉ ሶስት ቋሚ አትሌቶችን ለመምረጥ የማጣሪያ ውድድር አድርጎ እንደሚጠቀምበት በማሳወቁ አንጋፋዋ አትሌት ወርቅነሽ ኪዳኔ ቀሪውን ሶስተኛ ቦታ በመያዝ ወደለንደን ትሄዳለች ተብሎ ይጠበቃል። ባለድሏ ጥሩነሽ ዲባባ ከውድድሩ በኋላ በሰጠችው አስተያየት “ውድድሩ ጥሩ ነበር፤ ብዙም አላስቸገረኝም። ነገር ግን ሩጫው ላይ እንዳለሁ መጠነኛ የሆነ የሆድ ህመም ተሰምቶኝ ነበር። ከምንም በላይ ግን በኦሎምፒክ የምሳተፍ መሆኔን በማረጋገጤ እጅግ በጣም ተደስቻለሁ” ብላለች። በ10 ሺህ እና 5 ሺህ ሜትር ርቀቶች የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ጥሩነሽ ከቤጂንግ ኦሎምፒክ በኋላ በአብዛኛው በጉዳት ምክንያት ከውድድሮች ርቃ የነበረ ቢሆንም፤ በተሳተፈችባቸው ውድድሮች ግን አስደናቂ ብቃትን በማሳየት ማሸነፏ የተለመደ ክስተት ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና የኬኒያ አትሌትክስ ፌዴሬሽንም የዩጂኑን ውድድር በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ሀገሪቷን ለንደን ላይ የሚወክሉ አትሌቶችን ለመምረጥ እንደማጣሪያ ውድድር የተጠቀመበት ሲሆን ዊልሰን ኪፕሮፕ (27፡01.98)፣ ሞሰስ ማሳይ (27፡02.25) እና ቢታን ካሮኪ (27፡05.50) ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ በማግኘት በአሸናፊነት አጠናቀዋል።

ኪፕሮፕ ከውድድሩ በኋላ በሰጠው አስተያየት “ሩጫው በጣም አስቸጋሪ የነበረ ቢሆንም በደንብ እራሴን አዘጋጅቼ ነበር። እናም በውጤቱ እጅግ በጣም ነው የተደሰትኩት። የወቅቱ የአለም የግማሽ ማራቶን ሻምፒዮን ከመሆኔ በተጨማሪ ሀገሬ ኬኒያን በኦሎምፒክ ለመወከል መቻሌ በህይወቴ የፈጸምኩት ልዩ ተግባር ነው” ብሏል።
                         ጥሩነሽ ዲባባ በኦሎምፒክ የሚያሳትፋትን ሰአት ከአስደናቂ ብቃት ጋር አስመዘገበች (ከፍሰሃ ተገኝ)            www.maledatimes.com