"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Sunday 3 June 2012

ጥሩነሽ ዲባባ በኦሎምፒክ የሚያሳትፋትን ሰአት ከአስደናቂ ብቃት ጋር አስመዘገበች


ጥሩነሽ ዲባባ በኦሎምፒክ የሚያሳትፋትን ሰአት ከአስደናቂ ብቃት ጋር አስመዘገበች (ከፍሰሃ ተገኝ)
SHARE THIS
     
TAGS

(ከፍሰሃ ተገኝ –የቀድሞው የኤፍኤም አዲስ ስፖርት አዘጋጅ) ድንቋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አሜሪካ ዩጂን ውስጥ በተካሄደው የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር አንደኛ በመውጣት
አሸንፋ በለንደን ኦሎምፒክ ኢትዮጵያን በርቀቱ የሚወክሉት ሴት አትሌቶች መሀል አንዷ መሆኗን አረጋግጣለች። 5 ሺህ ሜትር ያህል ርቀት እንደሮጠች መሪነቱን የያዘችው ጥሩነሽ ርቀቱን ሮጣ ለመጨረስ 30 ደቂቃ ከ24.39 ሰከንድ የሆነ ጊዜ የወሰደባት ሲሆን ሰአቱም የአመቱ ፈጣን ሆኖ ተመዝግቧል። ኬኒያዊቷ ፍሎረንስ ኪፕላጋት ሁለተኛ ስትወጣ፤ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት በላይነሽ ኦልጅራ የራሷን ምርጥ ሰአት በማስመዝገብና የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የኦሎምፒክ መሳተፊያ አንደኛ ደረጃ ሰአት በሚል ካስቀመጠው 31 ደቂቃ ከ45.00 ሰከንድ በፈጠነ 30 ደቂቃ ከ26.70
ሰከንድ በሆነ ጊዜ በማጥናቀቅ ሶስተኛ ሆና ጨርሳለች። ሌሎቹ ኢትዮጵያዊያን ወርቅነሽ ኪዳኔ (30:50.16) እና አበሩ ከበደ (31፡09.28) ከአንደኛ ደረጃው የማለፊያ ሰአት የፈጠነ ሚኒማ በማስመዝገብ አራተኛና አምስተኛ ደረጃን አግኝተው የጨረሱ ሲሆን በኦሎምፒክ አንድ ሀገር በአንድ የውድድር አይነት ቢበዛ ሶስት አትሌቶችን ብቻ የምታሳትፍ በመሆኑና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ይሄንን የዩጂን ውድድር በለንደን ኦሎምፒክ የሚሳተፉ ሶስት ቋሚ አትሌቶችን ለመምረጥ የማጣሪያ ውድድር አድርጎ እንደሚጠቀምበት በማሳወቁ አንጋፋዋ አትሌት ወርቅነሽ ኪዳኔ ቀሪውን ሶስተኛ ቦታ በመያዝ ወደለንደን ትሄዳለች ተብሎ ይጠበቃል። ባለድሏ ጥሩነሽ ዲባባ ከውድድሩ በኋላ በሰጠችው አስተያየት “ውድድሩ ጥሩ ነበር፤ ብዙም አላስቸገረኝም። ነገር ግን ሩጫው ላይ እንዳለሁ መጠነኛ የሆነ የሆድ ህመም ተሰምቶኝ ነበር። ከምንም በላይ ግን በኦሎምፒክ የምሳተፍ መሆኔን በማረጋገጤ እጅግ በጣም ተደስቻለሁ” ብላለች። በ10 ሺህ እና 5 ሺህ ሜትር ርቀቶች የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ጥሩነሽ ከቤጂንግ ኦሎምፒክ በኋላ በአብዛኛው በጉዳት ምክንያት ከውድድሮች ርቃ የነበረ ቢሆንም፤ በተሳተፈችባቸው ውድድሮች ግን አስደናቂ ብቃትን በማሳየት ማሸነፏ የተለመደ ክስተት ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና የኬኒያ አትሌትክስ ፌዴሬሽንም የዩጂኑን ውድድር በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ሀገሪቷን ለንደን ላይ የሚወክሉ አትሌቶችን ለመምረጥ እንደማጣሪያ ውድድር የተጠቀመበት ሲሆን ዊልሰን ኪፕሮፕ (27፡01.98)፣ ሞሰስ ማሳይ (27፡02.25) እና ቢታን ካሮኪ (27፡05.50) ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ በማግኘት በአሸናፊነት አጠናቀዋል።

ኪፕሮፕ ከውድድሩ በኋላ በሰጠው አስተያየት “ሩጫው በጣም አስቸጋሪ የነበረ ቢሆንም በደንብ እራሴን አዘጋጅቼ ነበር። እናም በውጤቱ እጅግ በጣም ነው የተደሰትኩት። የወቅቱ የአለም የግማሽ ማራቶን ሻምፒዮን ከመሆኔ በተጨማሪ ሀገሬ ኬኒያን በኦሎምፒክ ለመወከል መቻሌ በህይወቴ የፈጸምኩት ልዩ ተግባር ነው” ብሏል።
                         ጥሩነሽ ዲባባ በኦሎምፒክ የሚያሳትፋትን ሰአት ከአስደናቂ ብቃት ጋር አስመዘገበች (ከፍሰሃ ተገኝ)            www.maledatimes.com

No comments:

Post a Comment