"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Sunday, 3 June 2012

በAውራምባ ታይምስ የተቆረጠው የታማኝ ቃለ-መጠይቅ


በAውራምባ ታይምስ የተቆረጠው የታማኝ ቃለ-መጠይቅ
Aርቲስት ታማኝ በየነ ከAውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ጋር የቃለ-ምልልስ  Eንዲያደርግ ከAዘጋጁየ ቀረበለትን
ጥያቄ ተቀብሎ ቃለ-ምልልስ  Aድርጎ ነበር፡፡ ቃለ-ምልልሱ በጋዜጣው ታትሞ ከወጣ በኋላ ግን: ለጋዜጣው
Aዘጋጅ በላከው ደብዳቤ "ቃለ ምልልሱን Aነበብኩት፡፡ ስሜንና ፎቶግረፌን ከመያዙ በቀር የኔ ሀሳብ የምለው
Aንድም በውስጡ ባለመኖሩ በጣም  Aዝኛለሁ፡፡"  ሲል ቅሬታውን ገልጿል፡፡ የAውራምባ ታይምስ  Aዘጋጅ
ቃለ-ምልልሱን  Eንዳለ ቢያወጣው በህይወቱ ላይ  Aደጋ ሊያስከትልበት  Eንደሚችል ገልጾ ሙሉውን
ባለማተሙ ይቅርታ ጠይቋል፡፡   ለAንባቢያን ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ ሙሉውን ቃለ-ምልልስ  Eንደሚከተለው
Aውጥተነዋል፡፡
ከAውራምባ ታይምስ:- Eንግዲህ በAሁኑ ሰዓት ለAገር ለወገን ትልቅ ስራ ሰርተው ያለፉ ታላላቅ
Iትዮጵያወገኖችን በማስታወስ ብዙ  Eንቅስቃሴዎችን በማከናወን ላይ  Eንደምትገኝ ይታወቃል፡፡  Eስኪ
ለAገር ውስጥ Aንባቢ ጠቅለል Aድርገህ ብትገልጽልኝ?

ታማኝ:-  Eንደ ትውልድ ብዙ  Eዳ  Aለብኝ ብየ  Aስባለሁ ስለዚህ ከEዚህ በፊት በተለያየ ሙያ ሀገራቸውን
ያገለገሉ  Iትዮጵያዊያንን ከተለያዩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር በመሆን  Eውቅና Eንሰጣለን
Eናመሰግናቸዋለን በዚህ መሰረት የኪነጥበቡን ሙያ ብንወስድ ትናንት ጋብቻ ከልክል የነበረ ሙያ ነው
በዚያ ዘመን የነበሩ ሙያተኞች ተዋርደው ተንቀው ግን ጥርሳቸውን ነክሰው ፀንተው ታግለው በከፈሉት
ህይወት ነው የዛሬው ትውልድ ባለሙያዎች በመላው  Aለም  Eየተዘዋወሩ ስራቸውን ሲያቀርቡ ሽህ ህዝብ
ተሰልፎ የሚያያቸው ስለዚህ ባለችን Aቅምና ትርፍ ጊዜ ይህን ውለታ ለዋሉልን Eንደነ ጋሽ ፀጋየ ገ/መድህን
ታላቁ ጥላሁን ገሠሠ ጋሽ ተስፋየ ለማ Aለባቸው ተካ ለሌሎቹም ምስጋና Aቅርበናል Eውቅና ሰተናል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ መቸም በዓለም ላይ መለኪያ የሌለው ስጦታ ህይወት ነው ሀገራችን ፈተና ውስጥ
ስትወድቅ መተኪያ የሌላትን ህይወታቸውን ለመስጠት በግምባር የዘመቱ የIትዮጵያ ወታደሮች የደርግ
ወታደር ተብለው ተበትነው ለማኝ  Eንዲሆኑ ተደርጓልይሄን  Eዚሁ ላይ ልተወው ምክኒያቱም በዚህ ዙሪያ
የተቋቋመው ኮሚቴ ከፖለቲካ ነፃ ስለሆነ የEኔ የግል ሃሳብ የኮሚቴውም ተደርጎ  Eንዳይወሰድ ስለምፈራ
ነው፡፡ ለማንኛውም በ1969  ሶማሊያ ሀገራችንን በወረረችበት ወቅት የIትዮጵያ  Aየር ሃይል ያስመዘገበው
ድል በታሪክ የተመዘገበ ነው ከያኔወቹ ጀግኖች  Aንዱ ብ/ጄኔራል ለገሰ ተፈራ ነው ይህ ጀግና 5 የሶማሊያን
Aውሮፕላን የጣለና በሶማሊያ ሜካናይዝድ ጦር ላይ ከፍተኛ ጉዳት  Aድርሶ በመጨረሻ  Aውሮፕላኑ ተመታ
ስትወድቅ በጠላት  Eጅ ወድቆ ለ11 Aመት ከመሬት በታች ጨለማ ውስጥ ታስሮ ከቆየ በኋላ በAለማቀፍ
ቀይ መስቀልና በወቅቱ በነበረው የIትዮጵያ መንግስት Eርዳታ ከEስር ተፈቶ በወቅቱ የሀገሩቱን የመጨረሻ
ነው የተባለውን ሜዳሊያ ተሸልሟል ፡ታዲያ ይህንን ጀግና ነው በስደት Eንዳልባሌ Eቃ ተጥሎ ያገኘነው ይህ
የEኛ ኮሚቴ የጀግና ምሽት  Aዘጋጅቶ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ  Iትዮጵያዊያን በተገኙበት የክብር
ሽልማት ሸልሞ ለሀገራችን ላደረከው በሙሉ  Eናመሰግንሀለን ብሎታል በዘንድሮው  Aመት ደግሞ ሌሎች
ጀግኖችን  Aፈላልገን ማለትም በሸህ1969  ዓም ናቅፋ ላይ በሻቢያ ተከቦ የሚገኘውን የ15ኛ ሻለቃ ጦርን
ለማስለቀቅ የAየር ወለድን ጦር ይዘው ካለማቀፍ ህግ ውጭ ከ2000 ጫማ ከፍታ ላይ በመዝለል ከ15ኛ
ሻለቃ ጋር በመገናኘት ለስድስት ወር ከተዋጉ በኋላ የሻቢያን ከበባ በመስበር ከወገን ጦር ጋር ለመቀላቀል
በመብቃታቸው በወቅቱ የሃገሪቱን የመጨረሻ የተባለውን ሜዳሊያ ለመሸለም የበቁትን ብ/ጄኔራል ተስፋየ
ኃ/ማርያምን  Eንዲሁም ገና ትምህርታቸውን ከAሜሪካን ሀገር ጨርሰው  Eንደተመለሱ ወደ ምስራቅ
Iትዮጵያ ዘመቱ ከዚያም በድል ወደ ኤርትራ  Aቀኑ  Eስከ 1981  ድረስ ያልተሳተፉበት የውጊያ ግንባር
የለም ለሀገራቸው ላደረጉትም ውለታ በጊዜው የሁለተኛ ደረጃ የላቀ የጦር ሜዳ ሜዳሊያ የተሸለሙትን
ብ/ጄኔራል ካሳየ ጨመዳን  Eንዲሁም በሶማሊያ ውጊያ በሚሊሻነት ዘምቶ  Aንድ ታጣፊ ክላሽንና ቦምብ ይዞ
ገብቶ ሶስት ታንኮችን ያቃጠለ ሁለት የሶማሊያ Aዋጊ መኮንኖችን የደመሰሰ በዚሁ ጀግንነቱ የጀግና ሜዳሊያ
የተሸለመውንና በAኑ ስዓት በAዲስ  Aበባ በኩሊነት የሚተዳደረውን ሚሊሻ  Aሊ በርኬን መርጠን ሁለቱ
ጄኔራሎች  Eዚሁ  Aሜሪካ ድረስ መተው ሽልማታቸውን ተቀብለዋል ሚሊሻ  Aሊ በርኬ ግን  Aድራሻው
በጊዜው ባለመገኘቱ ሊመጣ Aልቻለም ነበር ዝግጅቱ ከተኪያሄደ በኋላ ግን Aቶ ቅዱስ ሀብት በላቸው የተባሉ
Iትዮጵያዊ ከAውስትራሊያ  Aድራሻውን ስላገኙልን ሽልማቱን  Iትዮጵያ ድረስ ልከንለት ተረክቧል፡፡
የጄኔራል ደምሴ ቡልቶን በተመለከተ ደግሞ ልጃቸው የAባቱን ታሪክ በመፅሀፍ ሲያቀርብ ታሪኩ ልቤን
ስለነካው በመፅሀፉ ምረቃ Eለት የጄኔራሉን Aጭር የህይወት ታሪክ በፊልም Aቀናብሬ Aቅርቢያለሁ፡፡Eንዲህ
Eንዲህ Eያልኩ ድርሻየን ለመወጣት Eሞክራለሁ፡፡2
ከAውራምባ ታይምስ:- ብዙ  Iትዮጵያዊያን ለህግ የበላይነት፣ለሰብAዊ መብት መከበርና ለዴሞክራሲ መስፈን
Eየታገሉ፤የተለያየ ጥያቄ ሲቀርባላቸው ደግሞ ፖለቲከኛ  Aይደለሁም ሲሉ ይደመጣሉ?  በAንተ  Eምነት
Aንድ ሰው ፖለቲከኛ የሚያሰኘው ምንድነው? ፖለቲከኛ ነኝ ብለህስ ታስባለህ?
ታማኝ:- ጥልቅና ከባድ ጥያቄ ነው ፡፡ስለፖለቲከኛነት  Eኔ  Eንደሚመስለኝ ከምናገር በዚህ ዙሪያ ጥናትና
ምርምር ያደረጉ ሰዎች ቢናገሩ ደስ ይለኝ ነበር፡፡የሚሰማኝን ለመግለፅ ያህል በIትዮጵያ ውስጥ ፖለቲከኛ
መሆን ዘጠና በመቶ  Aደጋ  Aለው ብየ  Aምናለሁ፡፡ ወደ ኋላ መለስ ብለን  Eንኳን ብንመለከት  Aፄ ኃ/ሥላሴ
ወደ ስልጣን ሲመጡ ተቀናቃኛቸው የነበሩት ልጅ  Eያሱ  Eንኳን የት  Eንደ ደረሱ  Eስከ ዛሬ ድረስ
Aናውቅም፡ስለዚህ ወደ ፖለቲካ ስትመጣ ወይ ስልጣን ትይዛለህ ያለበለዚያ ትጠፋለህ፡፡መለስ ብለን  Aበበ
Aረጋይን Eንመልከት ፋሽሽት Iጣሊያ Iትዮጵያን በተቆጣተረበት ጊዜ በAዲስ Aበባ ዙሪያ Aፍንጫው ስር
ሆነው  Aምስት ዓመት የታገሉ  Aርበኛ ናቸው በ1953  በተደረገው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ
ቤተመንግስት ውስጥ የተረሸኑት፡፡
ሌላውን ታላቅ  Iትዮጵያዊ  Aክሊሉ ኃብተወልድን ብንወስድ በዲፕሎማሲ ትግል ኤርትራን ወደ  Iትዮጵያ
Eንድትመለስ ያደረጉ ከልጅነታቸው ጀምሮ ሀገራቸውን በቅንነት ያገለገሉ  Iትዮጵያዊ የAስር ደቂቃ የኑዛዜ
Eድል Eንኳ ሳይሰጣቸው ነው የተረሸኑት፡፡
ከAውራምባ ታይምስ:- የደርግና IህAዴግንም Aያይዘህ ብትገልፅልኝ
ታማኝ:- ደርግማ ከAርበኝነት ጀመሮ  Eስከ ዲፕሎማሲ ዘመናዊት  Iትዮጵያ  Eንድትፈጠር  Eድሚያቸውን
ሙሉ ያገለገሉ 60 Iትዮጵያዊያንን በመረሸን ስልጣኑን ጀምሮ በAራቱም ማEዘን ሀገራቸውን ከጠላት
ሲከላከሉ የኖሩትን ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በመረሸን ነው የስልጣን ዘመኑን ያጠናቀቀው የIህAዴግ ግን
በዘዴው ለየት ይላል  Eንደነ ሙሉዓም  (የAዲስ  Aበበ ከንቲባ የነበረው)  በድንገተኛ  Aደጋ ሞተ ትባላለህ
ወይም የቁም ሞት ትሞታለህ፡፡ ለምሳሌ Aቶ ታምራት ላይኔን ብትወስድ 17 ዓመት Aብረው ታግለው መጡ
በተከበሩበት ፓርላማ ውስጥ ወስደው ብመከር ብመከር  Aልሰማ ብየ ነው Aስብለው ለቀቋቸው ከልጅነታቸው
ጀምረው  Aብረዋቸው የታገሉትን  Aቶ ሰየ  Aብርሃን መላ ቤተሰባቸውን ሰብስበው  Aሰሯቸው  Eንግዲህ
Eነዚህንና ሌሎችንም ያየ ትውልድ ፖለቲካን ቢፈራ Aትፈርድም፡፡ ነፃ Eርምጃ ቀይ ሽብር የሚሉት ቃላቶች
በራሳቸው  Eንዴት ያስፈራሉ መሰለህ ከዚህ በመነሳት ፖለቲከኛ ከመባል የሚመጣውን ውጤት በመፍራት
ይመስለኛል  Eኔ ፖለቲከኛ  Aይደለሁም የምንለው፡፡ ለEኔ ፖለቲካ ማለት በጋራ በምንኖርበት ሀገር ውስጥ
Eኩል  Eንድንሆን የምናሰፋውን ልብስ ዲዛይን የምናደርግበት ነው፡፡  Aሁንም  Eኔን ብትጠይቀኝ ፖለቲከኛ
Aይደለሁም ነው የምልህ በፖለቲካ ውድድር ገብቸ ስልጣን ለመያዝ ፍላጎት ስለሌለኝና ከፖለቲካው ይልቅ
ኪነጥበብን የበለጠ ስለምወድ ነው፡፡ በፈራን ቁጥር ግን ነፃነታችንን Eያጣን ነው የምንሄደው ስለዚህ የግድያን
Aዙሪት ለማቆም የፍህርሀትን ቀንበር ለመስበር Aንድ ጌዜ Aምርረን Eንታገል ከፖለቲካ Aንሽሽ፡፡
ከAውራምባ ታይምስ:- ከAንድ Aመት በፊት በሰጠኸኝ ቃለምልልስ "በስልጣን ላይ ያለው Aካል ወደ ልቦናው
Eንዲመለስ ዝቅ ብዬ Eመክራለሁ" ብለህ ነበር፡፡ ምክርህ ተቀባይነት Aግኝቷል?
ታማኝ:-  Eኔ  Eንደ  Aንድ ዜጋ ቅን ነው ብየ ያሰብኩትን  Aቅርቤለሁ፡፡ ከEኔ በተሻለ ደግሞ የፖለቲካ
ድርጅቶች ላለፉት 18  ዓመታት ብሄራዊ  Eርቅ ፡ጥምር መንግስት፡ የሽግግር መንግስት ሌላም ሌላም
ተብሏል::ከመንግስት በኩል ግን  Aንድም ይሄን ጉዳይ በቅንነት ማየት የፈለገ የለም ፡፡Eኔ የማዝነው ግን
ከትናንት ይቅር ከዛሬ Eንኳን ለመማር ለምን Eንደማይፈልጉ ነው;ምን Aይነት የተረገመ ወንበር ነው
ኮሎኔል መንግስቱ  Eንኳን ይሄን ጦርነት በጦርነት ብቻ ማሽነፍ ያስቸግራል ድርድር ይሞከር ብለው የጦር
Aዛዦቻቸው ሲያማክሩዋቸው ሀገሪቱዋን ለወንበዴ ልትሸጡ ነው ብለው ሁሉንም ረሽነው በመጨረሻ ሀገሪቷን
ለEነዚሁ ወንበዴ ላሉዋቸው Aስረክበው ሄዱ፡፡ ብሄራዊ Eርቅ Eኮ ቀላል ነገር Aይደለም ለልጆቻችን የሰከነና
የተረጋጋ ሀገር መስጠት ማለት ነው፡፡መቸም  Eነ  Aቶ መለስ ከህውሃት ከIህAዴግም በላይ ልጆቻቸውን
የሚወዱ ይመስለኛል፡፡በEርግጥ ልጆች በAባቶቻቸው ሀጢያት ተጠያቂ  Aይደሉም ፡፡  Aንዳንድ የቀድሞ
የደርግ ባለስልጣን ልጆች ሰው  Eንዳያውቃቸው ሲሳቀቁ  Aይቻለሁ፡፡የEነሱ ልጆች ላለመባል ሲደበቁ
ነበር፡፡Aንድ ምሳሌ ላንሳ የAቶ Aሰፋ ማሩ የIትዮጵያ መምህራን ማህበርና የIሰመጉ Aባል የነበረ በጠራራ
ፅሀይ Aዲስ Aበባ ላይ ተረሽኗል ታዲያ የAሰፋ ልጆች ስለ Aቶ መለስ ልጆች ምን ስሜት ይኖራቸዋል3
የወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ልጅ ስንት  Aመት ሙሉ ስታለቅስ ስታድግ ስለ  Aቶ መለስ ልጅ ምን  Aይነት
ስሜት ይኖራታል የጋዜጠኛ የሰርካለምና የጋዜጠኛ Eስክንድር ልጅ ስታድግ የት ተወለድሽ ሲሉዋት Eድሜ
ለነ Aቶ መለስ Eስር ቤት ነው የተወለድኩት ትላለች፡፡Eንዴት በ18 Aመት ውስጥ መስከን ያቅታል፡Aሁንም
Eልህ ንዴት ፡Eንደ ገና ከሰሙኝ ስለ ልጆቻችሁ ስትሉ ስከኑ ስከኑ ስከኑ Eላለሁ
ከAውራምባ ታይምስ:- ምርጫ 97 ተከትሎ በEስር የተዳረጉ ወገኖችን ስላሸማገሉት ወገኖች ያለህ  Aስተያት
ምንድን ነው?
ታማኝ:- በEውነቱ መሰረታዊ የሆነ ጥያቄ ነው ያነሳሀው ፡፡Eንዲያውም ለዚህ ሁሉ መከራችን  Aንዱ
ምክኒያት ይሄው ይመስለኛል፡፡በIትዮጵ ውስጥ ሽማግሌዎች ትልቅ ቦታ ነበራቸው፡፡ሽማግሌ የመስማት
Eሴት ነበረን፡Aሁን  Eኮ በሞራል ሁሉ ሞተናል፡፡የሃይማኖት  Aባቶች ይህን  Aለም የናቁ በክርስትና  Eምነት
ደግሞ ሞትም ህይዎትም  Eየሱስ ብቻ ነው ብለው የሚያምኑ ነበሩ፡Aሁን  Eኮ በሀገር ላይ ይሄ ሁሉ ግፍ
ሲፈፀም Eያዩ ምንም Eንዳልተደረገ የሚሰብኩ Eንዲያውም ጳጳሶቹ ተጣልተው ፖለቲከኞቹ የሚያስታርቋቸው
ጊዜ ላይ ደረስን ፡፡የምርጫ 97  ግድያ  Eንዲያጣራ ከተመረጡት የሃይማኖት  Aባቶች  Aንዱ የሙስሊሙ
ተወካይ Eኮ መንግስት የወሰደው Eርምጃ ተገቢ ነው ብለው ነው ድምፅ የሰጡት፡፡ ክርስቲያን ስትሆን ስጋህን
ንቀህ ለዚያኛው  Aለም ማሰብ ሲገባህ ጥይት በማይበሳው መኪና የሚሄዱ በወርቅ ጫማ የሚዋቡ  Aባት
Aገኘን፡፡ በየAለሙ ስንዴ  Eየለመን  Eየበላን ባለ ወርቅ ጫማ  Aባት  Aሉን ስንል  Aናፍርም ከዚህ በላይ
መሞት Aለ፡፡
በምርጫ 97  የታሰሩትን የቅንጅት  Aመራሮችንና ጋዜጠኞችን ለማስፈታት በሽምግልና ተሳተፍን ያሉትን
ሰዎች  Eዚህ ዋሥግጸን መተው ፕሮፌሰር ኤፍሬምንና ፓስተር ዳንኤልን ቁጭ ብየ  Aነጋግሪያቸዋለሁ፡፡Eኔ
የAይንም የጆሮም ምስክር ነኝ፡፡ በወቅቱ  Eንዴት  Aልቅሰውና ተንበርክከው የቅንጅት መሪዎችን  Eንደለመኑ
Eያለቀሱ የነገሩኝ ሰዎች ዛሬ ብርቱካን በግፍ ታስራ  Aንድ  Aመት ሲሞላት  Eንኳ ወተው  Eውነቱን  Eንኳን
ለመናገር  Aለመቻላቸው፡ የIትዮጵያ ጀግና ብየ በህዝብ ፊት  Eግሩን የሳምኩት ሀይሌ ገ/ስላሴም ዝም ሲል
በሀይማኖትም በሞራልም የደረሰብንን ኪሳራ ያሳያል፡፡ይሄ ትውልድ  Eንዴት  Aንድ የሚያምነውና
የሚከተለው AርAያ ሰው ያጣል በጣም Aዝናለሁ፡፡
ከAውራምባ ታይምስ:- AህAዴግን ግለጸው ብትባል ከ1983  ዓ.ም ጀምሮ በስንት ምEራፍ ከፋፍለህ
ትገልጸዋለህ?
ታማኝ:- IህAዴግ የተለያየ ማሊያ ይለብሳል Eንጅ የሚጫወተው ያው ለAንድ ቡድን ነው፡፡ Eኔ ምን ያህል
Eንደሚፈቀድላችሁና ምን ያህሉን  Eንደምታወጡት  Aላውቅም፡፡ የ1983 IህAዴግ በጣም የተለየ ነው፡፡
በሦስት Eንኳን ከፍለን Eንይው ብንል:
ከ1983-Iትዮ ኤርትራ ጦርነት ያለው IህAዴግ
በፀረ Iትዮጵያዊነት የሰከረ IህAዴግ ነበር
የIትዮጵያ የሆነውን ሁሉ ጠልቶ፡
• ለ50 Aመት የተገነባውን የIትዮጵያን የመከላከያ ሀይል Aፈረሰ
• Iትዮጵያ በህጋዊ መንገድ የምታገኘውን ወደቧን Aስረክቦ ከባህር Aገለላት
• Eነ  Aቶ  Iሳያስን ያስደስታል ያለውን ሁሉ  Aደረገ፡፡ ኤርትራ በAፍሪካ ትልቋ ቡና ላኪ ሀገር
Eስክትባል ድረስ  Eነ  Aቶ  Iሳያስ በIትዮጵያ ውስጥ  Eንዳሻቸው ሆኑ፡፡ ይባስ ብለው  Aዲስ  Aበባ
ውስጥ የራሳቸው Eስር ቤት ከፍተው የፈለጉትን Eስከማሰር ድረስ ፈቀደ፡፡
• ያለፉት የIትዮጵያ መንግስታት ለብሄራዊ ደህንነት ሲሉ ያደረጉትን ብርቱ ሚስጥር ሳይቀር
በማውጣት ለሶማሊያ መፍረስ ተጣያቂ Iትዮጵያ ናት ብለው ዶክመንቱን በመፅሄት ሳይቀር Aትሞ
Aወጣ፡፡
ከኤርትራ ጋር ያለን ፍችም ቢሆን በAግባቡ ይሁን ያሉትን ፕሮፌሰር  Aስራትን  Eንዳይፈቱ  Aድርጎ
Aሰራቸው፡፡4
በኤርትራ ውጊያ የተሳተፉ የAየር ሃይል Aባሎች Eየተለቀሙ ታሰሩ Aራት የAማራ ሽማግሌዎች ተመርጠው
የAማራው መንግስት ላደረሰው በደል ሻቢያን ይቅርታ  Eንዲጠይቁ በIህዴን ተመርጠው ወደ  Aስመራ
ተልከው በAቶ Iሳያስ Eግር ስር Eንዲወድቁ Aደረገ፡፡
የክሱም ሀውልት ለወላይታው ምኑ ነው ያሉትን ጠ/ሚንስትር መለስን ተከትለው የ  Oህዴድ  Aቶ ሱሌማን
ደደፎ ለEኔ ያልሆነች  Iትዮጵያ ሽህ ቦታ ትበጣተስ ሲሉ የEህዴን  Aቶ ዳዊት ዮኃንስ ደግሞ  Iትዮጵያ
በታሪኳ ጦርነት Aሸንፋ Aታውቅም Aሉ፡፡
በዚህ መልክ ነው የ1983ቱ  IህAዴግ በIትዮጵያዊነት ላይ የዘመተው ከዚያ በኋላ ያለው  IህAዴግ ደግሞ
የኤርትራ ጦርነት ሲነሳ ተቀየረ ብለን ነበር፡፡በነገራችን ላይ IህAዴግ ከIትዮፕያ ህዝብ ጋር ሊታረቅበትና
Aገሪቷን ወደ ተሸለ ቅጣጫ የሚወስድበት ትልቅ  Eድል ገጥሞት ነበር ነገር ግን በEልህ በንዴትና ትEቢት
Eድሉን የሚያበላሽድርጅት ነው፡፡ ያን ያህል Iትዮጵያዊ ባድመ ድረስ ሄዶ የወደቀለት ጉዳይ በምን መልኩ
Eንደ ተጠናቀቀ Eኛም ታሪክም መዝግበናል፡፡Aሁን ወ/ት ብርቱካንን ይቅርታ ጠይቃ  Aልጠየኩም ብላለችና
ቃሏን ቀየረች ብለው  Eድሜ ልክ ብለው ሲያስሯት ይገርመኛል ምክኒያቱም ያኔ ባድሜ ለEኛ ተወስኗልና
ውጡና ጨፍሩ ያሉት  Aቶ ስዩም መስፍን በዚህ  Aይነት ስንት  Aመት ሊፈረድባቸው ነው; Aቶ መለስም
በ1983 ዓ/ም የሽግግር መንግስት ሲቋቋም በጉባኤው መዝጊያ ላይ ያሉትን ልጥቀስ ከAሁን በኋላ የIትዮጵያ
ወጣት የሚረግፍበት የኤርትራ ጦርነት ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ዘግተነዋል የIትዮጵያና የኤርትራ  Eናቶች
ሀዘናችሁን  Eየተካፈልን በሌላ በኩል ግን ብስራት ነጋሪ ሆነናል ከEንግዲህ ጦርነት  Aይኖርም ነበር ያሉት
፡፡ከዚህ  Aዋጅ በኋላ ባድሜ ላይ ያ ሁሉ  Iትዮጵያዊ ተሰዋ፡ታዲያ  Aቶ መለስ ባላከበሩት ቃላቸው ስንት
Aመት ይፈረድባቸው፡፡
ሦስተኛው ደግሞ ከ1997 በኋላ ያለው IህAዴግ ነው:
ከ1997 በኋላ ያለው  IህAዴግ የቆሰለ  Aውሬ ነው ድንጉጥ ተጠራታሪና ፈሪ ነው የጉዳዩ ባለቤትና የAይን
ምስክር የሆነው የ  Iትዮጵያ ህዝብ  Eያለ  Eኔ ከዚህ  Eንደዚህ ሆነ  Eንደዚያ  Aልልም ግን  Aንዳንዶቹን
ለማስታወስ የሚችለውን ገደለ Eስርቤት ጠቦ የጦር ካምፖች Eስርቤት Eስኪሆኑ ድረስ ወጣቱን በሙሉ Aሰረ
የህዝቡ ብቸኛ መተንፈሻ የነበሩትን ጋዜጠኞች በሙሉ  Aሰረ ያመለጡ ተሰደዱ በመላው  Aለም ያሉትን
ያሙኛል Aይወዱኝም ያላቸውን በሙሉ በዘር ማጥፋትና በሀገር ክህደት ከሰሰ
-ትልልቆቹን ፖለቲከኞች Eያስፈረመ የኔ ቢጤውን ደግሞ ቪድዮና ፎቶ Eያነሳ ዋ ሁለተኛ Eያለ ፈታቸው
የሰራዊቱን የደህንነቱንና የፖሊስ ቁልፍ ቦታወችን በሚያምናቸው ሰዎች  Aጠናከረ የስልጣን  Eድሜውን
ለማራዘም መግደል ብቻውን Eንደማያዋጣ ሲያውቅ ከጠመንጃ ቀጥሎ ፍርድቤት ነው ብሎ ወሰነ
ልክ ንፁሃንን ተኩሰው Eንደሚገድሉ ወታደሮች ንፁሃንን በህግ መሳይ ጥይት ለመግደል የሚችሉ የህግ ሙያ
የተማሩ ሰዎችን  Aሰማርተው  Aዲስ ግድያ ጀመሩ የሚያሳዝነው  Eነዚህ በህግ ስም የሞት ፍርድ የሚያረቁ
የሚፈርዱ  Aቃቢ ህግ ነን ብለው የሚቆሙ  Eንዴት  Eንደሚተኙና ለልጆቻቸው የሚተውትን የስም  Eዳ
Eንዴት  Eንደማያስቡ ይገርመኛል ፡፡ በተለይ የAማራ ክልል የOሮሞ ክልል የደቡብ ክልል የሌላም ክልል
ፕሬዝዳንቶች  Eየተባሉ የተቀመጡ ሰወች የAቶ መለስ የፖለቲካ ዝናብና ፀሀይ መከላከያ ጃንጥላ  Eንጅ
መለስን የሚከራከሩ  Aይደሉም ስለዚህ የሀገሪቱ  Eጣ ባንድ ሰው  Eጅ ወድቋል  IህAዴግም ጥሩ መንገድ
Eየሄደ Aይደለም ታሪክ ደግሞ ይህንንም Eየመዘገበ ነው፡፡
ከAውራምባ ታይምስ:- መገለጽ Aለባቸው የምትላቸው ተጨማሪ ነገሮች ካሉ Eድሉን ሰጥቼሃለሁ
ብዙዎቹን የዳሰስናቸው ይመስለኛል፡ ለማጠቃለያ ግን  Eንደሚወራው ማለትም  Eንደ  Aስፋልቱ መስፋት
Eንደ ህንፃው መገንባት  Eንደ  Iኮኖሚው ማደግ  Aይመስለኝም ያለብን ችግር፡፡ ያለብን ችግር ከዚያ በላይ
ነው ብየ Aስባለሁ፡፡ ስለሆነም ችግሩን Aውቀን የምንነጋገርበት መድረክ ፈጥረን Aሁኑኑ Eልባት ካላበጀንለት
Eየኖርን ያለነው በህመም ማስታገሻ ይመስለኛል፡ካንሰር ሊሆን የሚችል በውስጣችን  Eያለ ማስታገሻ
Eየወሰድን መኖር በሽታውን  Eያባበልን ለትልቅ ውድቀት የምንዳረግበት ችግር ያለ ይመስለኛል፡፡ ይሄ
የብሄር ብሄረሰቦች መብት ተብሎ የሚነገረን ነገር በEውነታው የሌለ ስለሆነ ለበለጠ መራራቅና ላዩነት
Eየዳረገን ነው ስለዚህ በጉዳዩ ላይ በግልፅ ብንነጋገር ደስ ይለኛል፡፡ ወደ ኋላ ተመልሸ በሽግግር መንግስቱ
የሰኔ ጉባኤ ላይ የAቶ መለስን ንግግር ልጥቀስ  Aምባ ገነኖች በሰላም  Eምቢ ያሉንን መብታችንን በሀይል
Aንበርክከናቸው ዲሞክራሲን ከዋናዋ ባለቤቶች ጋር  Eንዴት  Eንዳገናኘናት Eኛም  Eነሱም በህይወት Eያለን5
Aሳይተናቸዋል፡፡ ነበር ያሉት ታዲያ ዛሬ መብታችንን ተገፏል ያሉ  Iትዮጵያዊያን ለመብታቸው ሲታገሉ
ሽብርተኛ የሚባሉት በምን ሂሳብ ነው፡፡ በቅርቡ ራሱ መንግስት ባወጣው መግለጫ በሰራዊቱ ውስጥ የነበሩ
ጄኔራሎች የመንግስት ግልበጣ ለማድረግ ሞክረው ተያዙ ብሎናል ፡፡ዲመፐክራሲ ባለበት ሀገር ግልበጣን
ምን  Aመጣው ችግር  Aለ ማለት ነው፡፡በተባበሩት መንግስታት የሰብAዊ ጉባኤ ላይ የAሜሪካው ዲፕሎማት
ሲናገሩ በIትዮጵያ ያለው ከፍተኛ የመንግስት ስልጣኖች በAንድ ብሄረሰብ የተያዙ ናቸው ብለዋል ይሄ ጥሩ
ምልክት Aይደለም ፡፡Aሁን መንግስት ለመገልበጥ ተብለው ከተያዙትና Eድሜ ልክ የተፈረደባቸው የሰራዊቱ
Aባላት የነበሩት የAንድ ብሄረሰብ  Aባላት ናቸው፡፡Eንዴት የAንድ ብሄረሰብ  Aባላት  Aንድ  Aይነት ሀሳብ
ያስባሉ ችግር  Aለ ማለት ነው፡፡ ይሄ ደግሞ በሌሎች የብሄረሰቡ  Aባሎች ልብ ውስጥ ጥሩ ስሜት
Aይፈጥርም፡Oነግ  Eየተባሉ የሚታሰሩ የOሮሞ ልጆች ጉዳይ በሌሎች  Oሮሞዎች ልብ ውስጥ ጥሩ ነገር
ይፈጥራልን፡በሌላው በሌላውም ወገን  Eየተካሄደ ያለውስ በጋምቤላው በOጋዴኑ የተካሄደውስ  Aብሮ
የሚያኗኑረን ነውን በጅማ የታየው የሀይማኖት ግጭት ችግሩን ከመሰረቱ ነቅለነዋል ወይስ የህመም ማስታገሻ
ወስደን  Aልፈነዋል፡፡የደበቅናቸውና ያፈናቸው ትላልቅ ችግሮች በውስጣችን  Aሉ ሰብረን ወጥተን
ካልተነጋገርን  Eንጠፋለን፡፡ በዘር ጉዳይ የሚነሳ ነገር ከመተላለቅ በስተቀር  Aሸናፊ  Aይኖረውም፡፡ ስለዚህ
Eያንዳንዱ  Iትዮጵያዊ በዚህ ጉዳይ ላይ  Eንዲነጋገር  Eለምናለሁ፡፡ለዚህ ሁሉ ችግር መፍትሄው ደግሞ
Aንድ ብቻ ነው ስለዚህ  Iትዮጵያ  Eኩል የሁላችን  Eንድትሆን ሁላችንም ወደ ትግሉ
Eንቀላቀል፡፡ነፃነታችንን ከራሳችን በቀር ማንም Aይሰጠንም፡፡

No comments:

Post a Comment