Sunday, June 3rd, 2012 | Posted by zehabesha
በአበበ ገላው ዙሪያ – የግጥም ጦርነት በኢሕአዴጉና በነጻነት ትግሉ ደጋፊ
(ዘ-ሐበሻ) ጋዜጠኛ አበበ ገላው አቶ መለስ ዜናዊን በአደባባይ ካቀለለና ካስኮረፈ በኋላ በርከት ያሉ ግጥሞች ተጽፈዋል። የኢሕአዴግ ደጋፊዎች እንደተበሳጩ፤ የነጻነት ትግሉ ደጋፊዎች እንደተደሰቱ እስከዛሬ ደርሰዋል። በሁለቱም ወገን ያሉት በግጥም የሚያደርጉት መሸናቆጥ ለአንባቢ ቀልብ የሚስብ ቢሆንም በተለይ ከመለስ ዜናዊ ደጋፊዎች ዘንድ የሚሰማው “ደማችሁን ነው የምንመጠው” የንዴት አገላለጽ ትንሽ ይቀፋል። ዛሬ ድረ ገጻችን ከደረሱት በርካታ የድጋፍ ግጥሞችና የተቃውሞ መጣጥፎች መካከል ከኢሕአዴግ ወገን ደጋፊዎችም እንዲሁም ከነጻነት ትጉሉ ጎን ከቆሙት ወገኖች መካከል የአንዱን ልናቀርብ ወደድን።
በኤገን ሚኒሶታ ነዋሪ የሆነው አስመላሽ ሃይሉ የተባለው አፍቃሬ- ሕወሓት አበበ ገላውን በመቃወም “ዘመናይ ሰባኪ” ሲል ግጥም ጽፏል። በአንድ በኩል ደግሞ በዩቲዩብ ስሙን ያልገለጸ ገጣሚ በቪድዮ አቀናብሮ አበበ ገላውን “የጠላት አንገት ይደፋ” ሲል አሞካሽቷል። “የጠላት አንገት ይደፋ” ግጥምን በቅድሚያ ያድምጡና ከዛም የኢሕ አዴጉን ደጋፊ ግጥም ደግሞ ከታች ያንብቡ። በግጥሞቹ ዙሪያ የራሳችሁን አስተያየት መስጠት መታችሁ ነው።
ዘመናይ ሰባኪ
የኢሳቱ ጀግና – “ብሶት የወለደው”- ምላሱን ወድሮ
ሲያንጣጣው ዋለ – የቃላት እሩምታ – በጣቱ ቀስሮ
“መለስ አምባገነን ነው” ሲል – “ነው” የሚል ተቀባይ
ባዳራሹ ምህዋር – ውርውር የሚል – ለአይንም ባይታይ
“መለስ ወንጀለኛ ነው” ሲል – ይሰቀል ባይ ባይኖርም
እንደ ቀላል ትፋት – ቃል ለአፍ ባይመርም
“ነጻነት ነጻነት” አለ – ከምግብ በላይ በልጦበት
እጅ ላለመስጠት – ተገዝቶ – እውነታው ፈጦበት
ልክ እንደሬት ቢመረው – ከሃቅ ጋር መላተሙ
እልፍ አእላፍ ማይልስ ርቆ – አዳራሽ ውስጥ መከተሙ
“ነው! ነው!” ብሎ ‘ሚያስተጋባ
ፈልጎ ነበር ተቀባይ – የሱ እምባ የሚያነባ
አለቀረብህም በሉት – ይቁጠር ራሱን – ትፍቱን እንደላሰው
እሳት “ኢሳት”ን – አይፈራም ደርሶ ገላው እስኪያፈርሰው
“የዋሽንግተኑ ጀግና”
የኢሳቱ ” ሳተና
እርፍ ሳይጨብጥ – አሆ በል ባይ ከንቱ
ሃገረ ኢትዮጵያ – ላይደርስ የቃላት መክሊቱ
“…ነው! ነው!” ብሎ ባይ ፎካሪ
“የዴሞክራሲ ሰባኪ” የቃላት ደርዳሪ
“ዳግማዊ ቴዎድሮስ” ተብሎ ተሰይሞ
አያነው ባርምሞ
ይልቅ ወደ ነፈሰበት ከሚነፍስ – ሁለት ገጽታ ይዞ
ቢሞትም አይጎዳም – “ይሆነዋል ለጽድቅ” – ባንድ መንገድ ጉዞ
እንጂማ
ከማን ፊት እንደቆመ – መለስ ብሎ ቢያጠና
ጦርነቱ ከቃል አልፎ – በመድፍ ጥይት ቢሆንና
መድፍ ጥይት አስፈጥሮ – ላላስደነገጠው ጀግና
የአበበ ገላው መዝሙር – ምን እርባና አላትና?
ይልቅ አፉን ይቅደድ – ይቀባ ጥላሸት – እሱ እንደለመደው
ቁራ ሆኖ – ይኑር ሲጮህ – “ለህሊናው” ካልከበደው
አስመላሽ ከሚኒሶታ
No comments:
Post a Comment