Sunday, June 3rd, 2012 | Posted by zehabesha
በርከት ያሉ ምዕመናን በዋልድባ ጉዳይ በሚደረገው ሰልፍ ለመካፈል ወደ ዲሲ እየተመሙ ነው
13
Share
(ዘ-ሐበሻ) በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ መንግስት የዋልድባን ገዳም እየተፈታተነበት ያለውን ድርጊት በመቃወም በነገው ዕለት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ይደረጋል። በዋሽንግተን ዲሲ ለሚደረገው ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለመሳተፍ ከሚኒሶታ ኢትዮጵያውያን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች በመኪና ተጉዘው ዋሽንግተን ዲሲ ገብተዋል።
ትናንት ቅዳሜ ጁን 2 ቀን 2012 ከሚኒሶታ የተነሱት ምዕመናንን ጨምሮ ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የተንቀሳቀሱ ምእመናን በዋሽንግተን ዲሲ ሲደርሱ እዚያ የሚኖረው ምእመናን ደማቅ አቀባበል እንደተደረገለት የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዘጋቢዎች ከስፍራው ተናግረዋል።
ከሚኒሶታ የተንቀሳቀሰው ቡድን 8 የ እንግሊዘኛ እና 8 የአማርኛ መፈክሮችን ይዞ እንደሄደ የታወቀ ሲሆን በአጠቃላይ በዋሽንግተን ዲሲ እንዲሁም በሎስ አንጀለስ ነገ ጠዋት በሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ወደ 40 የሚጠጉ መፈክሮች እንደተዘጋጁ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
በዋሽንግተን ዲሲ፣ በሎስ አንጀለስና በሌሎች የአለማችን ክፍሎች የሚያዙት 18 የእንግሊዘኛ መፈክሮች የሚከተሉት ናቸው። በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያዘውን 18 የ እንግሊዘኛ መፈክሮች PDF ለማየት እዚህ ይጫኑ
ከሚኒሶታ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሄዱ ም እመናን የያዟቸው 16 የአማርኛና የ እንግሊዘኛ መፈክሮችን PDF ለማየት እዚህ ይጫኑ
ነገ ጁን 4/2012 በዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገውን ሰልፍ ለመዘገብ የዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ ሪፖርተርም ዋሽንግተን ዲሲ ገብታለች። ዘገባዎችን እንዳደረሰችን ለድረ ገጻችንን አባቢዎች እንደምናቀርብ ከወዲሁ እንገልጻለን።
No comments:
Post a Comment