"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Sunday, 3 June 2012

ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ደ. አፍሪካ የሄደው ብሔራዊ ቡድናችን 1 ለ 1 ተለያየ




Sunday, June 3rd, 2012 | Posted by zehabesha
ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ደ. አፍሪካ የሄደው ብሔራዊ ቡድናችን 1 ለ 1 ተለያየ
3
Share

ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ከደቡብ አፍሪካ ጋር ለመጫወት ወደዚያው ያቀናው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከደቡብ አፍሪካ ጋር በሃገሩ ላይ ነጥብ ተጋርቶ ወጣ። ምንም እንኳ በሮያል ባፎኪንግ ስታዲየም በተከናወነው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ሰላዲን ሰኢድ በ30ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መሪነቱን ቢይዝም በ71ኛው ደቂቃ በተቆጠረበት ግብ አቻ ለመውጣት ግድ ቢሆንበትም ውጤቱ ደቡብ አፍሪካ ካላት ስምና ዝና አንጻር ከበቂ በላይ ነው እየተባለ ነው።
የኢትዮጵያ ቡድን በ72 ደቂቃ አሉላን በአይናለም ሲቀይር ፤የደቡብ አፍሪካ ቡድን በ90 ደቂቃው ጨዋታ ጊዜ ሶስት ተጨዋች ቀይሯል፡፡ማዳካስካራዊው የመሃል ዳኛ ለአበባው ቡጣቆ በ23ኛው፤ለምንያህል ተሸመ 78ኛው፤ለሲሳይ ባጫ85ኛው፤ለአዲስ ህንፃ በ91ኛው ቢጫ ካርድ ሲያሳዩ፤ለደቡብ አፍሪካ ቡድን አንድ ቢጫ ካርድ ሰተዋል፡፡
የኢትየጵያ ቡድን ከሜዳው ውጪ ነጥብ ተጋርቶ መውጣቱ በሜዳውና በደገፊው ፊት ለሚያደርገው የመልስ ጨዋታ ትልቅ ብርታት ይሰጠዋል፡፡
አሰልጣኝ ሰውነት ከመሄዳቸው በፊት በሰጡት መግለጫ ‹‹ የሰላዲን ቡድኑን መቀላቀል ያለብንን ግብ የማስቆጠር ክፍተት ይሞላዋል ››ብለው ነበር፡፡እንዳሉትም ሰላዲን በናይጄሪያ ላይ ያሳየውን የግብ አዳኝነት ብቃት በደቡብ አፍሪካ ላይ በመድገም አሳይቷል፡፡

No comments:

Post a Comment