"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 5 June 2012

አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ፤ በአርቲስታ ታማኝ በየነ ዙሪያ ምሬት የተሞላበት ንግግርአደረጉ



አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ፤ በአርቲስታ ታማኝ በየነ ዙሪያ ምሬት የተሞላበት ንግግርአደረጉ
መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ፤ በአርቲስታ ታማኝ በየነ ዙሪያ ምሬት የተሞላበት ንግግር አደረጉ።
በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ተገኝተው ከኢትዮጵያውያን ጋር ታላቅ ስብሰባ ለማድግ ቢያቅዱም፤ በስብሰባው 27 ሰዎች ብቻ በመገኘታቸው፤ በአንፃሩ አርቲስት ታማኝ በየነ እና ዶክተር ብርሀኑ
በቴሌ ኮንፈረንስ በመሩት ስብሰባ ላይ በጆሀንስበርግ የሚኖሩ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን በመሳተፋቸው ክፉኛ የተበሳጩት አቶ ሀይለማርያም፤ “ የኛ ሰዎች የት ገቡ?” በማለት የኢህአዴግ ስብሰባ
አስተባባሪ የሆኑትን ካድሬዎቹን በቁጣ መልክ ሲጠይቁ ተሰምተዋል።
ከዚያም ለሦስት ሰዓታት በቆየው ገለፃቸው፤ በየጊዜው የሚፈጥሩት ሥጋት እየጨመረ የመጣውን እንደ ግንቦት 7 ዓይነቶቹን የተቃዋሚ ድርጅቶች እንቅስቃሴ እንዴት መግታት እንደሚቻል
አብራርተዋል።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አክለውም፦“ደቡብ አፍሪካ፤ ለመንግስታችን ህልውና አስፈላጊና ስትራቴጅክ ጠቀሜታዋ ከፍ ያለ አገር ነች።ግንቦት ሰባት እዚህ መንገዱን እንዲሠራ ልንፈቅድለት አይገባም።
እነሱ፦እዚያው ዋሺንግተን ተወስነው መቅረት አለባቸው” ብለዋል።

አቶ ሀይለማርያም በዚሁ ገለፃቸው አክቲቪስት የኔሰው ገብሬን፦’ የአዕምሮ ህመምተኛ የነበረ” ሲሉ የተደመጡ ሲሆን፤ ለሞቱም ተጠያቂው ግንቦት ሰባት ነው ብለዋል። ግንቦት ሰባት ተጠያቂ
የሚሆነው በምን መልኩ እንደሆነ ግን አላብራሩም።
የውጩ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለ 27 ካድሬዎች በሰጡት በዚሁ ማብራሪያቸው ሌላው አምርረው የተናገሩበት ጉዳይ፤ ስለ አርቲስት ታማኝ በየነ ነው።
መድረኩን ከመልቀቃቸው በፊት በሰብአዊ መብት ተመጓቹ ታማኝ በየነ መሪነት እየተካሄደ ባለው ስብሰባ ላይ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንደተገኙ መረጃ የደረሳቸው አቶ ሀይለማርያም
በንዴት፦”ታማኝ በየነ መንግስታችን የቀረው ዕድሜ ከሦስት ወራት እንደማይበልጥ ተናግረህ ነበር። ወደ አዲስ አበባ መጥተህ እንድትገለብጠን ጥሪ አደርግልሀለሁ”ብለዋል።
በወንደረርስ ክሪኬት ስታዲየም እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ማርች 24 ቀን በተካሄደው በዚሁ የኢህአዴግ ስብሰባ በጆሀንስበርግ ይኖራሉ ተብለው ከሚገመቱት ከሦስት ሺህ በላይ ሰዎች 27 ካድሬዎች
ብቻ የተገኙት፤ ተቃዋሚ ነን በማለት የመኖሪያ ፈቃድ ካገኙ በሁዋላ ኢህአዴግን ሲደግፉ የነበሩ ሰዎችን የማጋለጥ እንቅስቃሴ በመጀመሩ፤ብዙዎቹ፦”ፈቃዳችንን እንዳንነጠቅ”በሚል ስጋት የአቋም
ለውጥ በማድረጋቸው እንደሆነና በአካባቢው የሚገኙ ወጣቶች ባደረጉት ቅስቀሳ መሆኑን የደረሰን ዘገባ አመልክቷል።

No comments:

Post a Comment