ስንቶቻችን ነን እናታችንን በተለያየ የዕድሜ ክልል እያለን ያጣን ፩ እኛን ወለዳ ሳታየን ሳናያት ያጣናት ፪ ጡቷን ጠግበን ሳንጠባ ያጣናት ፫ እኛን ለቁም ነገር ለማብቃት ደፋ ቀና ስትል እሷን እየራባት እኛን ስታጎርስ እርሧን እየጠማት እኛን ስታጠጣ መከራን ችገርን በደልን ለልጆቿ ስትል ተቀብላ እፎይ ሳትል አሁን በቃሽ ደረስኩልሽ አረፍ በይ ሳንላት ያጣናት ኧዎ ቤቱ ይቁጠረው ሁል ጊዜ እንደ ድንጋይ ላይ መኝታ የሚቆረቁረን ፨እግዚኦ እናት አነሰን ኤሎሄ ፍርድ ተዛባ ባንተ ከጎናችን ሁሌ የማትርቅ እናት ትኑረን እንዳተ ስለማሪያም እንዳማሪያም እስከ አሪያም
No comments:
Post a Comment