"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Monday, 2 July 2012


መንግስት የጠላው ህዝብ
ከዳዊት ዋስይሁን, ጁላይ 02\2012
ይህ የምትመለከቱት ፎቶ እየጸለዩ ለመሆኑ ምንም ማብራሪያ አያስፈልገውም፣
ታዩታላችሁና ነው፣ ነገሩ ግን እየጸለዩ ያለው የእምነት ተቋም ውስጥ ነው ብላችሁ
እንዳትደመድሙ፣ ወይም የተመቻቸ ቦታ ላይ ሆነውም አይደለም፣ አንድ አይነት
እምነትም የላቸውም፣ ክርስቲያን ሙስሊም ሌላም ሌላም ሆነው ነው የሚታዩት፣
ጸሉታቸውን የሚመራ የሃይማኖትም አባት የላቸውም ሁሉም ባንድነት ሆኖ ያነባል፣
ይቃትታል፣ ያለቅሳል ወደፈጣሪ።
እነኝህ ከሞት መንጋጋ የተረፉ ኢትዮጵያውያን ለነሱና ከጎናቸው ስለተለዩአቸው 43
ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ያለቅሳሉ ለኢትዮጵያም መከራና ስቃይ ኡኡኡ ይላሉ ቀይ
መስቀል ለጊዜው እንዲጠለሉበት ከሰጣቸው አዳራሽ ውስጥ ሆነው!!!!!!
በአለፈው ወራቶች ውስጥ ከሰማናቸው አስከፊ የወገኖቻችን ሰቆቃዎች መሃል
 በሰኔ 20፣ 2012, 60 ኢትዮጵያውያን በሌክ ማላዊ ውስጥ ሰምጠው መሞታቸው፣
 ንጹኃን እህቶቻችን በመካከለኛው ምስራቅ ለአስከፊ እንግልትና ውርደት መጋለጣቸው፣
 1700  በላይ የሚሆኑ የአገራችን ዜጎች በሳውዲ አረቢያ እስር ቤት በመማቀቅ ላይ
መሆናቸው፣
 43  ወገኖቻችን ወደታንዛኒያ በኮንቴይነር ተጭነው ሲጓዙ በአየር ማጣት ታፍነው
በስቃይ ህይወታቸው ማለፉን፣
 ይህ አልበቃ ብሎን ከ50000  በላይ እህቶቻችን አሁንም ለባርነት በመንግስት ይሁንታ
ባለፈው ሁለት ወር ብቻ ወደ መካከለኛው ምስራቅ መላካቸው፣ይህ እንግዲህ የታየውንና የተሰማውን በጥቂቱ ለመጥቀስ በማሰብ ብቻ ነው ጉዳዩ ግን
ከምንገምተው በላይ ከመሆኑ የተነሳ ዛሬ ወገኖቻችን በየትኛውም የአለማችን ክፍል
በተበተኑበት ቦታ ሁሉ የመጀመሪያው የስደት መከራ ቀማሽ እየሆኑ ይገኛሉ።
ዛሬ የአለም አቀፍ ድርጅቶች መረጃ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያውያን አገራቸውን እየለቀቁ
በመሰደድ ግንባር ቀደም እየሆኑ መጥተዋል፣ ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግስት በዛች አገር
ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ እድገትና ለውጥ ማስገንዘቡን ህዝቡ ከመብላት አልፎ ሃብት
በሃብት መሆኑን በኢትዮጵያ የሚመረቱ ቁጥሮች ያሳዩናል።
የኢትዮጵያ መንግስት ቁጥርን በማምረት የሚወዳደረው የለም በሁሉም ዘርፍ ቁጥሩ
ትልልቅ ነው እውነቱ ግን የተገላቢጦሽ ነው። ከሰሞኑ አንድ የወያኔ ጽንፈኛ አቀንቃኝ
’’ለምን ቁጥር ይነግሩናል መለስ ዜናዊን አታለውታል ውነታው መርካቶ ሄዶ የጤፍና
የቅቤ ዋጋ መጠየቅ ነው ለምን መለስ ወረድ ብሎ ዞር ዞር ብሎ አይጠይቅም’’ በማለት
በተስፋ መቁረጥ ሲብከነከን ተስምቷል፣ እንግዲህ እውነቱን ራሳቸውም አልካዱት።
አንድ የሚጣረስ ነገር ይታየኛል ይህ ምናምን ፐርሰንት እየተባለ የሚነገረን ለማን ነው
እድገቱ ለህዝቡ ከሆነስ፣ ለየትኛው? ለምንስ ይሰደዳል?  ወይስ ለአቶ መለስ ቡድንና
ኃገሪቷን እየተቆራመቷት ላሉ ህንዶች፣ ቻይናዎችና አረቦች። ህዝቡማ በየቦታው ከቀየው
እየተፈናቀለ ጭሰኛ እና ስደተኛ እየሆነ በየደረሰበት ህይወቱን እያጣ ያለበት እውነታ ነው
የሚታየው።
ለምን አቶ መለስ አንዴ ረጋና ሰከን ብለው አያስቡም የዛች አገር ችግሯ ከቀን ወደቀን
እየከፋና ሁኔታዎች እየተወሳሰቡ እየሄዱ እንዳለ የፖለቲካ ተንታኝ መሆን አያስፈልግም
እዚህም እዚያም የመመረርና የአመጽ ምልክቶች ሲታዩ በመደብደብ፣ በማሰር እንዲሁም
በመግደል ለማፈን እየተሞከረ ነው በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በአፋር፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ፣
በኦጋዴን በሌሎችም የየለት ክስተት ከሆኑ ሰንበትበት ብሏል፣ ግን እኮ ይህ ሕዝብ የማን
ነው ለምንስ እንዲህ ሊጠላ ተፈለገ?  ያላሰቡበትና ያልተዘጋጁበት አደጋ ግን ሁሉም
በአንዴ በቃኝ ያለለት ውጤቱ የከፋ ይሆናል ለዚህም ነው ታላቁ መጽሃፍ ክፉ የሚባሉ
ቀኖች ሳይመጡ ….. ይላል፣
አሁን አልመሸም አብዮቱ ጎረቤት አገሮችን እያንኳኳ ነው ሰለዚህ ህዝብ ይደመጥ፣
ይከበር እንዲሁም ይወደድ፣ በኢንቬስትመንት ስም ህዝብ አይፈናቀል፣ የትውልድ ቅርስ
የሆነው የእምነት ቦታ አይነካ፣ የኃይማኖት ተቋማት ውስጥ የገቡ እጆች ይውጡ፣ በየስር
ቤት የታጎሩ ንጹሃን ዜጎች ይፈቱ፣ እርሶም በቃዎት ስልጣን ይልቀቁና ለህዝብ ያስረክቡ፣
በመቀጠልም መጽሃፍዎን ያንብቡ ካለበለዛ ይህ እድልም ሊያመልጥዎ ይችላል ያስቡ
ለዚህ ያልታደሉ አብዮቱ የበላቸው መሪዎች አሉና!!!
የሚገርመውና የሚያሳዝነው የተገለጠው እውነት የህዝቡ ድህነት፣ የመጎሳቆሉ መጠን
እንዲሁም ነጻነት የማጣቱ ጉዳይ ሲሆን፣ ነገር ግን ሁሌ ተቃራኒው ይነገረዋል። ምንያህል
እንደተንበሸበሸና እንደተትረፈረፈ፣ እንደፈለገ መሪዎቹን መምረጥ እንደሚችል፣ ኑሮውእንዴት እንደተቀየረ 24 ሰአት በኢቲቪ አላፊነት የጎደለው ፕሮፖጋንዳ ይጋታል ስለዚህ
በኢትዮጵያ ቴሌቪዢን ያለችው የበለጸገችውንና የተነገረላትን ኢትዮጵያ ፍለጋ ይሰደዳል።
መንግስት እንደመንግስት ህዝቡን የመጠበቅና የማስተዳደር አላፊነት ተጥሎበታል በዚህ
መስፈርት የአቶ መለስ መንግስት በተቋም ደረጃ የራሱን ህዝብ የሚጠላ፣ የሚዋሽ፣
የሚያስር፣ የሚገል እንዲሁም የሚያሰድድ ለመሆኑ ማጣቀሻ መስጠት አያስፈልግም ዜጎቹ
በገፍ ሲሰደዱ ምክንያቱ አጥንቶ ለዜጎቹ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ በመንግስት እቅድ
ተይዞ ዜጎች አገራቸውን ለቀው እንዲሰደዱ ይገፋፋል፣ ያበረታታል፣ ዜጎች በተሰደዱበት
ቦታ መከራና ስቃይ ሲበዛባቸው ቀድሞ ከመድርስና መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ
ተጠያቂነቱን ወደስደተኛው ወርውሮ አላስፈላጊ ስም ሲሰጥ ይታያል፣ ዜጎች በየትም ቦታ
አደጋ ቢደርስባቸው \ነፍስ ማጣትንም ያጠቃልላል\ የሚያስፈልገው መስዋእትነት ተከፍሎ
ላገራቸው ምድር እንዲበቁ ሲደረግ አይታይም ይልቁንም የፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያ
ያደርጉታል፣ ታዲያ የአቶ መለስ መንግስት ለማን ነው የቆመው ወይስ ’’ሁሉም እኩል
ናቸው እንዳንዶች ከእኩሎች በላይ ናቸው’’ ነው ጉዳዩ?።
ጽሁፌን ሳጠናቅቅ በመላው አለም በግፍና በታላቅ ስቃይ ላይ ያሉ ስደተኛ ወገኖቼ
የመጽናኛችንን ግዜ እግዚያብሄር አቅርቦ ሁላችንም በአገራችን የሰላም አየር
የምንተነፍስበትን ግዜ በመመኝት ሲሆን በሌክ ማላዊ፣ በአረብ አገራት አንዲሁም
በታንዛኒያ የተከበረ ህይወታቸውን ላጡ በገኖቼ የህሊና ጸሎት በማድረግ ጭምርም ነው።
በተለይ በታንዛኒያ ህይወታቸው በአሰቃቂ ሁኔታ ያለፈው 43  ወገኖቻችን የቀብር
ስነስርአት ከሚናፍቋትና ከሚወዷት አገራቸው ውጪ፣ 22ቱ በሞርጎጎ ቀሪዎቹ በዶዶማ
ተከናውኗል በስነስርአቱም ወቅት ከአደጋው የተረፉ ወገኖቻችን የመረረ ሃዘናቸውን
በቁጭትና በለቅሶ ገልጸዋል፣ በዚህ በተጠቀሱ አደጋዎች ሁሉ የአቶ መለስ መንግስት
ዜጎቹን ለመታደግም ሆነ አደጋው ከደረሰ በኋላ አስፈላጊውን እርዳታ ከማድረግና ፈጥኖ
ከመድረስ ይልቅ እንዳልሰማና እንዳላየ የዜጎቹን ጉጋይ ከመጤፍ ሳይቆጥር ዝምታንና
ማሰደድን ስራዬ ብሎ ይዞታል።
ጸሃፊውን ለመገናኘት፦zoloaba112@yahoo.com

No comments:

Post a Comment