"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Monday, 2 July 2012

ኳስና ቅሪላ ፤ ሆድና ሕሊና


                                                  ኳስና ቅሪላ ፤ ሆድና ሕሊና
                                              ከቴድሮስ ሐይሌ(tadyha@gmail.com)
                                      ‘’መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥
                                     አሳባቸው ምድራዊ ነው ፥መጨረሻቸው ጥፋት ነው ።’’ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3፥19
                                                  ዋሽቶ ለመኖር ልቤ አይችልም ከቶ፤ 
                                                      ታምኖ ይኖራል እንጂ ያለውን በልቶ። 
                                                   ደልቶኝ የሞላ ኑሮ መኖር ባልጠላም፤ 
                                                     ይህን ለማግኘት ብዬ እኔ አላጣም ሰላም ። 
                                                 …ሕሊና ሲያጣ ሰላም ወርቅ አልማዝ ሞልቶ ፤ 
                                                    ሳይተኙ መኖር ሊኖር  ከራስ ተጣልቶ ፤ 
                                                   አስኮንኛት ነብሴን እኔ አልሞላም ኪሴን!!! 
በሙያው የህዝብ ልጅነትን ከእድሜው በላይ መከበርን በሚሊዮኖች መፈቀርን በህፃን በአዛውንቱ መወደስን
የተቸረው ብላቴናው የሙዚቃው ኮከብ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ከዚህ በላይ የቀረበውን ስንኝ ያዘለውን አስተማሪ
መንፈሳዊና መካሪ በሆነው በዚህ ዘፈኑ ላይ በሐሰት ከሚገኝ ገንዘብ ይልቅ የሕሊና ሰላም ምንኛ የተሻለ እንደሆነ ያሳየበት
ከቤተመንግስቱ እስከ ቤተክህነቱ በንዋይ ፍቅር የእውነትን ዋጋ በሚያቃልሉበት ሃብት ሞልቶ የተተትረፈለት ከበርቴ
ከረሐብተኛ ሕዝብ መከራ ላይ የበለጠ ትርፍ ለማጋበስ ከማፍያና ወንጀለኛ አገዛዝ ጋር ተባብሮ ወገኑን ሲያስጨቁን
የሚታይበትን ‘’ምን አይነት ዘመን ነው የተገላቢጦሽ አህያ ወደ እርሻ ውሻ ወደ ግጦሽ ‘’ አበው እንዲሉ የኛ የኢትጽያውያን
ሁኔታ እንደምሳሌው እየሆነ ያ የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ በሚል ከባድ የቃልኪዳንን አክባሪ ከነበረ ማሕበረሰብ
የፈለቀ ወገን

እንዲህ ምግባሩ ተገላብጦ ተጠብቆና ተከብሮ የኖረ ባህሉን ሽሮ እንደ ውሃ ደራሽ እንደ ወፍ ዘራሽ ምንም
ትውፊትና የፀና መሰረት እንደሌለው አረማዊ ዛሬ ተበልቶ ነገ እዳሪ ለሚሆን ዛሬ ሞቆ ነገ ብል ለሚበላው የዛሬ ድምቀት
የነገ ውርደት ሊያመጣ ሕይወት እንደ አይን ጥቅሻ ለምትቀሰፍበት  ማናችንም ስለነገ ቀርቶ ስለ ዛሬ ውሎ አዳር እርግጠኛ
ባልሆንበት ለዚህ ላለቀ ዘመን ያውም የአመት ልብስ የእለት ጉርስ ሳይጎልበት የላመ የጣመ እየበላ የነጻነትን ወይን እየጨለጠ
የዲሞክራሲን ጮማ እየቆረጠ በሠላምና በእርጋታ በምዕራቡ ዓለም እየኖረ ኑሮ ሳይጎልበት ምንነካው ወገኔን በሃገር ውስጥ
ያለ የገዛ ወገኑን መከራ ሊያረዝምና ስቃዩን ሊያበዛ የእናት ሃገሩን ክብር ካቀለሉ ሃብቷን ከሚቦጠቡጡ አረመኔዎች ጋር
ሊዳራ ቀን ላነሳው ከበርቴ ሊጎነበስ ሠውበላውን የትግሬ ነጻ አውጪ የወንበዴ መንጋ የርኩሰትና የብተና መርዝ ሊጋት
እንዲህ ተነሳሳ ይህ አይነቱ ለጥቅም የመንበርከክ ክብርን ማድፋፋትና ይህን አይነቱ የመልከስከስ ባህል ከየት ተማርነው
ልበል ይህ ኢትዮጽያዊ ወግ አይደለም ሰብዓዊ ተፈጥሮ ያለው ሊፈጽመው የማይገባ የአራዊት ፀባይ ነው ።
ዳላስ ዲሲየፍቅር ጠንቅ የአንድነት ፀር መርገማዊው የዘራፊና የዘረኛ ጥርቃሞ የሆነው ሃገር ሻጩ የወያኔ ቡድን የጡት አባቱ
የሆነውና የኢትዮጽያን እምቅ ሃብት ያለገደብ የመጠቀም ኢ ፍትሐዊ የሆነ እድል ያገኘው የሳውዲው ቱጃር በሃገር ቤት
ያለው ሕዝባችን በረሃብ አለንጋ እየተለበለበ ሕጻናት በትምህርት ቤት በምግብ እጥረት በሚወድቁበት ወጣቱ ተስፋ ቆርጦ
ሃገር ጥሎ ለአስቸጋሪ ስደት በሚዳረግበት አረጋውያን ረዳት አጥተው
በየጎዳናው በወደቁበት በዚህ አስከፊ ዘመን እነዚህ ወገኖቹን
በመርዳት ለነብሱም ለስጋውም ለሞራሉም ለስሙም በሰማይም
በምድርም መጠቀም የሚችል ሆኖ እያለ ሕብረቱን ወያኔ ከተባለ
ሠይጣን ጋር በማድረግ ብዙ ሚሊዮን ዶላር በመመደብ በስደት
ያለውን ህዝብ ለማንበርከክ ለሃገሬ ለወገኔ ፍትህና ነጻነት ብሎ
የሚታገለውን ሞራል ለመግደል በታሰበ መልኩ በስፖርት ስም
የሚካሄደው አፍራሽ እንቅስቃሴ በሃገር ወዳድ ሃይሎች ተገቢውን
የማጋለጥና የተቃውሞ እንቅስቃሴ እየተደረገበት ያለ ቢሆንም
በዘረኝነት ትራኮማ የተንሸዋረረው ጎጠኛና ፤ ጥቅም አይነ ህሊናውን
የጋረደው አጎብዳጅ ሎሌ በዚህ የህዝብ ስቃይ መሳለቂያ መድረክ ላይ
በመኮልኮል የተለመደ አሳፋሪ ታሪኩ ከመድገም ያለፈ ምንም
ባይፈይድም ኢትዮጽያውያንን ለመበታተን እንኳን የወያኔ ድኩማን
ጭፍሮችና የአረብ ጀማላዎች ይቅርና ሃያላን ነን ለሚሉት የአለማችን
እብሪተኞች ያልተንበረከከ አኩሪ ታሪክ ያለው ጀግና ሕዝብ በመሆኑ ለነዚህም የሴራ ሃይሎች ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ
ታሪኩን ዳግም የሚያድስበት ግዜ እሩቅ አለመሆኑ እርግጥ ነው።
በዋሽንግተን ዲሲ ሊካሄድ ሽር ጉድ የሚባልለት ዝግጅት ስደተኛው ለሦስት አስርተ ዓመታት ተንከባክቦና ጠብቆ
ያቆየውን የስፖርትና የባህል ፌዴሬሽን ለማፍረስ ተዶልቶ የነበረው ሴራ ሲከሽፍ በሌላ ዙር ይህን የህዝብ አንድነት ያቆየ
ተቋም ለማዳከምና ብሎም ለመበታተን ሕሊናቸውን የሸጡ ጥቂት ሆድ አደር የቀድሞ የማሕበሩን አባላት በመረማመድ
የህዝባችንን ደም በመመምጠጥ ላይ ያለውን የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ወያኔ ሕዝብን እንደረገጠ እየዘረፈና እየገደለ ያለ
ሃሳብ የአገዛዝ እድሜውን ለማስቀጠል እንቅፋት በመሆን በማጋለጥና በመታገል የጎን ውጋት የሆነበትን የዲያስፖራ
ሕብረተሰብ ለመቆጣጠር ባለመ መልኩ የተጀመረውን ማምታታት እስከመጨረሻው በመታገል የሕዝባችን ገዳዮች ለፍርድ
የሚበቁበትን ሃገራችን ከዚህ አፋኝና ዘረኛ አገዛዝ ከነግብራበሮቹ የሚወገዱበትን ትግል ለማጠናከር የሚረዳበት አጋጣሚና
የወገን መነሳሳት ጎልቶ የታየበት ሁኔታን ፈጥሮዓል።
ኳስ በኛ ሕዝብ ዘንድ እጅግ የተወደደና የጋራ ስሜታችንን የምንጋራበት አንገት ላንገት ተቃቅፈን ለቡድናችን ድጋፍ
ለመስጠት ቀበሌ አዞን ወይም የግልገል ካድሬዎች ድንፋታ ተጽዕኖ ፈጥሮብን አይደለም የሃገር ፍቅር የባንዲራ ኩራት ግድ
ብሎን ነው አገዛዙ ያሰመረልንን የጎሳ መስመር አልፈን በአንድ ላይ የሚያቆመን በቆዳ የተወጠረው ድቡልቡል ቅሪላ ሳይሆን
የአብሮነት መንፈስ ነው። ባህልና ስፖርት የአንድነት መገንቢያ የፍቅር ማሰሪያ የአብሮነት ማሳያ እጅግ የላቀ ማህበራዊ
እሴትና ፋይዳ ያላቸው ህብረተሰባዊ ጸጋዎች በመሆናቸው ሰይጣናዊ አላማ ላነገቡ ሴረኞችና ሆዳቸውን ባስቀደሙ ሕሊና
ቢሶች የመገልሞቻ መድረክ እንዳይሆን አጥብቆ መታገል እያንዳንዱ የሃገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ዜጋ ሃላፊነትና ግዴታ
ባንዳ ነህ ይሉኛል የከበርቴ ሎሌ
ሆዴን ከሞላልኝ እኔ ምን ተዳዬ በመሆኑ ነቅቶ መገኘት ያለበት ከመሆኑም በላይ በዚህ የዋሽንግተን ዲሲው የሴራ ውጥን ውስጥ ባለማወቅና ከመረጃ
እጥረት የተነሳ ወገኖቻችን ተሳስተው በወገናቸው መከራ ላይ ዳንኪራ እንዳይረግጡ ሁሉም ዜጋ በየአካባቢው የማንቃትና
የቅስቀሳ ስራ በመስራት ሴራውን ለማክሸፍ የምንችለውን የማድረግ የሞራል ግዴታ አለብን።
በመጨረሻም በዚህ ሃገር አውዳሚዎች ዝግጅት ላይ በማን አለብኝነት በቅዱስ መጽሃፉ ሆዳቸው አምላካቸው
ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው ተብሎ አስቀድሞ የተነገረላቸው የትንቢት መፈጸሚያ የሆኑት ጥቅም አሳዳጆችና
ባለማወቅም ቢሆን ለመሳተፍ ለተዘጋጃችሁ ግለሰቦች የኪነት ባለሙያዎች ነጋዴዎችና የሃይማኖት ሰዎች በአጠቃላይ
ባንዶችና ጭፍሮች ጭምር ሊያውቁት የሚገባው መሪር ሃቅ ለዚህ የከበርቴ ተላላኪና የሰውበላው ወያኔ የሴራ መድረክ ላይ
መገኘት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሁኔታውች በከፋ መልኩ እንዲቀጥሉ ማበረታታት ማለት
መሆኑ እንዲያውቁት ይገባል።
 ረሃብ ስደት ውርደት ሞትና መከራ ይቀጥል ማለት ነው
 የሃይማኖት ነፃነት አይኑር እስላሙ መስኪዱ ደጃፍ እየተገደለ ይኑር ማለት ነው።
 የክርስቲያኑም መብት ይገፈፈፍ ገዳማት ይፍረሱ አባቶች ይዋረዱ ቤተክርስቲያን የካድሬ መፈንጫ ትሁን ማለት
ነው።
 የኢትዮጽያ ለም መሬት ለባዕዳን ችብቸባው ይቀጥል ማለት ነው።
 የመናገር የመጻፍ ሓሳብን የመግለጽ ነፃነት ተጨፍልቆ ይኑር ማለት ነው።
 ኢትዮጽያዊነት ይጥፋ ጎጠኝነት ይንገስ ማለት ነው።
 ጥቂት ዘራፊዎች ከህግ በላይ ተቀማጥተው ይኑሩ ማለት ነው።
 የአማራው የኦሮሞው የጋንቤላው የሱማሌው የአፋሩን ዘር የማጥፋት ሂደት ይቀጥል ማለተ ነው።
ስለዚህም ወንድሞቻችን አድራጎታቸውን ደግመው ደጋግመው ሊያጤኑት ይገባል አለያ የሚፈጠረው ሁኔታ ለሁላችን
የማይበጅ ከመሆኑም በላይ የዚህ ኢሞራላዊ አድራጎት ፈጻሚዎች በታረክም በትውልድም በእግዚያብሔርም ዘን
የሚያሰጠይቅ መሆኑን ሊረዱት ይገባል።
ኢትዮጽያ ለዘላለም ትኑር!!!
አሜን!!!

No comments:

Post a Comment