"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Sunday 1 July 2012

ዛሬ በአ. አ. ከሯጩ ቁጥር ይልቅ የፌደራል ፖሊሱ ቁጥር የማይተናነስበት የሩጫ ውድድር ተደረገ


 | 

ዛሬ በአ. አ. ከሯጩ ቁጥር ይልቅ የፌደራል ፖሊሱ ቁጥር የማይተናነስበት የሩጫ ውድድር ተደረገ


(ዘ-ሐበሻ)፦ ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ እየከዳው ያለው የአቶ መለስ አስተዳደር ትናንሽ ድሎችን ለማጣጣምና የሕዝብ ድጋፍ አለን በሚል ራሳቸውን ለማታለል ከፍተኛ ወጪ በማውጣት በአዲስ አበባ ለአባይ ግድብ ድጋፍ በሚል የሩጫ ውድድር ዛሬ በአዲስ አበባ አደረጉ። 4 ሚሊዮን የተመዘገበ አባል አለኝ የሚለው ኢሕአዴግ በቀበሌ ካድሬዎቹ አማካኝነት፣ በየሰፈሩ ለእናቶች እና ለስራ አጥ ወጣቶች የቀን አበል በመስጠትና “ስራ ታገኛለህ፣ ብድር ይሰጥሃል፣ ከስራ ትባረራለህ” በሚል ድለላና ማስፈራሪያ ሕዝቡን ሰላማዊ ሰልፍ ቢያስወጡትም፤ በሰልፉ ላይ የተገኘው ሕዝብ ግን አራት ሚሊዮን አባል ካለው ድርጅት የሚጠበቅ አይደለም።
እንደ ዘ-ሐበሻ የአዲስ አበባ ምንጮች ገለጻ ከሆነ የአቶ መለስ መንግስት የደረሰበትን የፖለቲካ ኪሳራ በትርፍ ለማካካስ የፈለገ ጥረት ቢያደርግም እየተሳካለት አይመስልም። “ሕዝቡ ጥርሱን ብቻ እንጂ ልቡን ለኢሕአዴግ እንዳልሰጠ በሰልፉ ላይም አሳይቷል” ያለው የዘ-ሐበሻ ምንጭ ዛሬ መንግስት በጠራው ሰልፍ ላይ የተገኘው አብዛኛው ሕዝብ የወያኔ የፓርላማ አሻንጉሊቶች፣ የቀበሌ ካድሬዎችና በጥቅም የተደለሉ ወጣቶች ናቸው። በዚህ ዛሬ 10 ኪሎ ሜትር በሸፈነው የ”እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን”ሩጫ ውድድር ላይ ከማረሚያ ቤት፣ ከፌደራል ፖሊስ የተውጣጡና በመንግስት ደመወዝ የሚከፈላቸው አትሌቶች ሳይወዱ በግዳቸው እንዲገኙ ተደርገዋል ያለው ምንጩ በዚህ ሰልፍ ላይ አልገኝም ያለ ማንም ሰው ለምን እንዳልተገኘ ሰኞ ጠዋት በሚሰራበት ቦታ ሪፖርት እንዲያቀርብ በካድሬዎች ማስፈራሪያ ተደርጓል። ሥራውን ቢያጣ ምን ሊሆን እንደሚችል የሚያስበው ሕዝብ ሳይወድ የግዱ በዚህ ሰልፍ ላይ ተገኝቷል።
በሩጫው ስፍራ ከፍተኛ ብጥብጥ ይነሳል በሚል ከሯጩ ቁጥር የማይተናነስ የፌደራል ፖሊስ ሩጫው የሚደረግበትን ቦታ አጥሮ እንደነበር የገለጸው ዘጋቢያችን፤ በሩጫው ላይ የተሳተፉትን አንዳንድ የክፍለከተማና የማዘጋጃ ቤት ባልሰልጣናትን ለማጀብም ስፍር ቁጥር የሌለው ሰምቶ አዳሪ (ሰላይ) በሩጫው እንዲሳተፍ መደረጉን ገልጾ ታዛቢዎች ሩጫው በመለስ ካድሬዎች የተደረገ እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብን ያማከለ አይደለም ብለዋል። ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ከቤት ውጭ ስብሰባን በተከለከሉበት ሃገር ኢሕ አዴግ ብቻውን ትናንሽ ድሎችን ፍለጋ ብዙ ወጪ አውጥቶ እንዲህ ያለውን ሰልፍ ማዘጋጀቱ ያስተዛዝባል የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች ይህ ሩጫ አላማውን የሳተ ነው ሲሉ ተችተውታል።
የመለስ መንግስት አባይ በሚል የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ያነሳው ጥያቄ በህዝብ ዘንድ እንደ ድራማ የሚታይ በመሆኑ ይህን ድራማቸውን ለማሳመን የማይምሱት ጉድጓድ ባይኖርም ሕዝብ ከዝንብ ማር አይጠብቅም የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ።
የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር አቶ በረከት ስምኦን የግድቡን ሥራ ለማቀላጠፍ በቅርቡ ከፍተኛ የግንባታ መሳሪያዎች ወደ ሥፍራው መንቀሳቀሳቸውንና ተጨማሪ የሰው ኃይል ተልኳል፤ ለዚህ ግድብ
ግንባታ ገቢ ለማሰባሰብ በሩጫው የተሳተፉ የፓርላማ አባላትን እና የመንግስት ባለስልጣናትን ማድነቃቸውን ተያይዞ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

No comments:

Post a Comment