"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Friday 19 October 2012

የኢትዮጵያ ፓርላማ አባላትን “እግዚአብሄር ኢትዮጵያን በበረከቱ ይጠብቃት” መባሉ አሳቃቸውያሳዝናል! (ደረጀ)


AMHARIC NEWS

የኢትዮጵያ ፓርላማ አባላትን “እግዚአብሄር ኢትዮጵያን በበረከቱ ይጠብቃት” መባሉ አሳቃቸውያሳዝናል! (ደረጀ)

October 18, 2012   ·   0 Comments
የትናንቱን የፓርላማ ውሎ አላየሁትም ነበር። ስብሰባውን በኢቲቪ የተከታተለ ጓደኛዬ፤ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ንግግራቸውን ሲጨርሱ<< እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን በበረከት ይጎብኛት>> በማለታቸው አፈ-ጉባኤውን አባ ዱላን ጨምሮ የፓርላማ አባላቱ እንደሳቁ በፌስ ቡክ ገጹ አስነበበን ። “ በዚህ እንዴት ሊስቁ ይችላሉ?”ብዬ ቅሬታዬን ስገልጽ ሌለኛው ጓደኛዬ፦< ..የሳቁትኮ “..በበረከት ይጎብኛት” የሚለውን አባባል- ከአቶ በረከት ስምዖን ጋር አያይዘውት ነው>> ብሎ በማስፈገግ አረጋጋኝ። አሁን ቪዲዮውን ሳየው ግን የሳቁት የንግግሩ ቅኔነት ገብቷቸው ሳይሆን፤ የእግዚአብሔር ስም በመጠራቱ እንደሆነ ተረዳሁ።
ያደጉትና የሰለጠኑት አገሮች ዶላራቸው ላይ፦We Trust in God እያሉ ሲጽፉ፤ እነ አባ ዱላና መሰሎቻቸው፦ <እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርካት>በሚል ንግግር መንጋጋቸው እስኪታይ ይስቃሉ።ልብ በሉ! ሰውን እያመለኩ ያሉ ደካሞች ናቸው በእግዚአብሔር ስም መጠራት የሳቁት። ይሁን እንጂ ቅሬታዬ “ለምን አሜን አላሉም?” ከሚል የመነጨ አይደለም። አለማመን ወይም በፈለጉት ማመን መብታቸው መሆኑን አውቃለሁ። እያልኩ ያለሁት ፤ብብቱን እንደኮረኮሩት ሰው የእግዚአብሔር ስም ሲጠራ፤ ምን አስገለፈጣቸው ነው?
<<የሮማው ፈረስ ካሊጉላ-በንቀት ልቡ የሰባ፦
ታዛዥና ተጋላቢ-ፈረሱን ፓርላማ አስገባ፣
ከዚያን ዕለት ጀምሮ-ፈረሶች ወንበር ለመዱ፣
ለማመን ማየት ካሻችሁ-እኛ አገር ፓርላማ ሂዱ>> ያለው ማን ነበር?
እነሆ ቪዲዮው፦
http://www.amharictube.com/musicvideo.php?vid=21a52302b

No comments:

Post a Comment