"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Thursday 21 June 2012

ስልሳ ኢትዮጵያዊንን ይዞ በማላዊ ኅይቅ ላይ ይጓዝ የነበረ ጀልባ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ እስካሁን 47 ሰውሞተ


ዋሽንግቶን ፖስት የማላዊ ፖሊስን በምንጭነት ጠቅሶ ባወጣው በዚህ የአሰቃቂ አደጋ ዘገባ 60 ኢትዮጵያዊያንን ይዞ በማላዊ ኃይቅ ላይ ይጓዝ የነበረ ጀልባ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ እስካሁን የ47 ኢትዮጵያውያን ሬሳ መገኘቱንና ቀሪዎቹም ሳይሞቱ እንዳልቀረ ጠቅሷል።

የፖሊስ ሪፖር ህገ ወጥ ስደተኞች ያላቸውን 60 ኢትዮጵያዊያንን የጫነው ጀልባ አደጋ የደረሰበት ካሮንጋ በተሰኘ ከተማ አቅራቢያ ማለትም ከማላዊ ዋና ከተማ 600 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ከምትገኝ ካሮንጋ በተሰኘች ከተማ አቅራቢያ ባለፈው ሰኞ ሌሊት እንደሆነ ተዘግቧል። የአካባቢው ነዋሪዎች  በውሃው ላይ የሚንሳፈፍ የሰው አካል ያዩት ማክሰኞ ጠዋት እንደነበርም ዘገባው አክሎ ገልጿል።

 ችግር ከበዛባቸው የአፍሪካ ሃገራት የሚነሱ ዜጎች በማላዊና ታንዛኒያ እንዲሁም በማላዊና ሞዛምቢክ መካከል የሚገኘውን ፖሮስ የተሰኘውን ድንበር በማቋረጥ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ጥረት ማድረጋቸው የተለመደ ነው ሲል ይሀው ዘገባ ያስረዳል።

Filed in: Amharic Posts

No comments:

Post a Comment