"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Monday, 18 June 2012

በቺካጎ የኢሳት ገንዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራም በድል ተጠናቀቀ “በሳውዝ አፍሪካ የአገኘሁት ክብር በሚሊዮን ዶላር አይከፈልም” ታማኝ በየነ


www.maledatimes.com

በቺካጎ የኢሳት ገንዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራም በድል ተጠናቀቀ
በሳውዝ አፍሪካ የአገኘሁት ክብር እሚሊዮን ዶላር አይከፈልም ታማኝ በየነ
በቺካጎ ከተማ የተካሄደው የኢሳት የገንዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራም በመልካም ጅመር የተከናወነ ሲሆን በእለቱ ከአምስት መቶ በላይ የሚጠጉ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያኖች እና የለውጥ ፈላጊ ኢስቶአክቲቪስቶች እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲ አባላቶች  በስፍራው መገኘታቸው በአካባቢው  የተገኘው ሪፖርተራችን ዘግቦአል። ይህም ሆኖ ሳለ  በአዘጋጅ ኮሚቴው የመክፈቻ ንግግር የተደረገ ሲሆን መልካም አስተዳደር በሃገሪቱ ላይ እንዲሰፍን እና የመገናኛ ብዙሃን ነጻነታቸውን አግኝተው መስራት የሚችሉበትን መንገድ መፍጠር አለብን ብለዋል ።ቀጣዩን ንግግር አክቲቪስት ታማኝ በየነ ከስር መሰረቱ አመጣጡን እና  እና የኪነጥበብ ሰውነቱን ከመግለጽ አንስቶ በአለው የድምጽ መናገር መብትን አስመልክቶ በሃገሪቱ ላይ የሚከናወነወን አሰቃቂ ተግባር ገልጾአል ። ይህም ሲሆ በመንግሥት አስተዳደር ግፋዊ አገዛዝ የሚደረገውን ጭቆና ሲኮንን ተሰምቶአል ። በመቀጠልም በኢትዮጵያ የሚደረጉትን አፈናዎች አስመልክቶ ሲጠቁም በቅርቡ የተካሄደውን የስካይፒ አፈና እና የፍርዱን ሁኔታ ጠቆም ሲያደርግ በሃገሪቱ ላይ መስዋት ከሆኑት አንስቶ የየኔሰው ገብሬ የነጻነት መንፈስ የሁላችንም የትግል ህይወት መሆንን አመክሮ ገልጾአል   በኩል የመለስ ዜናዊ አስተዳደር ፍራቻቸው የመገናኛ ብዙሃን ሲሆን ለዚህም ዋነኛ ምሳሌ የሚሆነው በሃገሪቱ ላይ የተሰማራውን የኢሳት ቴሌቪዥን አፈና እንደምክንያት ገልጾአል ። ለሃያ አንድ አመታት በአስተዳደርላይ የቆየው የወያኔ መንግስት አንድም ቀን እውነትን ሳይናገሩ መውደቂያቸው ደረሰ በአገሪቱ ላይ መንግስግት በሚያስተዳድረው ቴሌቪዥን ከእውነት የራቀ ነው ሲል አብራርቶአል መረጃዎችን በማጣቀስ ባቀረበው ሪፖርት ላይ ዘገባዎቹን ለህዝብ በምስል አቅርቦ አሳይቶአል ።በሌላም በኩል ባሳለፍነው ወር በሳውዝ አፍሪካ የተደረገለትን አቀባበል እና በኢሳት የገንዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራም ላይ ለተደረገው ትልቅ ተሳትፎ የሚደነቅ ነው በሳውዝ አፍሪካ ያገኘሁት ወይንም የሰጡኝ  ክብር የሚሊዮን ዶላርስ የሚከፈል አይደለም ።እንደ ሌሎቹ በጥቅም አልንበረከክም እኔ የምኖረው ለህዝብ ነጻነት እና የህሊና ዳኝነት እንጂ ውሸትን ዋሽቼ ለመኖር አይደለም እንደዚያ ቢሆን ኖሮ ቀድሞ ከሼክ መሃመድ አላህሙዲ ጋር የነበረኝን ግንኙነት አላቋርጥም ነበር ።የህሊና ዳኝነት የመንፈስ እርካታን ይሰጣል እንጂ አይጎዳም በማለት አክሎ ገልጦአል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በጂ8 ሰሚት ፕሮግራም ላይ ለመለስ መንግስት ላይ የተጣለባቸውን የግፋዊ አገዛዝ አመልካችነትን  ሃሳብ በገለጸው በጋዜጠኛ  አበበ ገላው አስመልክቶ የምስል ቅንብር በቀረበበት ሰአት የተስብሳቢው ህዝብ በሞቀ አቀባበል  እና ጭብጨባ አድናቆታቸውን ቸረውታል።
መለስ ዜናዊ በጋዜጠኞች ላይ የተናገሩትን የፓርላማ  ንግግር አስመልክቶ “ጋዜጠኞች በመንግስት ሳይከሰሱ በሚሳኤል ይገደላል “ብለው መናገራቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነበር ይህም ሆኖ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በመላው አለም ተቀባይነት አግኝተው የሽልማት የክብር ተሸላሚ በመሆን ስማቸው በአለም ገናና ሆነዋል በማለት በአለም አቀፍ ተሸላሚ የሆኑትን ሰርካለም ፋሲል፣ዳዊት ከበደ፣ሲሳይ አጌና ፣እስክንድር ነጋ ፣ ርዮት አለሙ በአብነት ሊጠቀሱ በቅተዋል ።
በየጊዜው ለሚከናወነው የኢሳት እርዳታ ማንኛውም ሰው ግዴታውን መወጣት የሚችለው በየወሩ ከኪስ ገንዘቡ 20$ በማውጣት ቢረዳው የወደፊት የሃገሪቱን ነጻነት እና የመገናኛ ፍላጎት ጥማት ማሳደግ እንደሚቻል በተደረገው ፓናል ውይይት ለይ ለመግለጽ ተችሏል። በሌላም በኩል የፕረስ ነጻነትን አስመልክቶ በተለያዩ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ላይ እየተሰራጨ ያለውን የአበበ ገላው የአለም አቀፍ የጋዜጠኝነት ፍቃድ ተነጥቆአል የሚለው የተናፈሰ ወሬ ከእውነት የራቀ ትልቅ ውሸት ነው በማለት አበበ ገላው የገለጸ ሲሆን የመንግስት ሚዲያዎች እንደ አንድ ተራ ሰው እንጂ እንደጋዜጠኛ አለመቁጠራቸውንና ምንም እንዳልተፈጠረ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በውጭ ጉዳይ ሚስኒስቴር ቃል አቀባይ የውሸት ሪፖርት መተላለፉም ይታወሳል ።ሆኖም ግን ይህንን ሪፖርት እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያኖች የመለስ ዜናዊን አስደንጋጭ የሆነ የራስ ምታቸውን በዩቲዩብ እና በሌሎች የቪዲዮ ቻናሎች ላይ መጎብኘታቸውን ለማወቅ ችለናል ።
አበበ በለውም በበኩሉ የህዝብ መረጃ ፍላጎት ተስተካክሎ እስካልቀረበ ድረስ እና ለውጥ እስካለመጣ እኔ እራሴን መስዋእት እስከማድረግ ድረስ ለመድረስ የምችል ሰው መሆኔን እና ለእውነት ብቻ በመቆም ለፕረስ ነጻነት እና  ለህዝብ ህሊና ዳኝነት ለመታገል ወደ ኋላ አልልም በማለት ገልጦአል ።
በመጨረሻም በቺካጎ በተደረገው የገንዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራም $ 12.000 ከበጎ ፍቃደኞች የተሰበሰበ ሲሆን ከአንድ ግለሰብ ደግሞ የቴዎድሮስ ካሳሁን ጥቁር ሰው አልበም እና የታደለ ገመቹን አልበም በበጎ ፍቃደኝነት በነጠላ 50 ኮፒዎችን በመስጠት የሽያጩ ገቢ ለኢሳት እንዲሆን ያደረገ ሲሆን በሌላም በኩል ደግሞ በአጼ ሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት መገባባያ የነበረውን የብር ኖት የያዘ ስእላዊ ቅርጻ ቅርጽ (እውነተኛ ብር ኖት)በተከፈተው ጨረታ $11369 የደረሰ ሲሆን የጨረታው ሁኔታ ከፍተኛ ፉክክር ስላመጣ  የብር ኖቱን የያዘው የፎቶ ግራፍ ፍሬም ለኢሳት የወደፊት ማሰባሰቢያ ሊያደርግበት እንዲችል ለአሰባሳቢው ኮሚቴ ገቢ እንዲሆን ተደርጓል።

No comments:

Post a Comment