"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Monday 18 June 2012

“የወያኔ ፌዴራል ፖሊስና ምስኪኑ ገበሬ......”


“የወያኔ ፌዴራል ፖሊስና ምስኪኑ ገበሬ......”
አንድ ገበሬ ካመረተው እህል ጥቂቱን ያህል ወደ ከተማ ወስዶ ለመሸጥ አህያው ላይ ጭኖ በአዲስ አበባ ዙሪያ
ከሚገኘው የገጠር መንደሩ በማለዳ ተነስቶ በቀለበት መንገድ ላይ ጉዞ ይጀምራል። ብዙ ከተጓዘም በኋላ በድንገት
ከኋላው በፍጥነት ይመጣ የነበረ ፌዴራል ፖሊሶችን የጫነ ትራክ እሱንም አህያውንም ክፉኛ ይገጫቸውና ገበሬው
በአንድ ጥግ አህያውም በሌላው ጥግ ተፈናጥረው ይዘረራሉ።
ይህ ከሆነ ከ15 ቀን በኋላ ገበሬው የትራኩን ሹፌር ከሶ ፍርድቤት ያቆመዋል። የትራክ ሹፌሩ ጠበቃም ገበሬውን ራሱን
በምስክርነት ይጠራዋል።
ገበሬው መዳፉን በመጽሃፍ ቅዱስ ላይ አስቀምጦ በእውነት  ለመመስከር መሃላ ከፈጸመ በኋላ በደረሰበት ጉዳት
አከርካሬው ተሰብሮ ነበርና ቆሞ ለመመስከር ስለማይችል ዊልቸሩ ላይ እንደተቀመጠ ጠበቃው ጥያቄውን ቀጠለ።
ጠበቃ፡ የፌዴራል ፖሊስ አባል የሆነው 10  አለቃ  ሃጎስ  በርሄ ያሽከረክረው በነበረው ትራክ ላደረሰብኝ ጉዳት ካሳ
ይክፈለኝ ብለሃል?
ገበሬው! እንዴታ አዎ! ብያለሁ ይ! ጉዳቱንም ሃኪም አርጋግጦታል፤ ይሀው ማስረጃው! አከርካሬዬ ተሰብሮ..! አድቅቆ
ጥሎኝ...እያለ በምሬት ሊቀጥል ሲል ጠበቃው ጣልቃ ገብቶ፤ እሺ ይበቃል መልሱ ተመልሷል ወደ ሌላው ጥያቄ
እንለፍ።.....ይላል

ጠበቃ፡ ግጭቱ እንደደረሰ ወዲያውኑ ሹፌሩ ወደ ወደቅክበት መጥቶ ጉዳትክን ሲጠይቅህ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰብህ
ነግረሀዋል አልነገርከውም?
ገበሬው! “ነገርን  ከስሩ! ውሃንም  ከጥሩ..” እንደሚባለው ከመጀመሪያው ጀምሮ ያለውን ላስረዳ፡ ብሎ ሊቀጥል ሲል
ጠበቃው አቋረጠው።
ጠበቃው፦ ዝርዝሩን አልፈልግም ለ10  አለቃ ሃጎስ ምንም ጉዳት አልደረሰብኝም ብለሃል አላልክም ነው ጥያቄው።
ስለዚህ አዎ! ብያለሁ። ወይም አላልኩም የሚል መልስ ይበቃል።
ገበሬው፡ ትራኩ ከኋላችን መጥቶ እኔንም አህያዬንም ወገባችንን ሰትሮ እንደጣለን ሹፌር ከመኪናው ዘሎ ወርዶ..... ብሎ
ሊቀጥል ሲል አሁንም ጠበቃው አቋረጠው።
ጠበቃው፡ ክቡር ፍርድ ቤቱ ምስክሩ ለጠየቅኩት አጭር ጥያቄ አጭር መልስ እንዲሰጥ ይዘዝልኝ። እኛ ባለን መረጃ
በአደጋው ወቅት ደንበኛዬ 10 አለቃ ሃጎስ ይህ ሰው ተገጭቶ የወደቀበት ድረስ ሄዶ ስለ ጉዳቱ ሲጠይቀው ምንም ጉዳት
አልደረሰብኝም ብሎ በፍጥነት ተነስቶ እየተራመደ ከአካባቢው መሰወሩን ማስመስከር እንችላለን። ደህና ነኝ ብሎ
ከሄደ ከ15 ቀን በኋላ ወገቤ ተሰብሯል ብሎ በዊልቸር መሄዱ የደንበኛዬን ገንዘብ በካሳ ስም አጭበርብሮ ሊበላ ማሰቡን
የሚጠቁም ነውና ፍርድ ቤቱ ቀጥተኛ መልስ እንዲሰጥ ያድርግልኝ ፡ ሲል ዳኛውን ይጠይቃል።
ዳኛው፡  ምስክሩ የሚሉት ካለ ፍርድ ቤቱ ቢሰማው ምንም ጉዳት የለውምና ምስክሩ በዝርዝር ያስረዱ።
ገበሬው፡ አመሰግናልሁ ክቡር ዳኛ! ቅድም እንዳልኩት በቀለበት መንገድ ከአህያዬ ጋር ስንጓዝ ይሄ 10 አለቃ ትራኩን
እያበረረ እላያችን ወጣ፡፡ እኔን ወገቤን ሰትሮ እያ ማዶ ጣለኝ አህያዬንም ተመሬት ለትሞ ወዲያ ጥግ ወሸቃት። እኔ
ወገቤን እንክት አደረገኝ። የሞት ሞቴን ቀና ብዬ ሳይ አህያዬ በጣር ታንኳርራለች ። ወዲያው ይሄው ሹፌር ከመኪናው
ዘሎ ወደ አህያዬ ሲሮጥ ተመለከትኩት። አጠገቧ ደርሶ ጎንበስ ብሎ ካያት በኋላ ሽጕን አውጥቶ በአይኖቿ መሃል ሁለት
ጥይት ለቀቀባት። ቀጥሎም ሽጉጡን በአንድ እጁ እንዳጠለጠለ ወደኔ ሮጥ ሮጥ እያለ መጣና ጎንበስ ብሎ አይኔን እያየ
በጣም ተጎዳህ? ብሎ ቢጠይቀኝ የአህያዬ  እጣ  እንዳይደርሰኝ እረ ምናምኒትም አልነካኝ ብዬ በድንጋጤ የአከርካሬዬ
ስብራት ሳይታወቀኝ በፍጥነት አካባቢውን ለቀቅኩ ።ከጥይት መዳኔን ሳውቅ ግን መላወስ አቅቶኝ ራሴን ስቼ አንዱ ጥግ
ወደቅኩ። ለነፍሴ ያለ ተዶክተር ወስዶኝ መራመድ ባልችልም ነፍሴ አልወጣችም ሲል መሰከረ ....
ምን ተፈረደ ብላችሁ እንደማትጠይቁ ተስፋ አለን ?

No comments:

Post a Comment