"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 19 June 2012

የባልካኑ የእግር ኳስ ንጉስ!(ቴዎዶር ገስላሴ)


የባልካኑ የእግር ኳስ ንጉስ!(ቴዎዶር ገስላሴ)

ከጥቂት ዓመታት በፊት ይህን ስም ማንም አያውቀውም
ከወላጆቹና አብሮ አደግ ጓደኞቹ በስተቀር ዛሬ ግን በዓለም
ላይ ያሉ የኳስ አፍቃርያን በሙሉ ማለት ይቻላል ይህን
ምትሃተኛ የቀኝ መስመር ተከላካይ ተጫዋች ዐይናቸውን
ሳያሹ የአውሮፓው ክስተት መሆኑን ያምናሉ።ይህ ልጅ ማን
ነው?የት ተወለደ?የትስ አደገ?ግለ ታሪኩን ቆንጥሬ
ላካፍላችሁ ወደድኩኝ።
ቴዎዶር ገስላሴ
24/12/86 እ.ኤ.አ. በቀድሞዋ ቼኮዝላቫኪያ በአሁኗ ቼክ
ሪፐብሊክ ለትምህርት ሄዶ ፍቅር ካጣመራቸው የአገራችን
ዜጋ ከኢትዮጵያዊ አባትና ከቼካዊት እናት በትንሿ
የቼኮዝላቫኪያ ከተማ ትሬቢክ(Třebíč, Czechoslovakia)ተወለደ።
1.82cm ቁመት ያለውና የ25 ዓመቱ ወጣት ቴዎዶር
እግር ኳስን ገና የ7ዓመት ልጅ እያለ ነበር የጀመረው።
በአሁኑ ወቅት ለአገሩ ቡድን ስሎቫክ ሊበራክ ሲጫወት፣
ለወጣት ብሔራዊ ቡድኑም አገልግሏል፣በቼክ ታሪክ
ውስጥ የመጀመሪያው ጥቁር ተጫዋች ሲሆን በቀለሙ
ከባላንጣዎቹ የስፓርታ ፕራግ ደጋፊዎችና አሁን
እየተካሄደ ባለው 2012የአውሮፓ ዋንጫ ላይም ከሩሲያ
ደጋፊዎች የዘረኝነት ፀያፍ ስድቦች ደርሰውበታል።
ስለዚህ ጉዳይ ሲጠየቅ ግን¨እኔ ምንም አስተያየት
አልሰጥም¨በማለት ጉዳዩን ለጋዜጠኞች ዘግቶታል።
ቴዎዶር ቼክ የምትመካበት ድንቅ ተከላካይ ብቻም
ሳይሆን ፈጣንና ንቁ፣ለጎል ኳሶችን አመቻችቶ የሚሰጥ፣
በሌሎች ትልልቅ የአውሮፓ ቡድኖች የሚፈለግ የወቅቱ
ክስተት ነው።የት መጫወት እንደሚፈልግ ሲጠየቅ
¨የስፔን እግር ኳስ ይስበኛል እወደዋለሁም¨ በማለት
አጭርና ግልፅ መልስ ሰጥቷል።የዚህ ኢትዮ-ቼካዊ ወጣት
ማረፊያ የት ይሆን?
*መልካም የጫወታ ዘመን ይሆንለት ዘንድ የሁላችንም
ኢትዮጵያዊያን ምኞት ነው!¨ደም ከውሃ ይቀጥናል
ይባል የለም?¨

Like ·

No comments:

Post a Comment