"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Friday 22 June 2012


አውራምባ ታይምስ (ዋሺንግተን ዲ.ሲ) – የህግ ባለሙያ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እንዲሁም የኢትዮጵያዊያን ውርስና ቅርስ ማህበር በሰሜን አሜሪካ ሊቀመንበር የሆነው ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ ኢትዮጵያዊን በዲሲው የአላሙዲን ሰፖርት ፌስቲቫል ላይ እንዳይገኙና ለነጻነትና ዴሞክራሲ የሚደረገውን ትግል አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቀረበ፡፡
ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ

የጀግኖች አባቶች አገር የሆነችው ኢትዮጵያ በትውልድ ሽግግር የተገነባ ማንነቷ በጥቅማጥቅም ሸጠው ዛሬን ብቻ እንኑር የሚሉ ጥቂቶች አገር ብቻ ሆናለች ያለው ዶ/ር ሼክስፒር፣ ጋዜጠኞች ገለልተኛ አመለካከት በማንጸባረቃቸው፣ ተቃዋሚዎች በህገ መንግስቱ የተረጋገጠላቸውን መብት ተግባራዊ በማድረጋቸው ብቻ ለእስር እየተዳረጉ እንዲሁም ሚሊዮኖች በረሀብ አለንጋ እየተገረፉ ባለበት በአሁኑ ወቅት ከወንጀለኞች ጋር አሸሼ ገዳሚ የምንልበት ምንም ምክንያት ሊኖር አይገባም በማለት ኢትዮጵያዊን ሆዳሞች የሚያቀርቡትን መደለያ ውድቅ አድርገው በዳላስ እንዲሰባሰቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

No comments:

Post a Comment