"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 19 June 2012

የስደቱ ወላፈን በኖርዌ


የስደቱ ወላፈን በኖርዌ
(ክፍል ሁለት)
ከብ.ወ

                          ናታን "መጠቀምያ" ወይንስ "የስደቱ ፖለቲካ የጥቃቱ ሰለባ"?

ዘወትር በሚታተሙት የኖርዌ ጋዜጦች ላይ ሕፃኑ ስደተኛውን ናትንን ያዘለ ዜና እስከነፎቶግራፉ ብቅ ይላል።
ምናልባት ማጋነን አይሁን እንጂ ከሃገሪቱ ንጉሳዊ ቤተሰቦች ይልቅ በሰሞነኞቹ ጋዜጣ ላይ በመውጣት ረገድ ናታን
የመሪነቱን ደረጃ ሳይዝ ይቀራል ብላችሁ ነው። በእርግጥ በሽብርተኝነት ከተከሰሰው ከአንደርስ ብራይቪክ
ባይበልጥም።
ናታን በዚህች ዓለም በተፈጥሯዊዋ ውድ የዘር ግንድ ሃገሩ ኢትዮጵያ ሳይሆን በኖርዌ መወለዱ የሕይወት ዕጣው
ሆኖ እንጂ ፈቅዶ ያደረገው አይደለም። ናታን በፈረንጅ ሃገር መወለዱ ከእናትና አባቱ የስደት ታሪክ ጋር የተያያዘ
እንድምታ ቢኖረውም እንኳን እርሱ ራሱ - በራሱ ላይ የደነገገው ውሳኔ አይደለም። ናታን የዚህችን ዓለም ውዝግብና
ቅራኔን ያልተረዳ የሰባት ዓመት ጨቅላ ነው።
ታድያ የናታን ወላጆች - "ኖርዌን ለቃችሁ ውጡ" - ወይንም ደጎም - "ጉዳያችሁ እንደገና እስከሚታው ቆዩ"  -
እየተባለ ወዲህና ወድያ ሲያወዛውዟቸው ናታንንም አብረው ያንገላቱታል። ይህ ሁኔታ የየሰዉ ዓይን የሚበላቸውን
የወላጆቹን ቅስም ያደቃል። እንደ ኢትዮጵያዊ ሆነን ስንመለከተው ደግሞ ጨርሶ አንገትን አስደፊ ሆኖ እናገኘዋለን።

ትላንት የጀግናው የአጼ ቴዎድሮስ ልጅ አለማየሁ በምርኮ ተወስዶ እዚያው ባዕድ ሀገር መቀበሩ የሚያብከነክነን
የሃገር ልጆች - ዛሬ ደግሞ በሕጻኑ ናታን ማንነት ላይ ሲቀለድ ስናይ - ከዚህስ የበለጠ ምን ሌላ ቅጣት ሊደርስብን
ይችል ይሆን ብለን እንጨነቃለን። ነገሩ - ውስጠኛው ምስጢር ከገባን ማለቴ ነው።
ኖርዌ በርካታ ኢትዮጵያውያንን በአንቀልባ አዝላለች። ለአንዳንዱ በዜግነት ወረቀቱ ሳብያ ሉዓላዊነቷንም በመጠኑ
አቋድሳዋለች። ያው መቼም የዘይቱን ገንዘብ በጡረታው፣ በየእርዳታው፣ በድጎማውምና በሕክምናው ከመቦጨቅ
አንጻር የሚጠቅመው "የወርቅ ወረቀቱ" ማለት ነው። ለአንዳንዱ የመኖርያ ፈቃዱን በመስጠት የቆየ የልቡን መሻት
በዘይት እጆቿ አብሳለታለች። ይሄኛው "የብሩ ወረቀት" መሆኑ ነው። መልስ እስካሁን ያልተሰጣቸውም ከዚሁ
ከወርቁም ከብሩም ስጦታ ውጭ ናቸው። ኖርዌ ከዚህ ቀደም እንዲሰሩ ፈቅዳላቸው "የነሃሱን ወረቀት" አድላቸው
ነበር። ዛሬ እሱንም ቀምታቸዋለች። ምስኪኖቹ የሃገሬ ልጆች በሃሳብ ቆዝመው የኖርዌን ፖለቲካ መከታተልን እንደ
ሥራ አድርገውታል። እንግልቱና ውርደቱ ያዛላቸውም ውልቅ ሊሉላቸው ነው።
ጥቂቱ ሃቀኛ ፕሮቴክሽኑ የሚያስፈልገውም አብሮ ተጨፍልቋል። እነዚህኑ ሃቀኞች አበጥሮ አውጥቶ ለመንግስት
ማሳወቅ ደግሞ አልተቻለም። በአንድ በኩል የቆዩት ነባሮቹ የወርቅ ወረቀቱ የታደላቸው አብረው ተሰባስበው በሃቅና
ከአድልዎ ውጭ መምከር የሚችሉበትን "የወርቁን መብት" መጠቀም እስኪያቅታቸው ድረስ ተበታትነዋል። ምን
አዚም እንዳስነኳቸው አይታወቅም። በሌላ በኩል ደግሞ የፖለቲካ ሽኩቻው፣ በዚህም በዚያም መቃቃሩ፣ መቀናናቱና
ሃሚታው - "ኢትዮጵያ" - የሚለው የሃገራችን ሕያው ስም እንዲጠራ ለማይፈልጉት ሁሉ በሩን ክፍት አደረገው።
ታድያ እነሱም ክፍቱን በር ካገኙ ጨዋታውን ያውቁበታልና - ውስብስቡ ችግር መፍትሄ እንዲያገኝ የማድረግ
EthioLion
Ethiopia Will Prevail!EthioLion.Com
የተፈጥሮ ችሎታ ያላቸው መካሪ አዛውንት ሽማግሌ ረዳት    –  –  – - ሊሆኑ የሚችሉት ጉምቱዎቹና በሳሎቹ ሁሉ
እመሰብሰብያው ድርሽ እንዳይሉ በአንደርቢያቸው አግደዋቸዋል። የኛ ነገር ሲያስቡት ያሳዝናል። በዚህም በዚያም
መፍረስ።
እንደው በሃሳብ እየማለልኩኝ ሌላ ነገር መዘባረቁን ቀጠልኩኝ እንጂ የጽሁፌ ዓላማስ ስለ ስባት ዓመቱ ሕፃን ናታን
ለማውራት ነበር። የኖርዌ ባለስልጣኖች ስለናታን መንከራተት ሲናገሩ - "ጥፋተኞቹ ወላጆቹ ናቸው" - ይላሉ። መኖርያ
ፈቃድ ሳይኖራቸው ለምን ወለዱት ሲሉም ይሰማሉ። ወላጆቹ ይህን ያደረጉት ፋይዳ ያለውንም የሌለውንም ደንብ
እየጠቃቀሱ "የብር ወረቀቱን" ለማግኘት የሚያደረጉት ዘዴ ነው እስከማለትም ደርሰዋል። ሌሎች ትምህርት ያገኙ
ዘንድ ናታን መቀጣጫ ነው ማለታቸው ይመስላል። ታድያ እነሱስ ቢሆኑ ከዚህ ቀደም በልጆች ስም ፍቃዱን አድለው
እያለ አሁን ምነው ናታን ላይ ሲደርሱ ሸርተት አሉ። አሰራራቸው አንድ ወጥ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን አድልዎን
የሚያንጸባርቅ ይመስላል።
ለተገንጣዮች በርካታ ገንዘብ ያፈሰሰችው ኖርዌ የተገነጠሉት መክነው እያየች እንኳን አሆንም በውጭ ጉዳይ
ፖለቲካዋ ላይ አንድ ወጥ አስተዳደራዊ ክህሎትን የተለማመደች አትመስልም። ያስገነጠለቻቸው ሁሉ ሃገሪቱን ድንገት
ሲሞሉ ባየች ጊዜ ደንግጣ ይሆን እንዴ እንደ ናታን ባሉት ሕፃናት ላይ የበቀል ዱላዋን የሰነዘረችው? ስደተኞች
ውጡልን ብላ መቧረቅ የጀመረችውም ከዚህ የተነሳ ሳይሆን ይቀራል? በእርግጥ መች ኖርዌ ብቻ - መከረኛውን
ኢትዮጵያዊ ማሊም፣ ኬንያም፣ እሥራዔልም፣ የመንም፣ ሱዳንም፣ ሁሉም አገሮች እየገፉት ነው።
ናታን ምንም በማያውቀው ነገር እየተጎዳ ነው። በየጋዜጦች ላይ መውጣቱ ነገ ምናልባት ላያስደስተው ይችላል።
ጋዜጠኝነት ራሱ ፖለቲካ ነው። ጋዜጠኞቹ እያሸተቱ የሰውን ገበና የሚያብጠለጥሉት ሃገራቸውን ለመጥቀም ሊሆን
ይችላል። አንዳንድ ጋዜጠኞቹ አዛኝ መስለው በአጭር ምናምንቴ ጽሁፍ አጅበው ምስሉን በፊተኛው ገጽ የደነቀሩት
ስደተኛ - "እኔን ያየህ ተቀጣ" - እንዲል ሆኖ - ስደተኞችን ከመቀነስ አኳያ ለሃገራቸው ሙያዊ እገዛ እያደረጉ
እንደሆነስ - ማን ያውቃል። በእርግጥ አንዳንዶቹም ለሰብዓዊ መብት መከበር ሲቆሙ ይታያሉ። ብቻ በዚህም ወጣን
- በዛኛውም ወረድን - የሰው ቤት የሰው ነው። "የወርቁም፣ የብሩም የነሃሱም ወረቀት" ያው ወረቀት ነው። የነገው
ፖለቲካ ሊቀደው ይችላል። ወገኖቼ እባካችሁ ስደቱን ታግለን እናስቁም። ሃገር ከሁሉም በላይ ነች።
ታድያ "ናታን መጠቀምያ" ወይንስ "የስደቱ ፖለቲካ የጥቃቱ ሰለባ"? እስቲ እናንተም ፍረዱ።
እግዚአብሄር ናታንን ይረዳዋል። አንድ ቀን እንደ ሙሴ ሆኖ ከሃገሩ የተሰደደውን ኢትዮጵያዊ ሁሉ እየመራ ዳግም
ወደ ነጻይቱ የሚኒልክ ሃገር ይዟቸው ይመለስ ይሆናል። ምነው ዘገየን ናታን እስከሚያድግ መጠበቅ የለብንም         – -
ከዚያ በፊት መመለስ አለብን - ከተባለም በቆራጥነት ጸንተው ቆመው በሃቅ ከሚጩኹትና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት
ለድርድር ከማያቀርቡት ጋር እንደባለቅ። ከዚህ በላይ ደግሞ ወደ ፍጹሙ ሕይወት መርታ የምታደርሰንን መለኮታዊ
እውነትን ብቻ ምርኩዛችን አድርገን እንነሳ። "ኖርዌ ከገባሁ፣ ጀርመን ከመጣሁ፣ ፈረንሳይ ቤት ከገዛሁ - ሰላሳ ዓመት
ሞላኝ" - ብሎ ማውራቱ አያኮራም። አራዳነትም አይደለም። ታታሪነትንም አያሳይም። በተፈጥሯዊው የሃገር ሽታና
ወዝ ያልታበሰ የሕይወት ብኩንነትን እንጂ። አንድ ሰው ውጭ በቆየበት ዓመታት ልክ የተፈጥሮ ዜግነቱ ቆዳ
ይላጣል፣ ፀጋውም ወጨፎ እንደመታው ወይራ ይኮማተራል።
እግዚአብሄር ናታንን ይባርከው። ወላጆቹንም በፍቅር ዓይኑ ይመልከታቸው። ለኛም ማስተዋሉን አይንፈገን። አሜን

No comments:

Post a Comment