"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday, 20 June 2012

መለስ ዜናዊ ፕሬዝዳንት ቡሽና ቶኒ ብሌር


መለስ ዜናዊ ፕሬዝዳንት ቡሽና ቶኒ ብሌር
የወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ የአሜሪካ የቀድሞው ፕሬዘዳንት ቡሽና የእንግሊዝ የቀድሞው ጠ/ሚ ቶኒ ብሌር በለንዶን
የጠ/ሚር ቢሮ ሻይ ቢጤ ይዘው ስለ የሃገራቸው የህክምና ሳይንስ እድገት እየተጨዋወቱ ነው።
ቡሽ፡ ይገርማችኋል የአሜሪካ ሳይንቲስቶች ነፍስ ለመስራት ተቃርበዋል ማለት ይችላል፡፤ በቅርቡ በችካጎ ዩኒቨርሲቲ
የህክምና ማዕከል ውስጥ ሁለት እጅ የሌላት ሕጻን ተወለደች። ሳይንቲስቶቹ ባጋጣሚ ህጻኗ በተወለደችበት ቀን ከሞተች
ሌላ ሕጻን ላይ እጆችዋን ወስደው ገጥመውላት አሁን ሁለቱም እጆችዋ የተፈጥሮ እጅ ያህል ጤነኛ ናቸው። ብሎ
በመኩራራት ይናገራል።
ብሌር ፈገግ ብሎና በንቀት አስተያየት ቡሽን መልከት አድርጎ። እናንተ አሜሪካኖች ለካ ገና 18 ኛው ክፍለ ዘመን ላይ
ናችሁ?  እንግሊዝ ውስጥ አሁን አንተ የተደቅክበት እጅ መቀጠል የተሰራው በ18ኛው ክፍለ ዘመን ነው። ሲል
በመኩራራት ከተናገረ በኋላ እኛ አሁን በጣም ረቀናል። ከአንድ ሰው ሴል ዲ ኤን ኤ በመውሰድ ያንኑ ሴል በላብራቶሪ
ካባዛን በኋላ የሰውየውን ኮፒ ወይም ክሎን መፍጠር ችለናል በማለት ቡሽና መለስ በእንግሊዝ የህክምና ጥበብ
እንደሚደነቁ ሳይጠራጠር እጅግ ተኩራርቶ በፈገግታ ይመለከታቸዋል። እውነትም ቡሽ ማመን አቅቶት እራሱን
እየነቀነቀ አድናቆቱን ገለጸ። መለስ ግን ምንም ሳይገረም እንዲህ ሲል ተራውን መናገር ጀመረ።
መለስ እናንተ ኃያላን መንግስታት ለካ በሳይንስ ረገድ ገና ብዙ ይቀራችኋል። እኛ በርሃ እያለን የሰራነውን ገና የዛሬ 100
ዓመትም የምትሰሩት አይመስለኝም። ሲል
ብሌር  ደሞ ወያኔ በርሃ እያለች... ምን ሰራች ልትል ነው ? ሲል ጠየቀ።
መለስ እኛ በርሃ ሳለን ሁለት ያለ ጭንቅላት የተፈጠሩ ሰዎች አግኝተን ለአንደኛው ዱባ ገጥመንለት ስሙን አባ ዱላ
ስንለው ሌላኛውን ደግሞ ድንች ገጥመንለት አዲሱ ለገሰ ብለነዋል። ሁለቱም ዛሬ ድረስ በሙሉ ጤንነት ከኛው ጋ
ይገኛሉ በማለት ወያኔ በበርሃ የፈጸመውን የህክምና ሳይንስ ጥበብ ነግሮ አስደንቋቸዋል።

No comments:

Post a Comment