"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Monday, 16 July 2012

አጭር ወሬ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሌሉበት ፓርላማው በጀት እያፀደቀ ነው!     

ለወትሮው ሰኔ 30 የሚዘጋውና ግልፅ ባልሆነ ምክንያት ተራዝሞ የነበረው የፓርላማው በጀት ማፅደቂያ ቀን በዛሬው ዕለት ሐምሌ  9 2004ዓ.ም እየተካሄደ ነው።
በስብሰባው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አልተገኙም። ይህንን ወሬ እስካቀብላችሁ ድረስ “ከፓርላማ አባላቱም የት ሄዱብን?” ብሎ የጠየቀ የለም! ከአፈ ጉባኤውም የተሰጠ መግለጫ የለም። እኔማ በሆዴ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፓርላማ አባላቱ ጋር ተጣልተዋል እንዴ!? ብዬ እያሰብኩ ነው።
ቆይ ይቺን መረጃ ብጤ ላድርሳችሁ ብዬ ነው እንጂ! ተመልሼ ስለፓርላማው ስብሰባ ትንሽ የምናወጋው ሊኖረን ይችላል!
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መታመማቸውን እስካሁን ድረስ በየትኛውም የመንግስት ሚዲያ አልተገለፀም።
ወየውላቹ ድነው የመጡለት!
ወዮላችሁ!

No comments:

Post a Comment