"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 17 July 2012

[ሰበር ዜና] በአዲስ አበባ ሙስሊሞች እየታፈሱ ነው። ኦህዴዶች ጥያቄ አነሱ።



(ዘ-ሐበሻ)፡ በአዲስ አበባ በተለያዩ ወረዳዎች የሙስሊሙን እንስቃሴ እየመሩ ነው ወይንም ይደግፋሉ የተባሉ ወጣቶች በሰፈር ጥቆማ እየታሰሩ መሆኑን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ። የኦሮሞ/ሕወሐት ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) የሙስሊሞቹ ጥያቄ ካልተፈታ በኦሮሚያ ክልሎች የሚፈጠረው ነገር ያሰጋናል፤ መንግስት ባስሸኳይ መላ ያበጅለት የሚል ጥያቄ እያቀረበ መሆኑ ተጠቆመ።

ባለፈው ሳምንት የተወሰኑ ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶች መብታችን ይከበር ባሉ ከተገደሉ፣ ከተቀጠቀጡና ከታሰሩ ወዲህ የሙስሊሞቹ ጥያቄ ከዚህም በላይ ሊቀጥል ይችላል በሚል መንግስት በየሰፈሩ ወጣቶችን እያሰረ መሆኑን የጠቆሙት የዘ-ሐበሻ ምንጮች፤ እነዚህ ታሳሪዎች ወደ ክፍለ ከተማ ተወስደው ይታሰሩና ከተመረመሩ በኋላ የሚለቀቁት ተለቀው ቀሪዎቹ ከአዲስ አበባ ውጭ እየተወሰዱ በመታሰር ላይ መሆናቸውን አጋልጠዋል።
እንደ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጻ መንግስት የፈለገውን ቢያስርም የሕዝበ ሙስሊሙ እንስቃሴ እንደሚቀጥል የፊታችን አርብም ትልቅ ነገር ይጠበቃል። ሙስሊሙም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ድምጹን ያሰማል ተብሏል። በአሁኑ ወቅት ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ እስርቤቶች ውስጥ በርካታ ሙስሊሞች ታስረዋል።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ በሌሎች ተቃዋሚ ድርጅት አመራሮች ላይ እንደተሰራው ዓይነት (አኬልዳማ ድራማ) በሙስሊሙ ማህበረሰብ እንቅስቃሴ ላይም ተጀመረ። ምንጮቻችን እንዳጋለጡት ከሆነ መንግስት ቢለዋ በማስያዝ ሰዎችን ከኮምቦልቻና ከሌሎች ከተሞች ገንዘብ ከፍሎ ወደ አዲስ አበባ በማምጣት ቪዲዮ እየቀረጸ ነው። በቅርቡ በቲቪ በምናየው በዚህ ቪድዮም ሰላማዊውን የሙስሊሙን ትግል ቢለዋ የያዙ በማስመስል “ሕዝቡን ሊጨርሱት ሊያስጨርሱት ነው” ሊል ተዘጋጅቷል።
ከታሰሩትና ታስረው ከተፈቱት መካከል አንዳንዱን በባዶ ወረቀት ላይ ከታች ምንም ሳይጻፍበት በግድ እንዲፈርሙ መታዘዛቸውን የሰሙ አስተያየት ሰጪዎች በቅርቡ በምናየው አኬልዳማ መሰል አስፈሪ የወያኔ የሆረር ፊልም ላይ ራሱ ወያኔ የሚጽፈውን ለክስ የሚመች ጽሁፍ እናነባለን ብለዋል።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ ኦህ ዴድ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ባለስልጣናት አቶ መለስ ከታመሙ በኋላ አፍ ማውጣት ጀምረዋል። እንደነዚህ ባለስልጣናት አገላለጽ “ኦሮሚያ ብዙ ሙስሊሞች የሚኖሩባት ክልል ነች። በአዲስ አበባ የተነሳው ጥያቄ በቶሎ ካልተመለስ በኦሮሚያ ክልል የሚስፋፋው እንቅስቃሴ ለደህንነት የሚያሰጋ በመሆኑ በአስቸኳይ የፌደራል መንግስቱ መፍትሄ ሊያፈላልግለት ይገባል” እያሉ ነው። “በኦሮሚያ ሙስሊሙ ከተነሳ ከባድ ችግር ውስጥ እንገባለን” እያሉ ያሉት ኦህዴዶች የሚፈለገው ተከፍሎ የሙስሊሙ ጥያቄ እንዲመለስ እየጠየቁ መሆናቸውን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው የውስጥ አዋቂ መረጃ አመልክቷል።

No comments:

Post a Comment