"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday, 18 July 2012

አቶ መለስ መግለጫ ሳይሰጡ ቀሩ።



(ዘ-ሐበሻ) አቶ መለስ ዜናዊ በከፍተኛ ሕመም ላይ መሆናቸውን ሲደብቅ የቆየው የኢትዮጵያ መንግስት ከሰሞኑ በምክትል ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካኝነት “አቶ መለስ ህመማቸው የሚያሰጋ አይደለም፤ በጥቂት ጊዜያት ወደ ሥራቸው ይመለሳሉ” የሚል መግለጫ መሰጠቱ ይታወሳል። ትናንት የመንግስት ባለስልጣናት አቶ መለስ ዜናዊ ዛሬ መግለጫ እንደሚሰጡ የተገለጸ ቢሆንም ተሰርዟል። የውጭ ሃገር ሚዲያዎች ሳይቀር መለስ በአስጊ ሁኔታ ላይ እንዳሉ በመዘገብ ላይ ናቸው።
ይህን ተከትሎ የአቶ መለስ ህመም እጅግ አደገኛነቱን ያሳያል የሚሉት ታዛቢዎች እንዳሉ ሆኖ ዛሬ
በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ለሥርዓቱ ቅርብ የሆነው ሪፖርተር ጋዜጣ እያስተዛዘነ በጻፈው ዜና አቶ መለስ በዶክተሮቻቸው ላልተወሰነ ግዜ እረፍት እንዲያደርጉ ታዘዋል ብሏል። እንደ ሪፖርተር አዛኝ ዘገባ ከሆነ “ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ፣ ወደ አገራቸው ሲመለሱም በቶሎ ሥራ እንደማይጀምሩ ታውቋል፡፡ ለ21 ዓመታት ያለዕረፍት ከፍተኛ የአገር ኃላፊነትን ሲወጡ የቆዩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የሕመማቸውም ምክንያት ካለባቸው የሥራ ጫና ብዛት የመጣ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተወሰኑ ጊዜያት ካለባቸው ከባድ ኃላፊነት ርቀው ዕረፍት እንዲያደርጉ በሐኪሞቻቸው መመከራቸውን ምንጮች አክለው ገልጸዋል፡፡” ብሏል።
አዲስ አበባ እንደገቡ ሲወራ የነበረው አቶ መለስ አሁንም በውጭ ሃገር ህክምና ላይ እንዳሉና በቅርብ ጊዜ ወደ ሃገር ቤት እንደሚመለሱ የዘገበው ሪፖርተር በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ግርማ ብሩ፣ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ሥዩም መስፍን፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦንና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚታከሙበት ቦታ ሄደው ከጐበኟቸው ባለስልጣናት መካከል ይጠቀሳሉ ብሏል። ይህን የሰሙ አስተያየት ሰጪዎች አቶ መለስ መንግስት እንደሚለው እረፍት ብቻ የሚያስፈልገው በሽታ ከያዛቸውና በሽታውም ቀላል ከሆነ እነዚህ ባለስልጣናት እንዴት ረዥም አገር አቋርጠው ጥየቃ ሊሄዱ ቻሉ? ሲሉ ይጠይቃሉ። አቶ መለስን ሚስታቸው በፓርላማ ለመገኘት ወደ አዲስ አበባ ስትመጣ እንኳ ከአጠገባቸው ያልተለዩት አቶ ብርሃኔ ገብረክርስቶስ መሆናቸውንም ሪፖርተር ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስት ፓርላማውን አቶ መለስ ንግግር አድርገው እንደሚዘጉት መግለጫ የሰጠ ቢሆንም፤ አቶ መለስን የሚታከሙበት ቦታ ጠይቀው የተመለሱት አባዱላ ገመዳ አማካኝነት ፓርላማው ካለ መለስ “ቡራኬና ስድብ” ሳይዘጋ ቀርቷል።
በሌላ በኩል ወላጅ እናቱን ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ለመጎብኘት ወደ ቤተ መንግስት እንዳይገባ በደህንነት ሚ/ሩ ጌታቸው አሰፋ መከልከሉን ከዚህ ቀደም በዘ-ሐበሻ ላይ የተዘገበው የሟቹ ክንፈ ገ/መድህን የጀመሪያ ልጅ “መለስ መጀመሪያ እናቴን አገባ ቀጥሎ አባቴን አስገደለ፤ መለስ ዜናዊን እፋረደዋለሁ”ብሎ በአደባባይ ከተናገረ በኋላ መለስን እንዳይበቀል፤ ሽማግሌ ሆነው ሲያግባቡት የነበሩት እነዚሁ መለስን የታመመበት ሃገር የጠየቁት ባለስልጣናት እንደነበሩ ይታወሳል።
ዜናውን ላላነበባችሁት እዚህ ጋር ተጭነው እዩት።

No comments:

Post a Comment