"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 17 July 2012

የኢትዮጵያ ሕዝብ ይወቅልኝ ለሠራሁት ፊልም ምንም ክፍያ አላገኘሁም” ፍልፍሉ



(ዘ-ሐበሻ) ኮሜዲያን ፍልፍሉ በዚህ ሳምንት በሰሜን አሜሪካ የተሠራጨውን አዲሱን “የዜግነት ክብር” የኮሜዲ ፊልም “ኢቫንጋዲ ፕሮዳክሽን ለኔ ምንም ዓይነት ክፍያ ሳይከፍለኝ የወጣ በመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቅልኝ እፈልጋለሁ። ሕብረተሰቡም ይህንን ሲዲ እንዳይገዛ ጠየቀ። የኢቫንጋዲ ፕሮዳክሽን ባለቤት ዳንኤል ታምሬ በበኩሉ እኛ ሲዲውን የገዛነው ከሌላ ሰው ነው ሲል ለዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ አስታወቀ።
ኮሜዲያን በረከት በቀለ ወይም እኛ የምናውቀው ስሙ ፍልፍሉ “እኔ ወደ አሜሪካ መምጣቴን ተከትሎ ከ እኔ እውቅና ውጭ ሲዲው ለገበያ መውሉን ሳይ በጣም አዝኛለሁ።” ካለ በኋላ ማህበረሰቡ ይህን ሲዲ ባለመግዛት ይተባበበር ብሏል። ፍልፍሉን በቪዲዮ ቃለ ምልልስ አድርገነዋል ይመልከቱት። ከቪዲዮው ቀጥሎ ደግሞ የኢቫንጋዲ ፕሮዳክሽን ባለቤት የሰጡንን አስተያየት ያንብቡና ፍርዱን እናንተ ስጡ።

ፍልፍሉ ለዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ ብሶቱን ካሰማ በኋላ አሁን ታትሞ የወጣውን “የዜግነት ክብር” ሲዲ ያሳተመው ኢቫንጋዲ ፕሮዳክሽን ባለቤት አቶ ዳንኤል ታምሬ ጋር ወደ አትላንታ ደውለን ነበር። አቶ ዳንኤል በቅድሚያ ፍልፍሉ ለዚህ ሲዲ ክፍያ እንደተሰጠው የሚያረጋግጥ የፊርማ ማስረጃ እንዳለውና ካለማስረጃ ምንም ዓይነት ሥራ እንደማይሰሩ ገለጸ። እኛም “ፍልፍሉ ክፍያ የተፈጸመለትን ማስረጃ ልትሰጠን ትችላልህ ወይ?” ስልነው “በሚገባ ብሎ የውሉን ማስረጃ በኢሜይል እንደሚልክልን ነገረን”። ከደቂቃዎች በኋላ አቶ ዳንኤል ወደ ዘ-ሐበሻ በመደውል “የውሉን ወረቅት ለናንተ መስጠት አልችልም። ጠበቃዬ አትስጥ ብሎኛል” ካለ በኋላ ቀጥሎም “ሲዲውን እኛ የገዛነው አቶ ተስፋዬ ፈጠነ ካሳና እንድሪያስ መኮንን ከተባሉ ሰዎች ነው” ሲል ተናግሯል።
“አቶ ተስፋዬ ፈጠነ እና አቶ እንድሪያስ እነማን ናቸው?” የሚል ጥያቄ አስከተልን ዳንኤልም “እንድሪያስ የፊልሙ ፕሮዲውሰር ነው፤ ፊልሙ ላይም ከፍልፍሉ ጋር ሰርቷል። አቶ ተስፋዬ ደግሞ ከእንድሪያስ ጋር የተዋዋለ ሰው ነው። እኛ ከነሱ በሕጋዊ መንገድ ነው የገዛነው። እነርሱም ለፍልፍሉ እንደከፈሉት ነው የምናውቀው። ምክንያቱም እንዴት አንድ ሰው ምንም ሳይከፈለው ከ30 ደቂቃ በላይ ቪድዮ ሊቀረጽ ይችላል?። ስለዚህ ፊልም ጉዳይ ማስረጃውን ከፈለግክ ወደ አዲስ አበባ አቶ እንድሪያስ እና ተስፋዬ ፈጠነ ጋር መነጋገር ትችላለህ። በኛ በኲል በሕጋዊ መንገድ ፊልሙን የገዛነው ከነሱ ነው” ሲል ተናግሯል።
ለአቶ ተስፋዬ ፈጠነ ና አቶ እንድሪያስ መኮንን ወደ አዲስ አበባ ደውለን ልናገኛቸው አልቻልንም። ሃሳብ ካላቸው ዘ-ሐበሻ ድረ ገጽን በማንኛውም ሰዓት ማስረጃምን ማቅረብ ይቻላል።

Share It

  •  

No comments:

Post a Comment