"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Friday 13 July 2012

የወያኔው ካንጋሮ ፍርድ ቤት እስክንድር ነጋ ላይ 18 ዓመት፣ አንዷለም አራጌ ላይ እድሜ ልክ እስራት ፈረደ




(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ አርብ በአዲስ አበባ የተሰየመው የወያኔው ካንጋሮ ፍርድ ቤት በነ አንዷዓለም የክስ መዝገብ ታስረው በሚገኙትና በስደት ላይ ባሉት፤ ጋዜጠኞች፣ ነጻ አሳቢ ዜጎችና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ላይ የፍርድ ውሳኔውን አስተላለፈ። ከገዢው ስርዓት ገለልተኛ ያልሆነው ካንጋሮው ፍርድ ቤት በታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ 18 ዓመት እስራት ፈርዶበታል።
ከአዲስ አበባ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ባስተላለፉት ዘገባ መሠረት በሰላማዊ መንገድ በሃገር ቤት እየታገለ የሚገኘው የአንድነት ፓርቲው አቶ አንዷለም አራጌ፣ የግንቦት ሰባት መሪዎች ዶክተር ብርሃኑ ነጋና አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እና የኢሳት ቴሌቭዥን እና ራዲዮ አዘጋጅ ፋሲል የኔ አለም ላይ በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ የወሰነው የካንጋሮው ፍርድ ቤት፤ አቶ መለስ ዜናዊን በአለም ሕዝብ ፊት አምባገነን መሪ እንደሆኑ ያስታወሳቸውና ያዋረዳቸው ጋዜጠኛ አበበ ገላው 15 ዓመት፣ በዋሽንግተን ዲሲ የአዲስ ድምጽ ራድዮ አዘጋጅ አበበ በለው 15 ዓመት እስራት በሌሉበት ፈርዷል፡፡
በቀድሞዎቹ የአዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጆች አብይ ተክለማርያም እና መስፍን ነጋሽ ላይም የ8 ዓመት እስራት የበየነው የካንጋሮው ፍርድ ቤት በአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መሪ ኦባንግ ሜቶ ላይ 18 ዓመት፣ በአቶ ጸጋ ስላሴ ዘለሌ፣ በአቶ ውቤ ሮቤና በአቶ ናትናኤል መኮንን ላይም የ18 ዓመት እስራት ፈርዷል።
ከፍርዱ በኋላ ለዘ-ሐበሻ የደረሱ አስተያየቶች እንደሚጠቁሙት “ድሮም ከወያኔ ፍርድ ቤት የሚጠበቅ ፍርድ ነው የተሰጠው። እነዚህን ነጻ አሳቢ ዜጎች መንግስትን ስለተቃወሙ ብቻ አሸባሪ ማለቱ አስነዋሪ ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ፍርድ ተጓደለ ብሎ ሊነሳና ሊሟገትላቸው ይገባል”
ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ “እነ እስክንድር ነጋ የሕሊና እስረኞች እንጂ አሸባሪዎች አይደሉም:: ፍርድ ቤቱ ይህን አይን ያወጣ ፍርድ እንደሚሰጥ ቀድሜ አውቄዋለሁ። ለምን እስካሁን ፍርዱን ማጓተት እንዳስፈለገውም አልገባኝም” ብለውናል።



No comments:

Post a Comment