"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 10 July 2012

ኃይሌ ገብረስላሴ ኤርትራ ኤንባሲ ምን ይሰራል!?


ኃይሌ ገብረስላሴ ኤርትራ ኤንባሲ ምን ይሰራል!?
ትላንት ሐምሌ 2/ 2004 ዓ.ም ታዋቂው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ኬኒያ በሚገኘው ኤርትራ ኤንባሲ መታየቱን ናይሮቢ የሚገኙ ኤርትራዊ ወዳጆቼ ነገሩኝ። ኃይሌ ገብረስላሴ ኤርትራ ኤንባሲ ምን ይሰራል!?

በነገራችን ላይ እንዲህ አይነት የጭምጭምታ ወሬዎችን መናቅ አይገባም። ከዚህ በፊት ራሱ ኃይሌ ገብረስላሴን ጨምሮ ሌሎችም ራሳቸውን “ሽማግሌ” ብለው የሚጠሩ ግለሰቦች ተሰባስበው በቃሊቲው እስር ቤት ሲመላለሱ ነበር። የሚል ጭምጭምታ በሰማን በማግስቱ ነው ነገሩ ሽምግልና መሆኑ የተሰማው። ማን ያውቃል አሁንም ኃይሌ ኤርትራ ኤንባሲ በታየ በነጋታው አቶ ኢሳያስ እና አቶ መለስ ሊሸማገሉ ነው የሚል ዜና እንሰማ ይሆናል።

እንግዲህ ዝርዝሩን ወደፊት የምንሰማው ቢሆንም፤ ለጊዜው ግን እኔ ነገር መደበቅ አይሆንልኝምና እንሆ ሹክ ብያችኋለሁ። ኃይሌ ገብረስላሴ  በኤርትራ ኤንባሲ ትላንት ታይቶ ነበር። መቼም “የኢትዮጵያ ኤምባሲ መስሎኝ ነው” አይለንም። ታድያ እንዴት እዛ ሊገኝ ቻለ?

ይቺን ያህል እኔ ወሬ ካቀበልኩ፤ እንዴት? ለምን? ከየት? ወዴት? የሚሉትን  ጠለቅ ያሉትን ግምቶች ለፕሮፌሽናል ገማቾች እንተዋለን!

ኃይሌ ገብረስላሴስ የተመለከቱት ወዳጆቼ ጠርተው ሰላምታ ሰጥተውት እሱም “ታድያስ ሰላም ናችሁ” ብሎ አፀፋውን የሰጣቸው ሲሆን ከሁለት አማርኛ ተናጋሪ ሰዎች ጋ እንደነበረም ሹክ ብለውኛል!

No comments:

Post a Comment