ጸሐዬ ዮሐንስ የኢትዮጵያ ባንዲራን ይዞ መድረክ ላይ አለቀሰ
(ዘ-ሐበሻ) ውድ አንባቢዎች ከዳላስ ያገኘናቸውን መረጃዎች በየሰዓቱ ወደናንተ በቪድዮ እያደረስን ነው። አሁንም አዲስ ነገር አግኝተን ልናካፍላችሁ ነው። ተወዳጁ ድምጻዊ ጸሐዬ ዮሀንስ በዳላስ በተደረገው የኢትዮጵያውያን ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ላይ በመገኘት በሕዝብ ዘንድ ክብርን ከተጎናጸፉ በርካታ አርቲስቶች መካከል አንዱ ነው። ጸሐዬ አርብ እለት በኢትዮጵያን ቀን ላይ እንዲሁም ቅዳሜ በመዝጊያው ምሽት ላይ “እምዬ ኢትዮጵያ እንዲህ ሆና አትቀርም” የሚለውን ዘፈኑን አቅርቦ ነበር። በመዝጊያው ዕለት በተመልካቹ የኢትዮጵያ ባንዲራ ልክ ‘እምዬ ኢትዮጵያ እንዲህ ሆና አትቀርም” የሚለውን ዜማ ሲጫወት ተሰጠው። ጸሀዬ ዘፈኑን እየዘፈነ እምባውን መቆጣጠር አልቻለም። ባንዲራውን በ እጁ ይዞ እያለቀሰ ዘፈኑን ለመጨረስ ተገዷል። በርከት ያሉ ተመልካቾችም ስሜታቸውን መቆጣጠር ተስኗቸው ሲያለቅሱ ነበር። የእምዬ ኢትዮጵያ ፍቅር አይደለም እምባ ደም ያስፈስሳል። የጸሐዬን ለባንዲራው ያለውን ፍቅር ብዙዎች በአድናቆት ሲያወሩበት ነበር። ጸሐዬ በኢትዮጵያን ቀን ላይ የዘፈናት “እምዬ ኢትዮጵያ እንዲህ ሆና አትቀርም” ዜማ በዘ-ሐበሻ ቪድዮ ተይዛለች፤ ይመልከቷት። ጸሐዬን እናመሰግናለን።
No comments:
Post a Comment