"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Monday 9 July 2012


“እናቴ እጄ ላይ ነው በጥይት ተመትታ የሞተችብኝ” ” ” ዝነኛው ተወዛዋዥ አብዮት ደመቀ

(ዘ-ሐበሻ) – ዝነኛው የቀድሞው የሃገር ፍቅር ተወዛዋዥ እና የውዝዋዜ አሰልጣኝ አብዮት ደመቀ ወደ አሜሪካ መጣ። በመጣ በሁለተኛው ቀንም ዳላስ በተደረገው የኢትዮጵያውያን የ እግርኳስ እና የባህል ዝግጅት ላይ ተገኝቶ የኢትዮጵያውያን ቀን አርብ ጁላይ 6 ቀን 2012 ሲከበር ‘ለኢትዮጵያ ሕዝብ የምናገረው አለኝ’ በሚል በእናቱ ላይ የአቶ መለስ ወታደሮች የፈጸሙትን ግድያ በአደባባይ ተናግሯል። “በቅድሚያ ከእናንተ መካከል ዛሬ እንድገኝ ላደረገኝ እግዚአብሄር፤ እመብርሃን ምስጋና ይድረስ።…ካእናቴ በጥይት ተመትታ የሞተችው እጄ ላይ ነው” ሲል አጋልጧል። “የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም እንደሚባለው” በ1993 ሚያዝያ 10 በአራት ኪሎ አደባባይ በአብዮት እናት ላይ ይህን ድርጊት የፈጸሙ ደም ያለባቸው ሰዎች ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲው የአላሙዲ (ወያኔ) ስፖርት ፌስቲቫል ላይ እንዲካፈል መጠየቃቸው እንዳስገረመው መድረክ መሪው አበበ በለው ተናግሮ ነበር። እኛ ከምንገልጸው ዘ-ሐበሻ ከስታዲየሙ ውስጥ ሆና የቀረጸችው ቪድዮው ትናገር።



No comments:

Post a Comment