"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday 11 July 2012

ሌላኛዋ ዓለም ደቻሳ በሳዑዲ አረቢያ ፖሊስ ስትሰቃይ፤ እኛ ስንዋረድ የሚያሳይ ቪድዮ ተሰራጨ




Wednesday, July 11th, 2012 | Posted by zehabesha

(ዘ-ሐበሻ) በሊባኖስ ተሰቃይታ ለህልፈተ ሞት የበቃችው የዓለም ደቻሳ ሃዘን ሳይለቀን ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊትን የሳዑዲ አረቢያ ፖሊሶች ሲያሰቃዩአት የሚያሳይ ቪድዮ በዩቲዩብ በኩል ተለቀቀ። ከአሰሪዎቿ ስቃይ አምልጣ ለመሄድ ስትል፤ አሰሪዎቿ ለፖሊስ እንደጠቆሙ የገለጸው ከሳኡዲ የመጣው የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ሪፖርት ፖሊስ ልጅቷን በ እጁ ሲያስገባ ልክ እንደ እንስሳ መኪና ውስጥ ለመጫን ክብሯን በመዳፈር ሲያሰቃዩአት ቪዲዮው ያሳያል። በኃይለ ሥላሴ ዘመን የሳዑዲ መንግስትም ሆነ ሕዝቡ ለኢትዮጵያውያን ልዩ ክብር እንደነበረው ታሪክ ያወራ ነበር። አሁን ግን ኢትዮጵያውያን በየቦታው እየተዋረዱ ይገኛሉ። በሳዑዲ እስር ቤት ብቻ አልፎልኝ ቤተሰቦቼን አሳልፋለ ብለው ከሃገር የወጡ ኢትዮጵያውያን በሺህዎች ይቆጠራሉ። የአ ዕምሮ በሽተኛ የሆኑ፣ የታመሙ፣ ተገደው የተደፈሩ ሴት እህቶቻችን ቁጥር ብዙ ነው። የሳዑዲ ፖሊሶች ኢትዮጵያዊቷን ሲያሰቃዩዋት የሚያሳየው ቪድዮ እጃችን ገብቷል። የ እህታችንን ማንነት ዘ-ሐበሻ እያጣራች ነው።
ላልሰማ አሰሙ፤ እንጩህ፣ እንደ ኢትዮጵያዊ ክብራችንን ለማስመለስ እንነሳ!!
>


No comments:

Post a Comment