"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Monday 9 July 2012

“የኢትዮጵያ አንድነት ለዘላለም ይኖራል”


Sunday, July 8th, 2012 | Posted by zehabesha
“የኢትዮጵያ አንድነት ለዘላለም ይኖራል” – አርቲስት ማህሙድ አህመድ
37
Share
(ዘ-ሐበሻ) የትዝታው ሙዚቃ ንጉሥ ማህሙድ አህመድ በዳላሱ የኢትዮጵያውያን የ እግርኳስ ውድድር ላይ በመገኘት በኢትዮጵያን ቀን ላይም እንደዚሁም በመዝጊያውም እለት ድንቅ ብቃቱን ያስመሰከረበትን የሙዚቃ ሥራዎቹን ለሕዝብ አቅርቧል። በዳላሱ የእውነተኞቹ ኢትዮጵያውያን ስፖርት በዓል ላይ በመገኘትም ከሕዝብ ክብርን አግኝቷል፡፤ ድምዳዊው ዘፈኖቹን አቅርቦ ሲጨርስ የብሄራዊ ስሜትን በሚያነቃቃ መልኩ የተናገራቸው ንግግሮች በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ አድናቆትን አግኝቷል። “ኢትይጵያ ለዘላለም ትኑር፤ የኢትዮጵያ አንድነት ለዘላለም ይኖራል” ሲል ተናግሯል። ቀጣዩ ቪድዮ ይህንን ያሳየናል። ዘፈኑን ዘፍኖ ሲጨርስ ንግግሩን ያድምጡት። ቪድዮውን የቀረጸው የዘ-ሐበሻ ድረገጽ ዋና አዘጋጅ ሔኖክ ዓለማየሁ ነው። መልካም እይታ፡ ማህሙድን ለወርቃማ ቃላቶቹ እናመሰግናለን።



No comments:

Post a Comment