"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Thursday 12 July 2012

የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በዝናብ ተጥለቀለቀ


የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በዝናብ ተጥለቀለቀ

በዝናብ ተጠለቀለቀ

ከፍተኛ ወጭ ተመድቦለት ግንባታውም በዚህ አመት የተጠናቀቀው እና ምርቃቱም በታላላቅ የአፍሪካ መሪዎች ባሉበት ተመርቆ በስራ ላይ የዋለው የአፍሪካ ህብረት ማእከል በትላንትናው እለት ምሽት በጣለው ከፍተኛ ዶፍ ዝናብ የህብረቱ አዳራሽ መጥለቅለቁ የደረሰን ዜና ዘገባ ያመለክታል ። ከ$200፣000 የአሜሪካን ዶላር ያወጣው እና የቀድሞውን ንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘ-ኢትዮጵያ መሰረታዊ ታሪክ ያጠፋ ከመሆኑም በላይ በመታሰቢያነት ከታሰበ ሊሰራላቸው ከሚገባቸው የሚገባው ሰዎች መካከል ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ፣የኬንያው ጆሞ ኬኝያታ  እና የግብጹ ጋማል አብዱል ናስር መሆን ሲገባቸው በምትኩ የአፍሪካ የአንድነት ታጋይ ተብለው የተሰየሙት“  በአፍሪካ አንድነት ከፍተኛ ትግል ላደረጉት በዶ/ር  ክዋሚ ኑክሩማህ” ስም ሃውልት ተሰርቶ መታሰቢያ እንዲሆነላቸው የተደረገው ይሄው ሃውልት በቻይናውያን ትብብር ተሰርቶ መጠናቀቁን ባለፈው ጃንዋሪ 28 ቀን 2012 የቻይናው የፖለቲካ አድቫይሰር  ጂያ ቂንጊል   በተገኙበት ተመርቆ ለስራ መብቃቱ ይታወሳል ::


ይሄው ህንጻ ለመገንባት እንደ ኤሮጳውያን አቆጣጠር በ2009 ተጀመሮ በ2012 የተጠናቀቀው ህንጻ የኢትዮጵያን መንግስት ያስደሰተ ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያን ህዝብ ደግሞ በተወሰነ በኩል ማስቆጣቱን እና የታሪክ አሻራችንን ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አበላሹት የሃይለስላሴ የአፍሪካ ህብረትን መስራችነት እና እስከዛሬ ድረስ ግንባር ቀደም የአንድነት ታጋይ መሆናቸውን አጠፋው በማለት ከፍተኛ ወቀሳ ከመሰንዘራቸውም በላይ በፓርላማ በሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥያቄ ቀርቦላቸው በጠ/ሚንስትሩ የተሰጠው ምላሽ የታሪክ መጣረስ እና ምንም የማይታመን  ከእውነትም ታሪክን ህዝብን እና አገርን ለመለያየት እና ለመገነጣጠል የመጣ መንግስት ነው የሚል ስያሜ ሊያሰጠው እንደቻለ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው ።ይኸው ህንጻ ከተገነባ ጊዜ ጀምሮ ገና የስድስት ወር እድሜ ጊዜ ያለጠገበ ከመሆኑም በላይ እንኳንስ ውሃ ይገባበታል ተብሎ ሊታሰብ የሚነፍስ አየር ይነፍስበታል ተብሎ የማታሰብ እና የማይታለም ነው ያሉት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የዚህ መንግስት ስራ ከሚሰራቸው ስራዎች ጥራት ማነስ የተነሳ በግንባታዎች ላይ የገንዘብ ቁልል መስጠት እንጂ መሰረታዊ የሆነ ጥናታዊ ስራዎችን ለማካሄድ እንደማይችሉ ይህ ለሁለተና ጊዜ የደረሰ ከፍተኛ ወጭ ከወጣባቸው ትልቅ ፕሮጀክት አንዱ ሲሆን ከዚህ ቀደም ለኤሌትሪክ ማመንጫ ግንባታ ይውላል ተብሎ የነበረው የጊቤ ቁጥር ሁለት ግድብ መፍረስ አንዱ መሆኑ ይታወቃል ።

No comments:

Post a Comment