"Food is nothing without freedom! We Need Freedom
”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!
Tuesday, 26 June 2012
ቀነኒሳ በኦሊምፒክ መሳተፍ የሚያስችለውን ሰዓት አስመዘገበ 4
Monday, June 25th, 2012 | Posted by zehabesha
ቀነኒሳ በኦሊምፒክ መሳተፍ የሚያስችለውን ሰዓት አስመዘገበ
4
Share
ካጋጠመው ጉዳት በኋላ በኦሊምፒክ በአሥር ሺ ሜትር ሦስተኛ የወርቅ ሜዳሊያ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኘው ቀነኒሳ በቀለ በእንግሊዝ በርሚንግሃም የተደረገውን ውድድር በዚህ ዓመት በርቀቱ ከተመዘገቡ ፈጣን ሰዓቶች መካከል ሦስተኛውን በማስመዝገብ ማሸነፍ ችሏል። ሰዓቱ በለንደኑ ኦሊምፒክ መሳተፍ የሚያስችለው ነው። ከውድድሩ በኋላ በሙሉ ብቃቱ ላይ እንደሚገኝ መግለጹን አሶሸዬትድ ፕሬስ ዘግቧል።
የአምስትና የአሥር ሺ ሜትር የኦሊምፒክ ሻምፒዮና እና የርቀቶቹ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቱ ቀነኒሳ በቀለ በዓመቱ በርቀቱ ያደረገውን የመጀመሪያውን ውድድር በ27 ደቂቃ ከ02 ነጥብ 59 ሰከንድ በማጠናቀቅ በለንደን ኦሊምፒክ ተሳታፊ መሆን የሚያስችለውን ውጤት ማስመዝገብ ችሏል።
«ለዓለም የተለየ ነገር እንደማሳይ ተስፋ አደርጋለሁ። አሁን በእርግጠኝነት ወደ ሙሉ ብቃቴ ተመልሻለሁ» ብሏል ለሁለት ዓመት ያህል በጉዳት ላይ የቆየውና የሰላሳ ዓመቱ ቀነኒሳ።
ለለንደኑ ኦሊምፒክ ሚኒማ ለማሟላት በተደረገው በዚህ ውድድር ላይ ከተሳተፉት ኢትዮጵያውያን መካከል ታናሽ ወንድሙ ታሪኩ በቀለ ሁለተኛ ሲወጣ ገብረእግዚአብሔር ገብረማ ርያምና ስለሺ ስህን ሦስተኛና አራተኛ ደረጃ ይዘው አጠናቅቀዋል።
«ውድድሩ በጣም ጥሩ ውድድር ነበር። በፍጥነት እንዳልሮጥ የቦታው ነፋሻማ አየር አግዶኛል። ለኦሊምፒክ ቡድኑ መመረጥ የሚያስ ችለኝን ሰዓት በማስመዝገቤ ተደስቻለሁ» በማለት ተናግሯል።
አትሌቱ ባለፈው መስከረም ወር በብራሰልስ በርቀቱ የተደረገውን ውድድር በ26 ደቂቃ ከ43 ነጥብ 16 ሰከንድ በመሮጥ የዓለም ፈጣን ሰዓት ማስመዝገብ ችሏል። ይህ ሰዓት በኦሊምፒኩ ተሳታፊ መሆን የሚያስችለው ቢሆንም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አትሌቱ በአዲሱ የአውሮ ፓውያን ዓመት ሚኒማ ማሟላት እንዳለበት በማሳ ወቁ በበርሚንግሃሙ ውድድር ይህንን ማሳካት ችሏል። «ማሸነፍና ሰዓቱ ለእኔ አስፈላጊዎች ነበሩ። በኦሊምፒክ ቡድኑ ለመካተት ፈጥኜ መሮጥ ነበረብኝ።ይህንንም አድርጌዋለሁ» ብሏል።
አክሎም «ለኦሊምፒኩ ለመዘጋጀት በቂ ጊዜ አለኝ። በተለይም በፍጥነትና ፅናት ላይ ትኩረት አድርጌ መሥራት እፈልጋለሁ» ብሏል። ቀነኒሳ ከሁለት ሳምንት በኋላ በፈረንሳይ ፓሪስ በሚካሄደው የሳምሰንግ ዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ እንደሚካፍልም ታውቋል።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment