"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Sunday 24 June 2012

የርዕዮት አለሙ ይግባኝ መታየት ጀመረ

Posted by admin on June 24, 2012 0 Comment

በአቤ ቶኪቻው

ትላንት ሰኔ 15 2004 ዓ.ም የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ይግባኝ ታይቶ ነበር። በይግባኟም “ከግንቦት ሰባት ጋር ወይም ከኤርትራ መንግስት ጋር አሲራለች ለሚለው ክስ ማስረጃ አልቀረበብኝም።” ብላ የተከራከረች ሲሆን ከኢትዮጵያ ሪቪው ድረ ገፅ ጋር ያላት ግንኙነት የጋዜጠኝነት ግንኙነት መሆኑን ለዚህም ክፍያ እንደተከፈላት እና ከውጪ ሀይሎች የገንዘብ ድጋፍ አግኝታለች የተባለው ይሄው የሰራችበት ክፍያ መሆኑን አስረድታለች። ያገኘችው ክፍያም አንድ ጊዜ 1500 ብር እና ሌላ ጊዜ ደግሞ 2100 የኢትዮጵያ ብር መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ተናግራለች።
 አቃቤ ህግ በበኩሉ ሌሎች አብረዋት የተከሰሱ ይቅርታ መጠየቃቸውን አውስቶ ርዮት አለሙ አዲሳባን ለመበጥበጥ ከውጪ ሀይሎች የገንዘብ ድጋፍ ማግኘቷን ደግሞ ለመናገር ሞክሯል።
 አሽሟጣጮችም በበኩላቸው ርዮት አለሙ በድምሩ 3600 ብር አግኝታ አዲሳባን የምትበጠብጠው እንዴት ነው? ሲሉ የጠየቁ ሲሆን ልጅቷ ጠጪ እንኳ ብትሆን “አንድ ምሽት በገንዘቡ ጠጥታበት በሞቅታ ከተማዋን ልትበጠብጥ ስትል በቁጥጥር ስር አውለናታል!” ለማለት ይመች ነበር። ከዚህ በላይ ግን የዘንድሮ ሶስት ሺህ ብር አይደለም ሀገር እና በሶ እንኳን መበጥበጥ ያስችላልን!? ሲሉ አሽሟጠዋል። ለማንኛውም ቀጣዩ ቀጠሮ ለሀምሌ 10 2004 ዓ. ም ሆኗል።


No comments:

Post a Comment