ከሕወሓት መውደቅ በሁዋላ
“አበበ ባልቻ – እንደ ሕወሓት” በሚል ርእስ ‘ሰውለሰው’ በሚለው ድራማ ላይ የፃፍኩትን ተከትሎ አንዳንድ አስተያየቶችን ሳነብ ቆይቻለሁ። አበበ ባልቻ ሕወሓትን ወክሎ ሲተውን እንደነበር በብዙዎች ዘንድ ታምኖበታል። የአስናቀ አወዳደቅ የሕወሓት (አዜብ / መለስ)ን ፍፃሜ የሚያመለክት ስለመሆኑም ሰፊ ግንዛቤ አለ።
በድራማው ውስጥ፣ “የኢትዮጵያ ወኪልማናት?” የሚለው ጥያቄ ላይ ግን ልዩነት አለ። አንድ ሰው በብእር ስም cyberethiopia.com ላይ እንዳሰፈረው ከሆነ የኢትዮጵያ ወኪል ከማህሌት ይልቅ የአስናቀ ሚስት ናት። እንዲህ ሲል አብራርቶታል፣
“…የመስፍን ሚስት ኢትዮጵያን ትወክላለች ተብሏል’ ሲል (መባልአለመባሉ አንድ ነገር ሆኖ)፣ ይሄ ምን ማለት ነው? በድራማው ውስጥ ማህሌትቤተሰቧን የምትወድና “ስኬታማ” እናት ብትሆንም ለባሏ ግልጽነት ይጎድላታል።ሚስጥሯን ከባሏ ይልቅ ለአስናቀ መንገር የሚቀላት እናት ናት። ከአንድም ሁለትሶስት ጊዜ ቃሏን ስታጥፍ ትታያለች። ማህሌት ለባሏ ግልጽ ልትሆንአልቻለችም። ከባሏ ይልቅ ለአስናቀ ግልጽ መሆንን ስለመረጠች፣ ይህ ስህተቷሊያስከትል የነበረውን አደጋ፣ እንደ አጋጣሚ በፊልሙ ድንገተኛ መቋረጥናበአስናቀ መሞት ከአደጋ ያመለጠች ይመስላል። ይህን ታሪክ በምን መልኩ ነውከኢትዮጵያ ጋር የምናያይዘው?
ይልቁን የአስናቀ ሚስት ኢትዮጵያንእንደምትወክል አድርጎ ማየት ይቻላል። አስናቀ ቤቱን ማስተዳደር እንዳልቻለባል፣ እንደ በዝባዥ መሪ ማየት ይቻላል። የአስናቀ ሚስት ቻይነትና ርህሩህነት በአንፃሩ ይስተዋላል። ለልጆቿ ያላት ፍቅር፣ ለአስናቀም ቢሆን ይቅር ባይነቷ፣መልካም ሰው መሆንን እስከመረጠ ድረስ ለሱ ያላትን ፍቅር በማንምእንደማትተካ ማሳየቷ፣ አገርን መወከል የሚያስችል፣ ትክክለኛ የእናትነትና”የሚስትነት” ባህሪ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የአስናቀ ወሮበላነት፣ እንደ አባትልጆቹን በወጉ ማስተዳደርና ማሳደግ አለማቻሉ፣ ሴት ልጁን ለህልፈት መዳረጉ፣ ወንድ ልጁ ከእናቱ ጋር የቁምስቅል ኑሮ እንዲኖር መፍረዱ ወዘተ… በትክክልም የአስናቀ ሚስት አገርን እንድትወክል ያደርጋታል….” (የዚህን ፅሁፍ የቋንቋ አጠቃቀም አርቄዋለሁ)
ከላይ ባለው ፅሁፍ አስተያየት የማይስማሙ አሉ። ይልቁን የአስናቀ ሚስት የትግራይ ክልል ወኪል ስለመሆኗ ይገምታሉ። እኔም ይበልጥ ወደዚህኛው አስተያየት አደላለሁ። በህወሃት አገዛዝ ይበልጥ እየተሰቃየ ያለው ክልል ትግራይ መሆኑን ብዙዎች አያምኑም። እንግዲህ ተደራስያን የጥበብ ስራዎችን በተለያየ መንገድ መገንዘብ መብታቸው ነውና በዚህ ጉዳይ መከራከር ተገቢ አይሆንም።
“ሰውለሰው” ድራማ አለመቋረጡና ከሶስት ሳምንታት በሁዋላ እንደሚቀጥል እየተነገረ ነው። በርግጥ ድራማው ከቀጠለ አጓጊ ይሆናል። ምክንያቱም በድራማው ውስጥ ከህወሃት መውደቅ በሁዋላ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ እንዴት ሊቀጥል እንደሚችል በምናብ ልናይበት እንችላለን። “በድራማው ውስጥ ኢትዮጵያ ማናት?” ለሚለው አከራካሪ ጥያቄም በትክክል ምላሽ ማግኘት ይቻላል።
“ሰውለሰው” የተባለው ድራማ ሲቀጥል ቁልፍ ለሆኑ አንዳንድ ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ምላሽ እያገኘን እንደምንሄድ ግልፅ ነው። እንደ ባለፈው የድራማው ፍፃሜ ከሆነ ህወሃት ወድቋል። በአንፃሩ የመስፍን ወልደማርያም የህጋዊነት የአስተሳሰብ መንፈስ የበላይነቱን ጨብጧል። ማህሌት መንታ መንገድ ላይ ቆማ፣ ያልፈፀመችውን ወንጀል ለመደበቅ እየጣረች ነው። ህወሃት በህገወጥ መንገድ ያከማቸው ገንዘብ ወደ ሼክ መሃመድ አላሙዲ የባንክ አካውንት ተዘዋውሮአል። በዚህ መሃል የትግራይ ክልል (የአስናቀ ሚስት) የምታገኘው ፖለቲካዊ ትርፍ ከቶ ምን ሊሆን ይችላል? የአስናቀ ሚስት በወንጀለኛው ባሏ ሞትና ውድቀት የሚሰማት ምን ይሆን? ከሁለት ሳምንታት በሁዋላ ድራማው ከቀጠለ የዚህን ምስጢር ፍንጭ ለማግኘት እንሞክራለን። ይህ ብቻ አይደለም። በመጪው ዘመን የኦህዴድና የብአዴን አመራር አባላት እጣ ፈንታ ምን ይሆናል? ይህም ትንቢታዊ ታሪክ ይኖረው ይሆናል። የመድሃኒት እናት ከአንድ ልክስክስ የህክምና ባለሙያ ጋር ሆና በልጇ እና በልጅ ልጇ ላይ በፈፀመችው ወንጀል የሚደርስባትን ችግር በቀጣዩ የድራማው ተከታታይ ክፍል እናየው ይሆናል። የመዲ እናት ስትተውን ኦህዴድና ብአዴንን እያሰብን ሊሆን ይገባል።
“ሶስና” ሆና የምትጫወተውን ገፀባህርይ በጣም ነው የምወዳት። ከልጅቱ ጋር ፍቅር ይዞኛል ለማለት እደፍራለሁ። በንግግሯ ወንዶችን ቆሌያቸውን ስትገፋቸው በተለይ ከልቤ እዝናናለሁ። የአበሻ ሴቶች ጥያቄ ወኪል ሆኖ ትታየኛለች። ሳቋ፣ እንባዋ፣ ስድቧ ሁሉም ያምርባታል። የምትሞቅ የምሽት የሻማ ብርሃን ናት። ከወያኔ መውደቅ በሁዋላ አዲሳባ ሄጄ ይህችን ሴት ማግኘቴ አይቀርም። እኔ ወዳለሁበት አካባቢ በድንገት ብቅ ካለችም እንግዳዬ አድርጌ ልጋብዛት እፈልጋለሁ።
“ሰውለሰው” ድራማ ላይ ኢትዮጵያ ተስፋ፣ የሃገር ምሰሶ ሆኖ የሚተውነው ገፀባህርይ መስፍን የሚናገራቸውን በጥንቃቄ መረዳት ይገባል። የምንመኘውን ስርአት የሚያንፀባርቅ ነው።
በመጨረሻ “ሰውለሰው” ድራማ ፖለቲካዊ ይዘት እንዳለው ብዙዎች ሳይገነዘቡ መቆየታቸውን ከተፃፉ አስተያየቶች መረዳት ችያለሁ። ወደፊት በድራማው ላይ ተከታታይ አስተያየት የመስጠት አሳብ አለኝ። እስከዚያው የቃጂማው ጊዮርጊስ በቸር ያሰንብተን።
No comments:
Post a Comment