"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday 27 June 2012

በሐዋሳ ከተማ እና በሲዳማ ዞን ቁጣ ተቀስቅሷል ይህን በሚመለከት ሲአን መግለጫ ሰጥቷል


ሐዋሳ ከተማ ወደ ፌደራል ከተማነት ትዛወራለች የሚል ዜና ከመንግስት ማፈትለኩን ተከትሎ በሐዋሳ ከተማና በተለያዩ የሲዳማ ዞን ወረዳዎች ተቃውሞ ተቀሰቀሰ፡፡ ከስፍራው የደረስን መረጃ  ንዳመለከተው አሁንም ግጭት ይፈጠራል የሚል ስጋት በመኖሩ ከፍረኛ ቁጥር ያላቸው ፌደራል ፖሊሶች በከተማዋ በተጠንቀቅ ላይ ናቸው፡፡ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የደኢህዴን/ኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ  “የሜትሮፖሊታን ከተማችንን እንዴት እንምራው?” የሚል ሰነድ ከግንቦት 27 ቀን 2004 ዓ.ም. ለሲዳማ ዞን ፣ለሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚና በየመንግስት መስሪያ ቤቶች ላሉ ለሲዳማ ብሔር ተወላጅ ኢህአዴግ አባላት ቀርቦ እንደነበር አስታውሷል፡ ፡ በዚህም የሲዳማ ዞን መስተዳደር ሐዋሳ ከተማን ለቆ እንዲወጣ የሚያስገድድ በመሆኑ በከተማዋ እና በዞኑ ህዝብ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠማቸው መግለጫው አትቷል፡፡
በከተማዋና በዞኑ ያሉ የኢህአዴግ አመራሮች ጉዳዩ ወደ ህዝብ ጆሮ አፈትልኮ የወጣውን ድብቅ አጀንዳ ለመካድ መሞከራቸውን ሰአን አስታውቋል፡፡ አጀንዳውንም የሚያራግቡት የተቃዋሚ ፓርቲዎች የሲዳማ አርነት ንቅናቄ፣ አንድነት/ መድረክ እንዲሁም የሲዳማ አርነት ግንባርና ኦነግ ናቸው በማለት በጉዳዩ ላይ ምንም ተሳትፎ የሌላቸውን አካላት ማስወገዝና ስም ማጥፋት ጀምረዋል፡፡ ይህንንም በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ላሉ ተማሪዎች በየሴክተሩ ለሚገኙ የሲዳማ ተወላጅ ለሆኑ የመንግስት ሰራተኞች እና ለብሔሩ ተወላጅ የሆኑ ነጋዴዎችና ባለሀብቶችን በመሰብሰብ ለማሳመን ቢሞክሩም ተቀባይነትን ሳያገኙ
ቀርተዋል፤ የፓርቲው አባላት ያልሆኑት ግን ባይተዋር ተደርገዋል ይላል መግለጫው፡፡

ይህም ከህዝብ እውቅና እና ፈቃድ ውጭ የተሞከረው አጀንዳ ተቃውሞ እንደገጠመው የተረዳው ገዥው አካል በህዝብ የተቀሰቀሰውን ቁጣ ለማክሸፍ የኃይል እርምጃ በመውሰድና በሰላም አብሮ የኖረውን ህዝብ በማጋጨት እንቅስቃሴ ላይ ተሰማርተዋል በማለት ሲአን ኮንኗል፡፡ እንደ ሲአን መግለጫ ከሆነ የሲዳማ ህዝብ ህገመንግስታዊ ክልል የመሆን ጥያቄ ዛሬም ባስቸኳይ እንዲመለስለት፣ ህዝቡ ራሱን
በራሱ የማስተዳደር መብቱ በክልልና በሐዋሳ ከተማ በተጨባጭ እንዲረጋገጥለት ጠይቋል፡፡ በወንድማማች ህዝቦች አብሮ የመኖር ባህልና ፍቅር ውስጥ የጥላቻ ፖለቲካን ለማካሄድ በሲዳማ
ብሔር ድንበሮች አካባቢ ግጭቶችን እየፈጠሩና እያባባሱ የሚገኙ ኃይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ፣ የሲዳማ ብሔር ተወላጆችም ሆኑ ሌሎች በሐዋሳና በዞኑ ውስጥ የሚገኙ ከተሞችና
ገጠሮች የሚኖሩ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እስከ ዛሬ እንዳደረጉት በሰላምና በመከባበር አብሮ የኖሩበትን መልካም እሴት ከሚሸረሽሩ ወገኖች እንዲጠነቀቁ በማሳሰብ ሰኔ 15 ቀን 2004 ዓ.ም ባለ 7 ነጥብ
አቋም በማካተት የሲዳማ አርነት ንቅናቄ(ሰአን) በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ በተያያዘ ዜና በሐዋሳ ከተማና በተለያዩ የሲዳማ ዞን ባሉ ወረዳዎች የተለያዩ ህዝባቢ ተቃውሞዎች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ተጠናክረው መቀጠላቸውን ምንጮቻችን ከስፍራው የጠቆሙ ሲሆን ምክንያቱን ለማጣራት የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም አልተሳካም፡፡ በተለይ በሐዋሳ ከተማ
በተለያዩ ክፍለ ከተሞች እና የመንግስት ት/ቤቶች እንዲሁም በአለታ ወንዶ እና በንሳ ወረዳ አልፎ አልፎ ተቃውሞዎች መታየታቸው ተጠቁሞል፡፡
ከምርጫ ግንቦት 1997 ዓ.ም. በፊት የሲዳማ ዞን ዋበና ከተማ ከሐዋሳ ወደ ይርጋለም ከተማ እንዲሄድ ተደርጎ መቆየቱንና ከምርጫው በኋላ የቀድሞ ቅንጅት ማሸነፉን ተከትሎ ከመስከረም 1998ዓ.ም. ጀምሮ የሲዳማ ዞን ዋና ከተማ ዳግም የደቡብ ክልል መዲና የሆነችው ሐዋሳ እንዲሆን መደረጉ አይዘነጋም፡፡

No comments:

Post a Comment