"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 26 June 2012

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ቶሎ ካልደረስንላቸው እግራቸው ሊቆረጥ ይችላል ተባለ




Tuesday, June 26th, 2012 |
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ቶሎ ካልደረስንላቸው እግራቸው ሊቆረጥ ይችላል ተባለ


(ፍኖተ ነጻነት) ኢትዮጵያን ለ6 ዓመት በፕሬዝዳንትነት ያገለገሉትና አሁን ደግሞ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር በመሆን በተቃውሞው ጐራ ተሰልፈው ገዥውን ፓርቲ እየታገሉ የሚገኙት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እግራቸው ላይ በተከሰተ የደም ዝውውር ችግር የተነሳ በአስቸኳይ ኦፕራሲዮን ካልተደረጉ እግራቸው ሊቆረጥ እንደሚችል የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ገለፀ፡፡
ከዚህ በፊትም ረጅም መንገድ ሲጓዙ እግራቸውን ያማቸው እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን ጀርመን ሀገር ከሄዱ በኋላ የእግራቸው ሕመም ተባብሶ ወደከፋ ደረጃ በመድረሱ እዚያው ጀርመን
ሀገር ሀኪም ቤት በመሄድ ከተመረመሩ በኋላ እንዳረጋገጡት በአስቸኳይ ኦፕራሲዮን ተደርገው ህክምና ካላገኙ ወደ እግራቸው የሚሄደውና የተዘጋው የደም ዝውውር ካልተስተካከለ
በስተቀር ወደ በድንነት እንደሚቀየርና ወደ መቆረጥ እንደሚያመራ ማወቃቸውን ለሕዝብ ግንኙነት እንደገለፁላቸው ለመረዳት ተችሏ ል፡፡
የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ለዝግጅት ክፍላችን እንደተናገሩት ‹‹ለኦፕራሲዮኑ በጠቅላላ 8 ሺ ዩሮ የተጠየቁ ሲሆን ዶ/ር ነጋሶ ይሄን ለመክፈል
የሚያስችል አቅም የላቸውም፡፡ ከዚህ በፊት ለ6 ዓመት ኢትዮጵያን በፕሬዝዳንትነት ያገለገሉ ቢሆንም የጡረታ መብታቸው ሳይከበርላቸው ቀርቷል፡፡ በተለይ ኢህአዴግን በአደባባይ በቃኝ
አልፈልግም ብለው በመናገር ከለቀቁ በኋላ የተለያዩ የማጥቃት ዘመቻዎች ተከፍተውባቸው ነበር፡፡ ስለዚህ ህይወታቸውን በትንሽ የፓርላማ ጡረታ ብቻ ለመግፋት ተገደዋል፡፡ እኚህን የህዝብ
ቅን አገልጋይ ህይወት ለመታደግ የኢትዮጵያ ህዝብ የአቅሙን በማዋጣትና በመረባረብ እንዲታደጋቸው ጥሪያችንን እናስተላልፋለን›› ብለዋል፡፡
ከሌሎች ባለስልጣናት በተለየ መልኩ ምንም አይነት ንብረትና ሀብት የሌላቸው ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ብቸኛው ሃብታቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ሲሆን ህዝቡም ይሄን እንደሚያደርግ እንተማመናለን
በማለት ያላቸውን እምነት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ገልፀዋል፡፡ ዶ/ር ነጋሶን ለመርዳት የሚፈልጉ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሳቸው በተከፈተ የባንክ አካውንት በንብ ባንክ ዑራኤል ቅርንጫፍ የሒሳብ ቁጥር 9095 ማስገባት የሚቻል ሲሆን በተጨማሪም በግንባር ፓርቲው ጽ/ቤት በመገኘትም ማነጋገር ይቻላል ተብሏል፡፡

No comments:

Post a Comment