"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 26 June 2012

የቴዲ አፍሮ ቃለምልልስ – ” እንዲከፋኝ ዕድል አልሰጥም”



የቴዲ አፍሮ ቃለምልልስ – ” እንዲከፋኝ ዕድል አልሰጥም
(ዘ-ሐበሻ) ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በካሳ ሾው ላይ ቀርቦ ተናገረ። ስለ እስር ቤት ዘመኑ ሲናገር “ማረሚያ ቤት አንድ ሰው ሊዝናና የሚሄድበት ቦታ አይደለም፤ በተወሰነ አስር ውስጥ መቆየት ነው። ትልቁ ነጥብ የራሱ የሆነ ቅኝት አለው ብዬ ነው የማምነው። በሕይወት ውስጥ ማናቸውም ነገር ሲገጥሙህ ከተነጫነጭን ቅኝቱ ራሱ ይጠብቃል የበለጠ። ነገር ግን ማለፍ የምትችለው ከዚህ አጥር ወደዚህ ነው ከተባለ አንድ ሰው ማሰብ ያለበት ከዚህ አጥር ወደዚህ እንዴት መኖር እችላለሁ ነው። ምክንያቱም ከዚያ አጥር ማለፍ እንደማይችል ካወቀ ያለው አማራጭ ከዚያ መስመር ወደዚህ መኖር የሚችልበትን ማመቻቸት እንደሆነ ከዚህ በፊት አንድ ወዳጄ ያወራ እንደነበር አውቃለሁና እዛ ውስጥ እንዴት መኖር እችላለሁ ነው ትልቁ ነጥብ። ካለው ነገር ጋር መደራደር ያስፈልጋል። እዚያ በነበርኩበት ጊዜ ማንም ሰው ተገድቦ መኖርን ስለማይወድ ከተገደበብህ ነገር በላይ የተለቀው ነብስህ ምናልባት ውጭ ውሎ ሊገባ ይችላል። የትም ሄዶ ሊመጣ ይችላል። በተመስጦም የፈለክበት ሰፈር ደርሰህ መመለስ ትችላለህ። ልክ ሰው በመኝታው ጊዜው በሕልሙ የትም ቦታ ሄዶ እንደሚመጣው ማለት ነው። ወይም በመጽሐፍት ወይም በመጻፍ የትም ቦታ ደርሰህ ትመጣለህ። እዚያ ካሉት ሰዎች ጋር እንዴት ተስማምተህ ያን ቦታ በትክክል አስደሳች፤ በጣም አስደሳች ባይሆን ጥሩ ሆኖ አንተንም አስተማሪ ሆኖ እንዲያልፍ እንዴት እጠቀምበታለሁ የሚለው ነጥብ ነው ትልቁ ነጥብ። በዚያ መሠረት በተቻለኝ መጠን ራሴን በጣም ያዘነንቅ የተከዘ ሰው እንዳይሆን ምክንያቱም በገጠሙህ ነገሮች ማዘን እና መተከዝ ሁልጊዜ የተሰባበረ መንፈስ ይዞ መውጣትና የተሸነፈ መንፈስ ይዞ መምጣት ያስከትላል። በሕይወት ውስጥ እንደዚህ ዓይነት ነገሮች ሲያልፉ ደግሞ ሁሉ ነገር ለበጎ ይሆናል ብለህ ካሰብክ ለበጎ እንዲሆን የተፈጠረና የተዘጋጀ ሥር አት ነው። በዚህ መሠረት እንዲከፋኝ እድል አልሰጥም። ካለው ነገር ጋር ቀጥሎ በየትኛው ነገር ነው የምደሰተው፤ የምዝናናው በየትኛው ነው፤ ቀጥሎ ይሄንኛውን ጊዜ የማሳልፈው ከየትኛው ጋር ነው? እንዴት እዚህ ቦታ መጣሁ ብሎ መማረር የባሰ ነገሩን ከባድ፤ ከማረሚያ ቤትም ከ እስር ቤትም ያለፈ ከባድ ቦታ ያውለዋል። እንደዚያ እያደረግኩ ነው የቆየሁት” ብሏል። ሙሉ ቃለ ምልልሱን ዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ አስተናግዳዋለች፤ ይመልከቱት።

No comments:

Post a Comment