"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Wednesday 13 June 2012

ሳላዲን እየታከመ ነው – መሪነታችን ይቀጥል ይሆን ወይስ እንደትላንቱ


 (ገነነ መኩሪያ ሊብሮ)

ወደ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ዘገባ ከመሄዳችን አስቀድሞ ኢሳት ቲቪ ላይ ኤርሚያስ አማረ ስለ ሴቶች እና ወንዶቹ ብሄራዊ ቡድናችን እንዲሁም ስለዩሮ 2012 ያቀረበውን ዘገባ ቪዲዮ እንከታተል።

(ሊብሮ) ሳላዲን ሰኢድ በትላንቱ ጨዋታ በመጎዳቱ ለሚቀጥለው ጨዋታ ይደርሳል ወይስ አይደርስም እየተባለ ነው፡፡ ይሳቅ ጋር እየታከመ ነው፡፡ ጥሩ ህክምናም እየተደረገለት እንደሆነም ይነገራል፡፡ በልምምድ ላይ ይታይና ለሚቀጥለው ጨዋታ ይደርሳል አይደርስም የሚለው ይወሰናል፡፡ በነገራችን ላይ ሁሉም ከኳስ ሲይዝ ሳላዲንን ነው የሚፈልገው፡፡ የቡድን ስራ የሚባል ነገር እየጠፋ ነው፡፡ ተጫዋቹ ከተጎዳ ማን ላይ ሊያተኩሩ ነው፡፡ ትላንት ሳላዲንን ፍለጋ በረጅሙ የተላኩ ኳሶች አብዛኞቹን ሴንትራል አፍሪካ ወስዷቸዋል፡፡ እነሱም ሰላዲን ነን እያሉ ነው የሚቀበሉት? ቡድናችን ለአፍሪካ ዋንጫ ቤኒንን ለመግጠም አርብ ይጓዛል፡
፡ ጨዋታው እሑድ ነው፡፡ በ15 ቀን 3 ጨዋታ ማድረጉ ነው፡፡ ቤኒንም እንደኛ 3 ጨዋታ ነው የሚያደርገው፡፡ ቡድናችን ትላንትና በማሸነፉ መሪነት ላይ ተቀምጧል፡፡ 4 ጨዋታዎች ይቀሩታል ሁለት በሜዳው ሁለት ከሜዳው ውጪ፡፡ መሪነቱን ይዞ ይቀጥል ይሆን? አንዳንድ ጊዜ በምድብ ጨዋታ ይመራና ይጠፋል በ5ተኛው አፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ፣ሱዳን፣ኬኒያ ፣ ኡጋንዳ ተመደቡና በመጀመሪያዎቹ 2 ጨዋታዎች ኢትዮጵያ አሸንፋ መራች ከዚያ በኋላ ነጥብ እየጣለች 2ተኛ ሆነች ሱዳን 9 ፣ ኢትዮጵያ 8 ነጥብ ይዘው ጨዋታውን ጨረሱ፡፡ ኢትዮጵያ በኬኒያ 3ለ2 ስትሸነፍ ኬኒያ 2 የኡጋንዳ ተጫዋቾች አሰልፋ ስለነበር ክስ ቀርቦባት ኢትዮጵያ ፎርፌ አገኘችና ምድቡን በአንደኝነት ጨርሳ ለ5ተኛ አፍሪካ ዋንጫ አለፈች፡፡ መጀመሪያ ምድቡን መራንና በኋላ ተንሸራተን በፎርፌ አለፍን፡፡ ከሁሉ የሚገርመው ግን እ.ኤ.አ በ1994 ማለትም ለ19ኛው አፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ፣ኡጋንዳ እና ሱዳን ጋር በዙር ጨዋታ እንድታደርግ ተደለደለች፡፡ ሶስቱም ጠንካራ ነበሩ፡፡(በነገራችን ላይ 19ኛው አፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ናይጄሪያ ነበረች) እያንዳንዱ ቡድን 3 ጨዋታ አድርጎ ያላቸው ነጥብ ሲታይ ኢትዮጵያ መሪነት ላይ ስትቀመጥ ኡጋንዳ 2ተኛ ናይጄሪያ 3ተኛ ነበረች፡፡ ቀጣዩን ጨዋታ እስክናደርግ መሪነቱ ላይ ስለተቀመጥን ዘንድሮ እናልፋለን ተባለ ፣ተፎከረ በኋላ ግን ሁሉም ጨዋታ ሲያልቅ ኢትዮጵያ 3ተኛ ሆነች፡፡ በዚያን ጊዜ ያንን ቦንብ ምድብ መምራታችንን ማረጋገጥ የምትፈል wikpedia ላይ ገብታችሁ 1994 ላይ እስከ 3 ጨዋታ ሁሉም ካደረጉ በኋላ ያለውን ውጤት ማየት ትችላላችሁ፡፡ በሌላ ጊዜ እንደዚሁ በምድብ ጨዋታ መሪነት ላይ እየተቀመጥን እንሸራተታለን፡፡ በእርግጥ ቀደም ሲል ከትልልቅ ቡድኖች ጋር ሰለምንመደብ ብንመራም በዚያው ለመቀጠላችን ስጋት ነበረን፡፡ አሁን ያለንበት ምድብ በእግር ኳስ ያለፈ ታሪካቸው ደካማ በመሆኑ መምራታችን ጥሩ ቢሆንም እስከመጨረሻው በዚሁ እንቀጥላለን ወይ የሚለው ምላሽ ያስፈልገዋል
ሀገርተጫወተአሸነፈተሸነፈአቻአገባገባበትጎልነጥብ
ኢትዮጵያ32105324
ኡጋንዳ31114403
ናይጄሪያ31112113
ሱዳን301214-32

No comments:

Post a Comment