የፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ዘገባ እነሆ፦
ምንጮቻችን እንዳስታወቁት ድብድቡ በጠባቂዎቻቸውና በሥፍራው ለጥበቃ የተመደቡ ፖሊሶች ሊበርድ ባለመቻሉ የዕለቱ የክብር እንግዳ ተነስተው ፀቡ እንዲበርድ አድርገዋል ብለዋል፡፡
በሥፍራው የነበሩ የአይን እማኞች ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፁት በዕለቱ የውሃና ማዕድን ሚኒስትሩ አቶ አለማየሁ ተገኑ የእለቱ የክብር እንግዳ፣ የስፖርት ኮሚሽነሩ አቶ አብዲሳ ያደታ፣ የደደቢት ስፖርት ክለብ መሥራችና ፕሬዝዳንት ኰሎኔል አወል ኢብራሂም እና ሌሎች ባለሥልጣናት በእንግድነት ተገኝተው ነበር፡፡ ኰሎኔል አወል ከአቶ አብዲሳ ኋላ ተቀምጠው በስሜታዊነት ተውጠው እየጮሁ ተጫዋቾችን ‹ያዘው! ሩጥ! አቀብል› እያሉ ይጮሁ እንደነበር ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ አቶ አብዲሳ ያደታ ኮሎኔሉን ‹‹እባክህን ጆሮዬን አሞኛል አትጩህብኝ!›› በማለት ሲጠይቋቸው ኰሎኔሉም ‹‹ጆሮህን ካመመህ እዚህ ምን አስቀመጠህ? ሄደህ አትተኛም!›› በማለታቸው አለመግባቱ ተፈጠረ ይላሉ የአይን እማኞቹ፡፡
ስለ ዕለቱ ግጭትም ሲያብራሩም ‹‹አለመግባቱ ተካሮ ሁለቱም ለድብድብ ሲነሱ የባለሥልጣናቱ አጃቢዎችና በሥፍራው ለጥበቃ የተመደቡ ፖሊሶች ፀቡን ለማብረድ ቢሞክሩም ሊበርድ ባለመቻሉ
የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ አለማየሁ ተገኑ ተነስተው ገላጋይ በመሆናቸው ፀቡ ሊበርድ ችሎአል” ሲሉ ገልፀዋል፡፡
No comments:
Post a Comment