"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Tuesday 12 June 2012

ቂ.ቂ.ቂ.ቂ..ቂ.. መለስ ዜናዊ አኬልዳማ ፊልምን በአበበ ገላው ላይም አሠሩ

(ከሮቤል ሔኖክ)
አቶ መለስ የአእምሮ ኪሳራ እንደደረሰባቸው የሚያሳይ ዜና ነው ዋልታ ያስደመጠን። አበበ ገላው በአሜሪካ መንግስት በየትኛውም ስብሰባ ላይ እንዳይገኝ ታገደ ይልና ዜናው ዝርዝሩ ላይ ሲገባ ደግሞ አቶ ብርሃኔ ገብረክርስቶስ (የሰሎሜ ታደሰ…) “እኔን እንደሚገባኝ… የአሜሪካ መንግስት በሚያዘጋጃቸው ስብሰባ ላይ አበበ እንዳይገኝ ታግዷል” ይሉናል። አቶ ብርሃኔ የመለስ ታማኝ ቡችላ ምን ማለታቸው ይሆን እርሳቸውን የገባቸው እኛን ያልገባን የአበበ መታገድ? ነው ወይስ ለወያኔዎች የሚገባቸው እንግሊዘኛ እና ለኛ የሚገባን እንግሊዘኛ ይለያል። እስኪ እንሳቅ። አቶ መለስ ሽንፈታቸውን ለማሸነፍ ብለው ቢያሰሩበትም ግን የተሸነፉበትን ቪድዮ አብረን እያየን አብረን እንሳቅባቸው። ቂ.ቂ.ቂ.ቂ.ቂ…
 | 

አበበ ገላው መልስ ሰጠ

(ዘ-ሐበሻ) ከሰሞኑ በወያኔ ሚዲያዎች በአበበ ላይ የተጀመረውን ዘመቻ በማስመልከት ጋዜጠኛው መልስ ሰጠ። አዲስ አድማስ ጋዜጣን ጀምሮ የተለያዩ የወያኔ ደጋፊ ሚድያዎች ስለ ጋዜጠኛው የተሳሳቱ መረጃዎችን ለሕዝብ በማድረስ ላይ መሆናቸውን አበበ “በጣም አሳፋሪ ነው” ብሎታል። አቶ መለስ ዜናዊ አንገታቸውን በአደበባይ ሲደፉ፤ ደጋፊዎቻቸው ጭምር የሚገበት አጥተው አንገታቸውን የደፉ ቢሆንም አንገታቸውን ቀና ለማድረግ 21 ዓመት ሙሉ የሰለቸንን ፕሮፓጋንዳቸውን በአበበ ላይ ቀጥለዋል። የአበበን ምላሽ እነሆ በቪድዮ፦
Short URL: http://www.zehabesha.com/?p=7683

No comments:

Post a Comment