"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Saturday 16 June 2012

ሉሲዎች ለአፍሪካ ዋንጫ አለፉ፤ ቡድናችንን የጫነው አውሮፕላን ከአደጋ ተረፈ




(፟ዘ-ሐበሻ) በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን መጠሪያው “እቱ መላ ምቺ” ይሰኝ ነበር። ዛሬ ስማቸው ተቀይሮ “ሴቶቹ ዋሊያዎች” ወይም “ሉሲ” በመባል ይጠራሉ።በተለያዩ ጊዜያት አኩሪ ድሎችን እያስመዘገቡ የሚገኙት ሉሲዎች ዛሬ ወደ ታንዛኒያ ተጉዘው አኩሪ ድል ይዘው ተመልሰዋል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ብርቱካን ገ/ክርስቶስ በ65ደቂቃ ባስቆጠረችው ግብ የታንዛኒያ አቻውን 1-0 በማሸነፍ ኢኳቶሪያል ጊኒ ለምታዘጋጀው ስምንተኛ የአፍሪካ ማለፉን አረጋግጧል። የሴቶች የእግር ኳስ ቡድን ተጫዋቾቻችን 60ሺ ተመልካች በሚይዘው በታንዛኒያ ስታዲየም ፍፁም የጨዋታ የበላይነት ነው ጨዋታውን በድል የማጠናቀቅ የቻሉት፡፡ ቡድኑ በታንዛኒያ ባስመዘገበው ድል ኢትዮጵያ ቡድን ለሁለተኛ ጊዜ ለአፍሪካ ጨጫቻ እንዲያልፍ አድርገዋል፡፡
በ እንዲህ እንዳለ ነገ ቤኒን ላይ ላለበት ወሳኝ ጨዋታ የወንዶቹ ብሔራዊ ቡድናችን በቴክኒክ ችግር ምክንያት ከመንገድ ተመልሶ እንደነበር ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ አመለከተ፡፡ አውሮፕላኑ ወደ ቤኒን መብረር ከጀመረ በኋላ የቴክኒክ ችግር ገጥሞት ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ለመቆም ተገዶ ነበር። የአይን እማኞች እንደሚሉት በአሁኑ ሰዓት አውሮፕላኑ በሰላም ካረፈ በኋላ የእሳት አደጋ መኪና ሲከተለው ነበር ብለዋል። ሆኖም ግን አውሮፕላኑ ከቆመ በኋላ መንገደኞቹ በሰላም መውረዳቸውንና ምንም የተጎዳ ሰው እንደሌለ ከአዲስ አበባ ለዘ-ሐበሻ ድረ ገድ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

No comments:

Post a Comment