"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Thursday 14 June 2012

ተወዛዋዥ ኩሪባቸው ወ/ማርያም ተወገዘች




Wednesday, June 13th, 2012 | Posted by

(ከሮቤል ሔኖክ)
“የበላችበትን ወጪት ሰባሪ” ነበር ያለው በዋሽንግተን ዲሲ የሚኖረው ኢትዮጵያዊው ስንታየሁ ገብሩ። “ኩሪን ለረዥም ጊዜ በውዝዋዜዋ አደንቃት ነበር። በተለይ በዋሽንግተን ዲሲ ከማሪቱ ለገሠ ጋር ከ15 ዓመት በፊት እዚህ ስትመጣ በችግር ላይ በነበረችበት ወቅት የደረሰላት የኢትዮጵያ ሕዝብ ነበር። ይህች አርቲስት ዲሲ በወረቀት እጦት ስትሰቃይ ቆይታ ለአሜሪካ መንግስት ጥገኝነት ጥያቄ አቅርባ ወረቀት ያገኘችው በባል ነው። በችግሯ ጊዜ የደረሰላትን ሕዝብ ክዳ ዛሬ ከደም መጣጭ ወያኔዎች ጋር ሆና ለሆዷ መሰለፏ አሳፍሮኛል። ከዚህ በኋላ በዚህች አርቲስት ዝግጅት ላይ አልገኝም” ሲል አስተያየቱን የቀጠለው ስንታየሁ “ኩሪ ስሟን ቀይራ እፈሪ ብትባል ይሻላል” ብሏል።
በወያኔና በአላሙዲ ገንዘብ ዋናውን ESFNA በእጃቸው ማስገባት ያቃታቸው ተላላኪዎች ተገንጥለው በመውጣት ተለጣፊ የስፖርት ፌዴሬሽን በማዘጋጀት በዋሽንግተን ዲሲ የስፖርት ፌስቲቫል ቢያዘጋጁም፤ ከወያኔ በስተቀር የትኛውም ሕዝብ አልተቀበላቸውም። በድፍረት ድምጻዊ ነኝ ትበል እንጂ እኛ በውዝዋዜዋ የምናውቃት ኩሪባቸው ወልደማርያም ለሆዷ በማደር አርቲስቶቹን ዳላስ ላይ ከሚከፈላችሁ ገንዘብ የበለጠ ይከፈላችኋል በማለት ዘፋኞችን ልታባብል ብትሞክርም አልተሳካላትም። ለዘፋኞች በዋሽንግተኑ ኮንሰርት ተሳተፉ በሚል የፊርማ ወረቀትና የ$3000 በስማቸው የተጻፈ ቼክ ይዛ ብትዞርም ዘፋኞች ሁላ እምቢ ብለዋታል።

“ኩሪ ከአላሙዲ ተላላኪ ወያኔዎች እጅ የተቀበለችው አርቲስቶችን እንድታስተባበር $10000 ነው። ሆኖም ግን ከዚህ በኋላ በየትኛውም እርሷ ባለችበት መድረክ ማንም አይገኝም። ካሴት ላውጣ ብትል አታገኝም። ወያኔን ደግፋ ሕዝቡን ማሳዘኗ የኋላ የኋላ ጥበቡን ትታ እንደ አቦነሽ አድነው ታክሲ መንዳት፤ እንደሰለሞን ተካልኝ ኪሳራ፣ እንደነዋይ ደበበ የሙዚቃ አቀናባሪ ማጣት ውስጥ ትገባለች” ያለን አስተያየት ሰጪ ደግሞ ፍሰሃ ነው ከቨርጂኒያ።
ከአላሙዲ ሰዎች ጋር በቅርበት እየሠራች የነበረችውና የአሜሪካንን መንግስት መኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት ወያኔን ስታወግዝ የነበረችው፤ አሁን ደግሞ ዞራ የወያኔ አቃጣሪ የሆነችው ኩሪ በድምጻዊያኑ ዘንድ “እምቢ ያመጣሽውን ዶላር እዛው፤ እኛ የምንሄደው ዳላስ ነው” ተብላለች። አብዛኛው ድምጻዊ ወደ ዳላስ የሚሄድ ሲሆን በዲሲው የተለጣፊዎችና በባዶ ስታዲየም የሚደረገው ዝግጅት ላይ የሚገኙት ተወዛዋዦችና የመንደር ዲጄዎች ብቻ ናቸው።
በዲሲው ዝግጅት ላይ የሚገኙትና በፍላየር ላይ የታዩት ተወዛዋዦች የመለስ መንግስት ለሥራ ውጭ ልኳቸው እዚህ ጥገኝነት የጠየቁ ይገኙበታል። እነዚህ በአንድ በኩል ወያኔ አላሠራ አለን ብለው ከሃገር ወጥተው የአሜሪካ መንግስት ወረቀት እንዲሰጣቸው የሚማጸኑት ተወዛዋዦች ዛሬ አብረው ከወያኔ ጋር መሥራታቸውን ያዩ ወገኖች እናጋልጣቸዋለን እያሉ በመዛት ላይ ናቸው። ወያኔ በሃገር ላይ እንዳልኖር አደረገኝ ብሎ እዚህ ሃገር እየኖሩ ለወያኔ ዞሮ መሰለል በአሜሪካ ሕግ ወንጀል ነው።
ተወዛዋዥ ኩሪ ለሆዷ ስትል ሙያዋን በማራከስ የ14 ዓመቱን ሕጻን ነብዩን ከገደሉት ወገኖች ጋር ቆማ መታየቷ ያሳፈራቸው ኢትዮጵያውያን በዲሲ ዓይንሽ ለአፈር ያሏት ሲሆን፤ በአደባባይ ሲያገኟትም “ሆዳም፤ ሌባ” እያሉ እየሰደቧት ይገኛሉ። ከአሁን በኋላም በመንገድ ላይ የሚያገኟት እርሷን ሲያዩ ምራቃቸውን ለመትፋት ሁሉ እንደተዘጋጁ በተለያዩ ቦታዎች ተሰምተዋል።
ሌላው ሆዳም የቀድሞው የወያኔው ራድዮ ፋና የተጻፈ አንባቢ ወንደሰን ከበደ ነው። ይህ ሰው የዲሲውን ዝግጅት መድረክ በመምራት ገንዘብ ተቀብሏል። በርግጥ ይህ ሰው ደም ፈሶ የተገኘን ገንዘብን ለመብላት የመጀመሪያው አይደለም። የርሱን ጉድ ደግሞ በቀጣይ እጽፈዋለሁ። ወንደሰን ማን ነው? ከወያኔ ጋር የነበረው ፍቅር ከአዲስ አበባ እስከ ዲሲ በቀጣይ እመልስበታለሁ። ይጠብቁኝ። ጉዱ ይፍረጠረጣል።

No comments:

Post a Comment