"Food is nothing without freedom! We Need Freedom

”Food is nothing without freedom! We Need Freedom!

Sunday 10 June 2012

ለዳያስፖራ ኢትዮጵያዉያን በያላችሁበት!


ለዳያስፖራ ኢትዮጵያዉያን በያላችሁበት!

ዓመታዊዉ 29ኛ ዓመት የኢትዮጵያ የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል በዳላስ ቴክሳስ ከጁላይ 1 እስከ ጁላይ 7 ቀን 2012 ድረስ ይካሄዳል።
ይህንን በዉጭ አገር የሚገኙ የኢትዮጵያዉያን የጋራ መድረክ ለማፍረስ ጥቂት ግለሰቦች ያደረጉት ሙከራ ይታወሳል። ይሁን እንጂ፣ ተልእኮዋቸዉ ከሽፎ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን (ESFNA) የበለጠ ተጠናክሮ ወጥቷል።
ሆኖም፣ በሼህ አላሙዲን ገንዘብ የሚተነፍሱ ግለሰቦች ዛሬም ቢሆን እርኩስ ተልእኮዋቸዉን ለመወጣት ከመሞከር አልታቀቡም።
ቡድኑ በአንጋፋዉ (ESFNA) ስም ላይ (ONE) በመቀጠል እኔ ነኝ “አንጋፋዉ” ለማለት የፈጸመዉ ተንኮል በፍ/ቤት ሳይቀር ተበይኖበት ስሙን እንዳይጠቀም ተገዷል። በዚህም ሳያበቃ፣ የሁሉም ኢትዮጵያዉያን የስፖርት ማሕበር አንድ (AESAONE) በሚል ስያሜ በዋሽንግተን ዲሲ ከጁላይ 1 እስከ ጁላይ 7 ቀን 2012 ድረስ የሰፖርት ፌስቲቫል አዘጋጃለሁ ብሎ ተነስቷል። አዘጋጅቻለሁ የሚለዉ ፌስቲቫል ቀናት፤ በዳላስ ከሚካሄደዉ የአንጋፋዉ ESFNA ታላቅ የሰፖርትና የባሕል ፌስቲቫል ዝግጅት ቀናት ጋር ተመሳሳይ እንዲሆን በማድረግ ያሰራጨዉ ጥሪ የቡድኑን መሰሪ ተልእኮ በግልጽ የሚያስረዳ ይመስለናል።

በቅድሚያ ቡድኑ የጥቂት ሆድ አደሮች ጥርቅም እንጂ ከአንጋፋዉ የሰሜን አሜሪካዉ የኢትዮጵያ የስፖርት ፌዴሬሽን ተገንጥሎ የወጣ አንጃ አለመሆኑን ግልጽ ለማድረግ እንፈልጋለን።Boycott Alamoudi's gathering AESAONE በተጨማሪ ሆድ አደሮቹ ከሼሁ በሚቸራቸዉ ገንዘብ ከርሳቸዉን ከመሙላት ባሻገር፤ ከነርሱና ከሼሁ ጀርባ የወያኔ አገዛዝ እንዳለበትና ዓላመዉም ኢትዮጵያዉያንን የመከፋፈል አጀንዳ ቅጥያ መሆኑን ማስገንዘብ እንፈልጋለን።
ዉድ ወገኖች!
በመስጠም ላይ ያለ ሰዉ፣ አድኖ ላያድነዉ አረፋም ቢሆን ይጨብጣል እንዲሉ፣ አንዴ በአባይ ስም፣ አሁን ደግሞ በስፖርት ሽፋን የተገመደዉ ተንኮል ለወያኔ የቋንጃ እከክ የሆነበትን ዲያስፖራ ለማወናበድ የታለመ ነዉ። ታዲያ ይህን እየተካሄደ ያለዉን ሴራ እንደወትሮዉ ሁሉ ዛሬም ለማክሸፍ ሃገርና ወገን ወዳድ ኢትዮጵያዉያን ሁሉ በጋራ እንሰለፍ።
በዲያስፖራ በሚገኙ የኢትዮጵያ ነጻ የብዙሃን መገናኛ ተቋማት የተመሰረተዉ Boycott TPLF ግብረሃይል፤ ይህን በስፖርት ሽፋን ኢትዮጵያዉያንን ለማወናበድና ለመከፋፈል የተዶለተዉን ሴራ በጋራ እንድናከሽፍ ጥሪዉን ያቀርባል።
በዋሺንግተን ዲሲ የወያኔ መልእክተኞች ትላንት ተቋቋምን ብለዉ ዛሬ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር አዉጥተዉ አዘጋጀን የሚሉትን ፌስቲቫል፣ ለአንጋፋዉ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ የስፖርት ፌዴሬሽን ጥንካሬና ለኢትዮጵያዉያን አንድነት የቆመ ዜጋ ሁሉ እንዳይተባበረዉና እንዲያገልለዉ ጥሪ እናደርጋለን። በሚሊዮን ዶላር የተከራዩት ስታዲዮም የሰዓት እላፊ የታወጀበት መንደር ሆኖ ጭር እንዲል እንድናደርገዉ እንጠይቃለን።
በአንጻሩ ወደ ዳላስ ቴክሳስ በማምራት ከጁላይ 1 እስከ ጁላይ 7 ቀን 2012 ድረስ በሚካሄደዉ የሁላችንም መገናኛ፣ መዝናኛና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ በሆነዉ 29ኛዉ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን ፌስቲቫል ላይ በመሳተፍ በዓሉን የደመቀ እንድናደርገዉ እናሳስባለን።
የወያኔ ሴራ በየፈርጁ ይከሽፋል!
Boycott TPLF ግብረሃይል  

No comments:

Post a Comment